ዘፍጥረት 32:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለባሪያህ በአደረግኸው በምሕረትህና በእውነትህም ሁሉ በጎውን አድርግልኝ፤ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበርና፥ አሁን ግን የሁለት ክፍል ሠራዊት ሆንሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ባሪያህ እስካሁን ላደረግህልኝ ቸርነትና ታማኝነት ብቁ አይደለሁም፤ ዮርዳኖስን ስሻገር በእጄ ላይ ከነበረው በትር በቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን ይኸው ሁለት ሰራዊት ሆኛለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለባርያህ ካሳየኸው ከጽኑ ፍቅርና ከታማኝነትህ ሁሉ ትንሽ ስንኳ የማይገባኝ ነኝ፥ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበር፥ አሁን ግን ለሁለት ወገን የተከፈልኩ ሆንሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ባሪያህ ይህን ያኽል ቸርነትና ታማኝነት ልታሳየኝ የሚገባኝ አልነበርኩም፤ ዮርዳኖስን ተሻግሬ ስመጣ ከምመረኰዘው በትር በቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን እነዚህን በሁለት ቡድን የተከፈሉ ወገኖች ይዤ ተመልሻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለባሪያህ ከሠራኸው ከምሕረትህን ከእውነትህም ሁሉ ትንሽ ስ ስንኳ የማይገባኝ ነኝ፤ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበርና አሁን ግን የሁለት ክፍል ሠራዊት ሆንሁ። |
እንዲህም አለ፥ “የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ እማልድሃለሁ፤ መንገዴን ዛሬ በፊቴ አቅናልኝ፤ ለጌታዬም ለአብርሃም ምሕረትን አድርግ።
እንዲህም አለ፥ “ቸርነቱንና እውነቱን ከጌታዬ ያላራቀ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ ለእኔም ወደ ጌታዬ ወደ አብርሃም ወንድም ቤት መንገዴን አቀናልኝ።”
እነሆም፥ እግዚአብሔር በላዩ ቆሞበት ነበር፥ እንዲህም አለ፥ “የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ አትፍራ፥ ይህችን አንተ የተኛህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁ፤
እነሆም፥ እኔ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፤ በምትሄድበትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚያችም ምድር እመልስሃለሁ፤ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።”
ያዕቆብም እጅግ ባለጠጋ ሆነ፤ ሴቶችም ወንዶችም አገልጋዮች፥ ብዙ ከብትም፤ ላሞችም፥ በጎችም፥ ግመሎችና አህዮችም ሆኑለት።
ላሞችንም፥ ግመሎችንም፥ አህዮችንም፥ በጎችንም፥ ወንዶች አገልጋዮችንም፥ ሴቶች አገልጋዮችንም አገኘሁ፤ አሁንም በፊትህ ሞገስን አገኝ ዘንድ ለጌታዬ ለዔሳው ለመንገር ላክሁ።”
ያዕቆብም እጅግ ፈራ፤ የሚያደርገውንም አጣ። ከእርሱም ጋር ያሉትን ሰዎች ላሞችንም፥ ግመሎችንም፥ በጎችንም ሁለት ወገን አድርጎ ከፈላቸው፤
ንጉሡ ዳዊትም ገባ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ፥ “ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ ይህን ያህል የወደድኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድን ነው?
መድኃኒቴ በእግዚአብሔር ነው፤ ክብሬም በእግዚአብሔር ነው፥ የረድኤቴ አምላክ፥ ተስፋዬም እግዚአብሔር ነው።
እኔም፥ “ከንፈሮች የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸው በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዐይኖች የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ!” አልሁ።
በስጦታው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቸርነትና የእግዚአብሔርን ምስጋና ዐሰብሁ፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል ወገኖች እውነተኛ ፈራጅ ነው፤ እንደ ቸርነቱና እንደ ጽድቁ ብዛትም ይቅርታውን ያመጣልናል።
እንዲሁ እናንተም ያዘዝኋችሁን ሁሉ አድርጋችሁ ‘እኛ ሥራ ፈቶች አገልጋዮች ነን፤ ለመሥራትም የሚገባንን ሠራን’ በሉ።”
ስምዖን ጴጥሮስም ይህን አይቶ ከጌታችን ከኢየሱስ እግር በታች ሰገደና፥ “እኔ ኀጢአተኛ ሰው ነኝና አቤቱ ከእኔ ፈቀቅ በል፤” አለው።
እነሆ እናንተ ስላገበራችሁኝ በመመካቴ ሰነፍ ሆንሁ፤ ለእኔማ በእናንተ ዘንድ ልከብርና እናንተም ምስክሮች ልትሆኑኝ ይገባኝ ነበር፤ እኔ እንደ ኢምንት ብሆንም ዋናዎቹ ሐዋርያት ሁሉ ከሠሩት ሥራ ያጐደልሁባችሁ የለምና።
ነገር ግን ዛሬ እንደ ሆነ ለአባቶችህ የማለውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ እርሱ ኀይልን ስለሚሰጥህ አምላክህን እግዚአብሔርን አስበው።
እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ልበሱ፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል።