Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሮሜ 3:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 እን​ግ​ዲህ በእ​ም​ነት ኦሪ​ትን እን​ሽ​ራ​ለን? አን​ሽ​ርም፤ ኦሪ​ትን እና​ጸ​ና​ለን እንጂ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ታዲያ እንዲህ ከሆነ ከእምነት የተነሣ ሕግን ዋጋ የሌለው እናደርግ ይሆን? ፈጽሞ አይደረግም፤ ሕጉን እናጸናለን እንጂ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ስለዚህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? በጭራሽ! ነገር ግን ሕግን እናጸናለን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ታዲያ፥ በእምነት ምክንያት ሕግን እንሽራለን ማለት ነውን? አይደለም፤ ይልቅስ ሕግን አጥብቀን እንይዛለን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እንግዲህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? አይደለም፤ ሕግን እናጸናለን እንጂ።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 3:31
27 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ጸጋ አል​ክ​ድም፤ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት የሚ​ጸ​ድቁ ከሆነ እን​ኪ​ያስ ክር​ስ​ቶስ በከ​ንቱ ሞተ።


“ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ የዘ​ነ​ጋሁ ሳል​ሆን፥ በክ​ር​ስ​ቶስ ሕግም ሳለሁ ሕግ የሌ​ላ​ቸ​ውን እጠ​ቅ​ማ​ቸው ዘንድ ሕግ ለሌ​ላ​ቸው ሕግ እን​ደ​ሌ​ለው ሆን​ሁ​ላ​ቸው።


የኦ​ሪት ጽድቅ ፍጻ​ሜስ ለሚ​ያ​ም​ኑ​በት ሁሉ በክ​ር​ስ​ቶስ ማመን ነው።


እናን ያጸ​ድ​ቀን ዘንድ፥ የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ ሠርቶ እንደ ፈጸመ ሰው ያደ​ር​ገን ዘንድ፤ ይህም በመ​ን​ፈ​ሳዊ ሕግ ጸን​ተው ለሚ​ኖሩ ነው እንጂ በሥጋ ሕግ ለሚ​ሠሩ አይ​ደ​ለም።


እኔስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕያው ሆኜ በሁ​ለ​ተ​ኛው ሕግ እኖር ዘንድ ከቀ​ደ​መው ሕግ ተለ​የሁ።


በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ እኔ በልቤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ እገ​ዛ​ለሁ፤ በሥ​ጋዬ ግን ለኀ​ጢ​አት ሕግ እገ​ዛ​ለሁ።


በል​ቡ​ናዬ ውስጥ ያለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ መል​ካም ነው።


የኦ​ሪ​ትን ሕግ የፈ​ጸመ ብቻ ተስፋ የሚ​ያ​ገኝ፥ ዓለ​ም​ንም የሚ​ወ​ርስ ቢሆን ኖሮ፥ ለአ​ብ​ር​ሃም እም​ነቱ ባል​ጠ​ቀ​መ​ውም ነበር፤ ተስ​ፋ​ው​ንም ባላ​ገ​ኘም ነበር።


መጽ​ሐፍ፥ “በነ​ገ​ርህ ትጸ​ድቅ ዘንድ፥ በፍ​ር​ድ​ህም ታሸ​ንፍ ዘንድ” ብሎ እንደ ተና​ገረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተና ነውና፥ ሰውም ሁሉ ሐሰ​ተና ነውና።


አባቱን ወይም እናቱን አያከብርም፤” ትላላችሁ፤’ ስለ ወጋችሁም የእግዚአብሔርን ቃል ሻራችሁ።


እላችኋለሁና ጽድቃችሁ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ካልበለጠ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።


ኢየሱስም መልሶ “አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና” አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ምስ​ጋ​ና​ውን ያጸ​ድ​ቅና ከፍ ያደ​ርግ ዘንድ መከረ።


የበ​ደ​ልን ነገር በእኔ አወጡ። የተኛ ሰው ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​ነ​ቃ​ምን?


የወ​ይኑ ባለ​ቤት በመጣ ጊዜ እን​ግ​ዲህ ምን ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል? ይመ​ጣል፤ እነ​ዚ​ያ​ንም ገባ​ሮች ይገ​ድ​ላ​ቸ​ዋል፤ ወይ​ኑ​ንም ለሌ​ሎች ገባ​ሮች ይሰ​ጣል፤” ቃሉ​ንም ሰም​ተው፥ “አይ​ሆ​ንም፤ እን​ዲህ አይ​ደ​ረ​ግም” አሉ።


ሰነ​ፎ​ችን ልባ​ሞች የም​ታ​ደ​ርግ፥ ሕፃ​ና​ትን የም​ታ​ስ​ተ​ምር፥ ጻድ​ቅና የም​ት​ከ​ብ​ር​በ​ትን የኦ​ሪ​ትን ሕግ የም​ታ​ውቅ የም​ት​መ​ስል፥


እን​ዲ​ህማ ከሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ለም እን​ደ​ምን ይፈ​ር​ዳል?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios