አካዝም፥ “እኔ ባሪያህና ልጅህ ነኝ፤ መጥተህ ከተነሡብኝ ከሶርያ ንጉሥና ከእስራኤል ንጉሥ እጅ አድነኝ” ብሎ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ቴልጌልቴልፌልሶር መልእክተኞችን ላከ።
ኤርምያስ 13:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንቺ ትምህርት ያስተማርሻቸው አለቆችሽ ሆነው በጐበኙሽ ጊዜ ምን ትያለሽ? እንደ ወላድ ሴት ምጥ አይዝሽምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልዩ ወዳጆች እንዲሆኑሽ ያስተማርሻቸው፣ ባለሥልጣን ሲሆኑብሽ ምን ትያለሽ? እንደምትወልድ ሴት፣ ምጥ አይዝሽምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዳጆችሽ እንዲሆኑ ያስተማርሻቸውን በራስሽ ላይ አለቆች ባደረጋቸው ጊዜ ምን ትያለሽ? እንደ ወላድ ሴት ምጥ አይዝሽምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወዳጆች ብለሽ ያቀረብሻቸው ወራሪዎችሽና ገዢዎችሽ ሲሆኑ ምን ትያለሽ? በምጥ ላይ እንዳለች ሴት ሕመም አይሰማሽምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወዳጆችሽ እንዲሆኑ ያስተማርሻቸውን በራስሽ ላይ አለቆች ባደረጋቸው ጊዜ ምን ትያለሽ? እንደ ወላድ ሴት ምጥ አይዝሽምን? |
አካዝም፥ “እኔ ባሪያህና ልጅህ ነኝ፤ መጥተህ ከተነሡብኝ ከሶርያ ንጉሥና ከእስራኤል ንጉሥ እጅ አድነኝ” ብሎ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ቴልጌልቴልፌልሶር መልእክተኞችን ላከ።
ሽማግሎች ይደነግጣሉ፤ እንደምትወልድ ሴትም ምጥ ይይዛቸዋል፤ እርስ በርሳቸውም ይገዳደላሉ፤ ይደነቃሉ፤ ፊታቸውም እንደ እሳት ይንበለበላል።
ስለዚህም ወገቤ ሕማም ተሞላ፤ እንደምትወልድ ሴትም ምጥ ያዘኝ፤ ከሕማሜ የተነሣ አልሰማም፤ ከድንጋጤም የተነሣ አላይም።
እግርሽን ከሰንከልካላ መንገድ፥ ጕሮሮሽንም ከውኃ ጥም ከልክዪ፤ እርስዋ ግን፥ “እጨክናለሁ፤ እንግዶችንም ወድጄአለሁ” ብላ ተከተለቻቸው።
አንቺ በሊባኖስ የምትቀመጪ፥ በዝግባ ዛፍም ውስጥ የምታለቅሺ ሆይ! ምጥ እንደ ያዛት ሴት ሕማም በያዘሽ ጊዜ እንዴት ትጨነቂያለሽ!
ጠይቁ፤ ወንድ ይወልድ እንደ ሆነ ተመልከቱ፤ ስለ ምን ሰው ሁሉ እንደ ወላድ እጁን በወገቡ ላይ አድርጎ፥ ፊቱም ሁሉ ወደ ጥቍረት ተለውጦ አየሁ?
እነሆ በይሁዳ ቤት የቀሩትን ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ያወጣሉ፤ እነዚያም ሴቶች፦ ባለሟሎችህ አታልለውሃል፤ አሸንፈውህማል፤ እግሮችህ ግን አሁን በጭቃ ውስጥ ከገቡ እነርሱ ከአንተ ወደ ኋላ ተመልሰዋል ይላሉ።
አንቺስ ምን ታደርጊያለሽ? ቀይ በለበስሽ ጊዜ፥ በወርቅ አንባርም ባጌጥሽ ጊዜ፥ ዐይንሽንም በኵል በተኳልሽ ጊዜ፥ በከንቱ ታጌጫለሽ፤ ፍቅረኞችሽ አቃለሉሽ፥ ነፍስሽን ይሹአታል።
እንደምታምጥ፥ የበኵር ልጅዋንም እንደምትወልድ ሴት ጩኸት፥ ጩኸትሽን ሰምቻለሁና፤ የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድካም ሰለለ፤ እጆችዋንም ትዘረጋለች፤ ተገድለው ከሞቱት የተነሣ ነፍሴ ዝላለችና ወዮልኝ! አለች።
ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእጃቸው ያጨበጭባሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?
አንተ ሰው ስትሆን ለሚገድሉህ ሰዎች፦ እግዚአብሔር ነኝ ትላቸዋለህን? ሰው ነህ እንጂ እግዚአብሔር አይደለህም።