Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ዘዳግም 8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የተ​ስ​ፋ​ይ​ቱን ምድር ለመ​ው​ረስ የተ​ሰጠ መመ​ሪያ

1 “በሕ​ይ​ወት እን​ድ​ት​ኖሩ፥ እን​ድ​ት​በ​ዙም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ገብ​ታ​ችሁ እን​ድ​ት​ወ​ር​ሱ​አት፥ ዛሬ ለአ​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛዝ ሁሉ ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ።

2 አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ት​ንህ ዘንድ፥ በል​ብ​ህም ያለ​ውን ትእ​ዛ​ዙን ትጠ​ብቅ ወይም አት​ጠ​ብቅ እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ፥ ሊያ​ስ​ጨ​ን​ቅህ በም​ድረ በዳ የመ​ራ​ህን መን​ገድ ሁሉ አስብ።

3 ሰውም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ በሚ​ወጣ ነገር ሁሉ በሕ​ይ​ወት እን​ዲ​ኖር እንጂ ሰው በእ​ን​ጀራ ብቻ በሕ​ይ​ወት እን​ዳ​ይ​ኖር ያስ​ታ​ው​ቅህ ዘንድ አስ​ጨ​ነ​ቀህ፥ አስ​ራ​በ​ህም፤ አን​ተም ያላ​ወ​ቅ​ኸ​ውን፥ አባ​ቶ​ች​ህም ያላ​ወ​ቁ​ትን መና መገ​በህ።

4 የለ​በ​ስ​ኸው ልብስ አላ​ረ​ጀም፤ እግ​ር​ህም አል​ነ​ቃም፤ እነሆ፥ አርባ ዓመት ሆነ።

5 ሰውም ልጁን እን​ደ​ሚ​ገ​ሥጽ እን​ዲሁ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አን​ተን እን​ዲ​ገ​ሥጽ በል​ብህ ዕወቅ።

6 በመ​ን​ገ​ዱም እን​ድ​ት​ሄድ፥ እር​ሱ​ንም እን​ድ​ት​ፈራ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ጠብቅ።

7 አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መል​ካ​ምና ሰፊ ምድር፥ ከሜ​ዳና ከተ​ራ​ሮች የሚ​መ​ነጩ የውኃ ጅረ​ቶ​ችና ፈሳ​ሾ​ችም ወዳ​ሉ​ባት ምድር፥

8 ስንዴ፥ ገብ​ስም፥ ወይ​ንም፥ በለ​ስም፥ ሮማ​ንም ወደ ሞሉ​ባት፥ ወይ​ራም፥ ቅቤም፥ ማርም ወደ ሞሉ​ባት ምድር፥

9 ሳይ​ጐ​ድ​ልህ እን​ጀ​ራን ወደ​ም​ት​በ​ላ​ባት፥ አን​ዳ​ችም ወደ​ማ​ታ​ጣ​ባት ምድር፥ ድን​ጋ​ይዋ ብረት ወደ ሆነ፥ ከተ​ራ​ራ​ዋም መዳብ ወደ​ሚ​ማ​ስ​ባት ምድር ያገ​ባ​ሃል።

10 ትበ​ላ​ማ​ለህ፤ ትጠ​ግ​ብ​ማ​ለህ፤ ስለ ሰጠ​ህም ስለ መል​ካ​ሚቱ ምድር አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ና​ለህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ይ​ረሱ የተ​ሰጠ ማስ​ጠ​ን​ቀ​ቂያ

11 “ዛሬ እኔ አን​ተን የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛ​ዙ​ንና ፍር​ዱን፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ባለ​መ​ጠ​በቅ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ት​ረሳ ተጠ​ን​ቀቅ፤

12 ከበ​ላ​ህና ከጠ​ገ​ብህ በኋላ፥ መል​ካ​ምም ቤት ሠር​ተህ ከተ​ቀ​መ​ጥ​ህ​ባት በኋላ፤

13 የላ​ምና የበግ መንጋ ከበ​ዛ​ልህ በኋላ፥ ብር​ህና ወር​ቅ​ህም፥ ያለ​ህም ሁሉ ከበ​ዛ​ልህ በኋላ፥ ልብህ እን​ዳ​ይ​ታ​በይ፤

14 ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ህን፥

15 የሚ​ና​ደፍ እባ​ብና ጊንጥ፥ ጥማ​ትም ባለ​ባት፥ ውኃም በሌ​ለ​ባት፥ በታ​ላ​ቂ​ቱና በም​ታ​ስ​ፈ​ራው ምድረ በዳ የመ​ራ​ህን፥ ከጭ​ንጫ ድን​ጋ​ይም ጣፋጭ ውኃን ያወ​ጣ​ል​ህን፥

16 በመ​ጨ​ረ​ሻም ዘመን መል​ካም ያደ​ር​ግ​ልህ ዘንድ ሊፈ​ት​ንህ፥ ሊያ​ዋ​ር​ድ​ህም አባ​ቶ​ችህ ያላ​ወ​ቁ​ትን መና በም​ድረ በዳ የመ​ገ​በ​ህን አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ት​ረሳ፥

17 በል​ብ​ህም፦ በጕ​ል​በቴ፥ በእ​ጄም ብር​ታት ይህን ሁሉ ታላቅ ኀይል አደ​ረ​ግሁ እን​ዳ​ትል።

18 ነገር ግን ዛሬ እንደ ሆነ ለአ​ባ​ቶ​ችህ የማ​ለ​ውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ እርሱ ኀይ​ልን ስለ​ሚ​ሰ​ጥህ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አስ​በው።

19 አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሞ ብት​ረሳ፥ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት ብት​ከ​ተል፥ ብታ​መ​ል​ካ​ቸ​ውም፥ ብት​ሰ​ግ​ድ​ላ​ቸ​ውም፥ ፈጽሞ እን​ደ​ም​ት​ጠፋ እኔ ዛሬ​ውኑ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን አስ​መ​ሰ​ክ​ር​ብ​ሃ​ለሁ።

20 የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስለ አል​ሰ​ማ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊ​ታ​ችሁ እን​ደ​ሚ​አ​ጠ​ፋ​ቸው እንደ አሕ​ዛብ ሁሉ እና​ን​ተም እን​ዲሁ ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos