እስራኤልን ከሰጠኋቸው ምድር አጠፋቸዋለሁ፤ ለስሜም የቀደስሁትን ይህን ቤት ከፊቴ እጥለዋለሁ፤ እስራኤልም በአሕዛብ ሁሉ መካከል ለጥፋትና ለተረት ይሆናሉ።
ሆሴዕ 9:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ምድር ላይ አይቀመጡም፤ ኤፍሬምም በግብፅ ይቀመጣል፤ በአሦርም ርኩስ ነገርን ይበላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ምድር አይቀመጡም፤ ኤፍሬም ወደ ግብጽ ይመለሳል፤ የረከሰውንም ምግብ በአሦር ይበላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ምድር ላይ አይቀመጡም፤ ኤፍሬምም ወደ ግብጽ ይመለሳል፥ በአሦርም ርኩስን ነገር ይበላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር በሰጣቸው ምድር አይኖሩም፤ ነገር ግን ተገደው ወደ ግብጽ ይመለሳሉ፤ ወደ አሦርም ሄደው በሥርዓት ንጹሕ ያልሆነ ምግብ ይበላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔር ምድር ላይ አይቀመጡም፥ ኤፍሬምም ወደ ግብጽ ይመለሳል፥ በአሦርም ርኵስን ነገር ይበላሉ። |
እስራኤልን ከሰጠኋቸው ምድር አጠፋቸዋለሁ፤ ለስሜም የቀደስሁትን ይህን ቤት ከፊቴ እጥለዋለሁ፤ እስራኤልም በአሕዛብ ሁሉ መካከል ለጥፋትና ለተረት ይሆናሉ።
በሆሴዕም በዘጠነኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤልንም ወደ አሶር አፈለሰ፤ በአላሔና በአቦር፤ በጎዛንም ወንዝ፤ በሜዶንም ከተሞች አኖራቸው።
ምድሬንም በተጠሉ በጣዖቶቻቸው ሬሳዎች አርክሰዋልና፥ ርስቴንም አስጸያፊ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋልና አስቀድሜ የበደላቸውንና የኀጢአታቸውን ዕዳ ሁለት እጥፍ እከፍላቸዋለሁ።”
ፍሬዋንና በረከቷንም ትበሉ ዘንድ ወደ ቀርሜሎስ አገባኋችሁ፤ ነገር ግን በገባችሁ ጊዜ ምድሬን አረከሳችሁ፤ ርስቴንም አጐሳቈላችሁ።
እግዚአብሔርም፥ “እንዲሁ የእስራኤል ልጆች እነርሱን በምበትንባቸው በአሕዛብ መካከል ንጹሕ ያልሆነ እንጀራቸውን ይበላሉ” አለ።
እንደ ወፍ ከግብፅ፥ እንደ ርግብም ከአሶር ምድር እየተንቀጠቀጡ ይወጣሉ፤ ወደ ቤታቸውም እመልሳቸዋለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
ወደ ከንቱ ነገር ተመለሱ፤ እንደ ጠማማ ቀስትም ሆኑ፤ አለቆቻቸውም ከምላሳቸው ስንፍና የተነሣ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ይህም በግብፅ ምድር ውስጥ መሳለቂያ ይሆንባቸዋል።
መሥዋዕትንም ቢሠዉ፥ ሥጋንም ቢበሉ፤ እግዚአብሔር አይቀበላቸውም፤ አሁንም በደላቸውን ያስባል፤ በኀጢአታቸውም ይበቀላቸዋል፤ እነርሱም ወደ ግብፅ ይመለሳሉ፤ በአሦርም ርኩስ ነገርን ይበላሉ።
ስለዚህ እነሆ ከግብፅ ጕስቍልና የተነሣ ሸሽተው ይሄዳሉ፤ ሜምፎስም ትቀበላቸዋለች፤ በማከማስም ይቀብሩአቸዋል፤ ጥፋትም ወርቃቸውን ይወርሳል፥ እሾህም በድንኳኖቻቸው ውስጥ ይበቅላል።
ምድሪቱም ከእናንተ በፊት የነበረውን ሕዝብ እንደ ተፋች ባረከሳችኋት ጊዜ እናንተንም እንዳትተፋችሁ ተጠንቀቁ።
“እንግዲህ ትቀመጡባት ዘንድ የማገባችሁ ምድር እንዳትተፋችሁ ትእዛዜን ሁሉ፥ ፍርዴንም ሁሉ ጠብቁ፤ አድርጉትም።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሚስትህ በከተማይቱ ውስጥ አመንዝራ ትሆናለች፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ምድርህም በገመድ ትከፈላለች፤ አንተም በረከሰች ምድር ትሞታለህ፤ እስራኤልም ከምድሩ ተማርኮ ይሄዳል።”
እግዚአብሔርም በጎ ያደርግልህ ዘንድ፥ ያበዛህም ዘንድ ደስ ይለው እንደ ነበረ፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ሲያጠፋህ፥ ሲያፈርስህም ደስ ይለዋል፤ ትወርሳትም ዘንድ ከምትገባባት ምድር ትነቀላለህ ።
ከእንግዲህ ወዲህ ተመልሰህ አታያትም ባልሁህ መንገድም እግዚአብሔር በመርከብ ወደ ግብፅ ይመልስሃል፤ በዚያም ለጠላቶቻችሁ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮች ትሆናላችሁ፤ የሚራራላችሁም አይኖርም።”
ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትገቡባት ምድር ፈጥናችሁ እንድትጠፉ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በእናንተ አስመሰክራለሁ፤ ፈጽሞም ትጠፋላችሁ እንጂ ረዥም ዘመን አትቀመጡባትም።
አምላካችሁ እግዚአብሔር የተናገረው መልካም ነገር ሁሉ እንደ ደረሰላችሁ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከዚህች ከመልካሚቱ ምድር እናንተን እስኪያጠፋችሁ ድረስ እግዚአብሔር እንዲሁ ክፉን ነገር ሁሉ ያመጣባችኋል።