Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 13:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ሽማ​ግ​ሎች ይደ​ነ​ግ​ጣሉ፤ እን​ደ​ም​ት​ወ​ልድ ሴትም ምጥ ይይ​ዛ​ቸ​ዋል፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ይገ​ዳ​ደ​ላሉ፤ ይደ​ነ​ቃሉ፤ ፊታ​ቸ​ውም እንደ እሳት ይን​በ​ለ​በ​ላል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ሽብር ይይዛቸዋል፤ ሥቃይና ጭንቀት ይደርስባቸዋል፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ያምጣሉ፤ እርስ በርሳቸው በድንጋጤ ይተያያሉ፤ ፊታቸውም በፍርሀት ቀይ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሽብር ይይዛቸዋል፤ ሥቃይና ጭንቀት ይደርስባቸዋል፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ያምጣሉ፤ እርስ በርሳቸው በድንጋጤ ይተያያሉ፤ ፊታቸውም በፍርሀት ቀይ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የምትወልድ ሴት በምጥ እንደምትሠቃይ እነርሱም በፍርሃት ይሠቃያሉ፤ እርስ በርሳቸው በፍርሃት ይተያያሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ይደነግጣሉ፥ ምጥና ሕማም ይይዛቸዋል፥ እንደምትወልድ ሴትም ያምጣሉ፥ አንዱም በሌላው ይደነቃል፥ ፊታቸውም የነበልባል ፊት ነው።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 13:8
21 Referencias Cruzadas  

ስለ​ዚ​ህም የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸው ሰዎች እጆ​ቻ​ቸው ዝለ​ዋል፤ ደን​ግ​ጠ​ውም አፍ​ረ​ዋል፤ እንደ ምድረ በዳ ሣር፥ እንደ ለም​ለ​ምም ቡቃያ፥ በሰ​ገ​ነ​ትም ላይ እን​ዳለ ሣር፥ ሳይ​ሸት ዋግ እንደ መታ​ውም እህል ሆነ​ዋል።


ወን​ድም ወን​ድ​ሙን አያ​ድ​ንም፥ ሰውም አያ​ድ​ንም፤ ቤዛ​ው​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ሰ​ጥም፥


የፀ​ነ​ሰች ሴት ለመ​ው​ለድ ስት​ቀ​ርብ እን​ደ​ም​ት​ጨ​ነ​ቅና በምጥ እን​ደ​ም​ት​ጮህ፥ አቤቱ፥ እን​ዲሁ በፊ​ትህ ለወ​ዳ​ጅህ ሆነ​ናል።


አንቺ ትም​ህ​ርት ያስ​ተ​ማ​ር​ሻ​ቸው አለ​ቆ​ችሽ ሆነው በጐ​በ​ኙሽ ጊዜ ምን ትያ​ለሽ? እንደ ወላድ ሴት ምጥ አይ​ዝ​ሽ​ምን?


ጠይቁ፤ ወንድ ይወ​ልድ እንደ ሆነ ተመ​ል​ከቱ፤ ስለ ምን ሰው ሁሉ እንደ ወላድ እጁን በወ​ገቡ ላይ አድ​ርጎ፥ ፊቱም ሁሉ ወደ ጥቍ​ረት ተለ​ውጦ አየሁ?


እን​ደ​ም​ታ​ምጥ፥ የበ​ኵር ልጅ​ዋ​ንም እን​ደ​ም​ት​ወ​ልድ ሴት ጩኸት፥ ጩኸ​ት​ሽን ሰም​ቻ​ለ​ሁና፤ የጽ​ዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድ​ካም ሰለለ፤ እጆ​ች​ዋ​ንም ትዘ​ረ​ጋ​ለች፤ ተገ​ድ​ለው ከሞ​ቱት የተ​ነሣ ነፍሴ ዝላ​ለ​ችና ወዮ​ልኝ! አለች።


ፈር​ተው ወደ ኋላ ሲመ​ለሱ፥ ኀያ​ላ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ሲደ​ክሙ፥ ወደ ኋላ​ቸ​ውም ሳይ​መ​ለ​ከቱ ፈጥ​ነው ሲሸሹ ለምን አየሁ? በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ይከ​ቡ​አ​ቸ​ዋል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሐቄ​ር​ዮት ተያ​ዘች፤ አን​ባ​ዎ​ች​ዋም ተወ​ስ​ደ​ዋል፤ በዚ​ያም ቀን የሞ​አብ ኀያ​ላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆ​ናል።


እነሆ እንደ ንስር ወጥቶ ይመ​ለ​ከ​ታል፤ ክን​ፉ​ንም በባ​ሶራ ላይ ይዘ​ረ​ጋል፤ በዚ​ያም ቀን የኤ​ዶ​ም​ያስ ኀያ​ላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆ​ናል።


ደማ​ስቆ ደከ​መች፤ ተሸ​ብ​ራም ሸሸች፤ እን​ቅ​ጥ​ቅ​ጥም ያዛት፤ እንደ ወላ​ድም ሴት ጣርና ምጥ ያዛት።


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ውካ​ታ​ቸ​ውን ሰም​ቶ​አል፤ እጁም ደክ​ማ​ለች፤ ምጥ ወላድ ሴትን እን​ደ​ሚ​ይ​ዛ​ትም ጭን​ቀት ይዞ​ታል፤


የባ​ቢ​ሎን ተዋ​ጊ​ዎች መዋ​ጋ​ትን ትተ​ዋል፤ በአ​ም​ባ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ውስጥ ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ኀይ​ላ​ቸ​ውም ጠፍ​ቶ​አል፤ እንደ ሴቶ​ችም ሆነ​ዋል፤ ማደ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ነድ​ደ​ዋል፤ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ተሰ​ብ​ረ​ዋል።


ለና​ጌ​ብም ዱር እን​ዲህ በለው፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በአ​ንተ ውስጥ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በው​ስ​ጥ​ህም ያለ​ውን የለ​መ​ለ​መ​ው​ንና የደ​ረ​ቀ​ውን ዛፍ ሁሉ ይበ​ላል፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም ነበ​ል​ባል አይ​ጠ​ፋም፤ ከደ​ቡ​ብም ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ ፊት ሁሉ ይቃ​ጠ​ል​በ​ታል።


ምጥ እንደ ያዛት ሴት ጭንቅ ይይ​ዘ​ዋል፤ ይህ ልጅ ሰነፍ ነው፤ አዋ​ቂም አይ​ደ​ለም፤ በል​ጆ​ችም ተግ​ሣጽ አይ​ጸ​ናም።


ከፊ​ታ​ቸው አሕ​ዛብ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ የሰ​ውም ፊት ሁሉ እንደ ድስት ጥላ​ሸት ይጠ​ቍ​ራል።


ባዶና ባድማ ምድረ በዳም ሆናለች፣ ልብ ቀልጦአል፥ ጕልበቶችም ተብረክርከዋል፣ በወገብም ሁሉ ሕማም አለ፥ የሰዎችም ሁሉ ፊት ጠቍሮአል።


ሴት በም​ት​ወ​ል​ድ​በት ጊዜ ወራቷ ስለ ደረሰ ታዝ​ና​ለች፤ ነገር ግን ልጅ​ዋን ከወ​ለ​ደች በኋላ ስለ ደስ​ታዋ ከዚያ ወዲያ ምጥ​ዋን አታ​ስ​በ​ውም፤ በዓ​ለም ወንድ ልጅን ወል​ዳ​ለ​ችና።


ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ከቶም አያመልጡም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos