የሕዝቡንም ቅሬታ እጥላለሁ፤ በጠላቶቻቸውም እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ለጠላቶቻቸውም ሁሉ ምርኮና ብዝበዛ ይሆናሉ፤
ኤርምያስ 19:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህም ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምክር አፈርሳለሁ፤ በጠላቶቻቸው ፊት በጦርና ነፍሳቸውን በሚሹት እጅ እጥላቸዋለሁ፤ ሬሳቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል አድርጌ እሰጣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘በዚህ ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ዕቅድ አፈርሳለሁ፤ በጠላቶቻቸው ፊት ሕይወታቸውን በሚሹት እጅ በሰይፍ እንዲወድቁ አደርጋለሁ፤ ሬሳቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ምግብ አድርጌ እሰጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህም ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምክር አፈርሳለሁ፥ በጠላቶቻቸውም ፊት በሰይፍና ነፍሳቸውን በሚሹት እጅ እጥላቸዋለሁ፥ ሬሳቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል አድርጌ እሰጣለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ያቀዱት ነገር ሁሉ በዚህ ስፍራ እንዳይፈጸም አደርጋለሁ፤ ጠላቶቻቸው ድል እንዲነሡአቸውና በጦርነትም እንዲገድሉአቸው አደርጋለሁ፤ ሬሳቸውንም የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት እንዲበሉት አደርጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚህም ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምክር አፈርሳለሁ፥ በጠላቶቻቸውም ፊት በሰይፍና ነፍሳቸውን በሚሹት እጅ እጥላቸዋለሁ፥ ሬሳቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል አድርጌ እሰጣለሁ። |
የሕዝቡንም ቅሬታ እጥላለሁ፤ በጠላቶቻቸውም እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ለጠላቶቻቸውም ሁሉ ምርኮና ብዝበዛ ይሆናሉ፤
ስለዚህ፥ እነሆ፥ ይህ ሕዝብ በድጋሚ እንዲፈልስ አደርጋለሁ፤ አፈልሳቸዋለሁም፤ የጥበበኞችንም ጥበብ አጠፋለሁ፤ የአስተዋዮችንም ማስተዋል እሰውራለሁ።”
ምክርን ብትመክሩም እግዚአብሔር ምክራችሁን ይለውጣል፤ የተናገራችሁትም ነገር አይሆንላችሁም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።
እነርሱም፦ ወዴት እንሂድ ቢሉህ፥ አንተ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለሞት የሆነ ወደ ሞት፥ ለሰይፍም የሆነ ወደ ሰይፍ፥ ለራብም የሆነ ወደ ራብ፥ ለምርኮም የሆነ ወደ ምርኮ ትላቸዋለህ።
ሰባት የወለደች ባዶ ቀረች፤ ነፍስዋም ተጨንቃለች፤ በቀትር ጊዜ ፀሐይዋ ገብታባታለች፤ አፍራለች፤ ተዋርዳማለች፤ የተረፉትንም በጠላቶቻቸው ፊት ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
“በክፉ ሞት ይሞታሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ አይቀበሩምም፤ ነገር ግን በመሬት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ፤ በሰይፍም ይወድቃሉ፤ በራብም ይጠፋሉ፤ ሬሳዎቻቸውም ለሰማይ ወፎችና ለዱር አራዊት መብል ይሆናሉ።”
ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ ስጥ፤ ለሰይፍም እጅ አሳልፈህ ስጣቸው፤ ሚስቶቻቸውም የወላድ መካንና መበለቶች ይሁኑ፤ ወንዶቻቸውም በሞት ይጥፉ፤ ጐልማሶቻቸውም በጦርነት ጊዜ በሰይፍ ይመቱ።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና አገልጋዮቹን፥ ከቸነፈርና ከሰይፍ፥ ከራብም በዚህች ከተማ የቀሩትን ሕዝቡንም በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ፥ በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውንም በሚሹት እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እርሱም በሰይፍ ስለት ይመታቸዋል፤ አያዝንላቸውም፤ አይራራላቸውም፤ አይምራቸውም።”
ነፍስህንም ለሚሹአት፥ ከፊታቸውም የተነሣ ለምትፈራቸው እጅ፥ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆርና ለከለዳውያንም እጅ እሰጥሃለሁ።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ይችን ከተማ ለከለዳውያን እጅና ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እርሱም ይይዛታል።
ለጠላቶቻቸው እጅ፥ ነፍሳቸውንም ለሚሹአት እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።
ነፍሳቸውንም በሚፈልጉ ሰዎች እጅ፥ በባቢሎንም ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ፥ በአገልጋዮቹም እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ እንደ ቀድሞው ዘመን የሰው መኖሪያ ትሆናለች፥ ይላል እግዚአብሔር።”
በወደዱአቸውና በአመለኳቸው፥ በተከተሉአቸውና በፈለጓቸው፥ በሰገዱላቸውም በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም፥ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጓቸዋል፤ አያለቅሱላቸውም፤ አይቀብሯቸውምም፤ በምድርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ።
“እናንተስ፦ ጥበበኞች ነን የእግዚአብሔርም ሕግ ከእኛ ጋር ነው እንዴት ትላላችሁ? እነሆ ጸሓፊዎቻቸውም ከንቱ ሆኑ፤ በሐሰትም ብርዕ ተጠቀሙ።
ጥበበኞች አፍረዋል፤ ደንግጠውማል፤ ተማርከውማል፤ እነሆ የእግዚአብሔርን ቃል ጥለዋል፤ ምን ዓይነት ጥበብ አላቸው?
ፊቴንም አከብድባችኋለሁ፤ በጠላቶቻችሁም ፊት ትወድቃላችሁ፤ የሚጠሏችሁም ያሸንፉአችኋል። ማንም ሳያሳድዳችሁ ትሸሻላችሁ።
የቃል ኪዳኔንም በቀል ይበቀልባችሁ ዘንድ ሰይፍ አመጣባችኋለሁ፤ ወደ ከተማችሁም ትሸሻላችሁ፤ ቸነፈርንም እሰድድባችኋለሁ። በጠላቶቻችሁም እጅ ተላልፋችሁ ትሰጣላችሁ፤
የኦሪትን ሕግ የፈጸመ ብቻ ተስፋ የሚያገኝ፥ ዓለምንም የሚወርስ ቢሆን ኖሮ፥ ለአብርሃም እምነቱ ባልጠቀመውም ነበር፤ ተስፋውንም ባላገኘም ነበር።
እግዚአብሔር ዛሬ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጣል፤ እመታህማለሁ፤ ራስህንም ከአንተ እቈርጠዋለሁ፤ ሬሳህንና የፍልስጥኤማውያንንም ሠራዊት ሬሶች ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ዛሬ እሰጣለሁ። ምድር ሁሉ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር እንዳለ ያውቃሉ፤