ኢሳይያስ 34:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ጌታ መሥዋዕት በባሶራ፥ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና፥ የጌታ ሰይፍ በደም ትርሳለች፤ ስብ ትጠግባለች፤ በበግ ጠቦትና በፍየል ደምም፥ በአውራም በግ ኩላሊት ስብ ትወፍራለች። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተነክራለች፤ ሥብ ጠግባለች፤ በበግ ጠቦትና በፍየል ደም፣ በአውራም በግ ኵላሊት ሥብ ተሸፍናለች። እግዚአብሔር በባሶራ ከተማ መሥዋዕት፣ በኤዶምም ታላቅ ዕርድ አዘጋጅቷልና። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ለመሥዋዕት የቀረቡ የበግና የፍየል ጠቦቶች በሚሠዉበት ጊዜ ደማቸውና ስባቸው ሰይፉን እንደሚሸፍን የእርሱም ሰይፍ በኤዶማውያን ደምና ስብ ይሸፈናል፤ እግዚአብሔር ይህን መሥዋዕት በቦጽራ ከተማ፥ ይህንንም ታላቅ ዕርድ በኤዶም ምድር ያቀርባል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 እግዚአብሔር መሥዋዕት በባሶራ፥ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተሞልታለች፤ በበግ ስብ፥ በፍየል ደምም፥ በአውራም በግ ስብ ወፍራለች። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 እግዚአብሔር መሥዋዕት በባሶራ፥ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተሞልታለች፥ በስብም፥ በበግ ጠቦትና በፍየል ደምም፥ በአውራም በግ ኵላሊት ስብ ወፍራለች። Ver Capítulo |