Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ በዋ​ሽ​ንት የዳ​ዊት መዝ​ሙር።

1 አቤቱ ጌታ​ችን፥ ስምህ በም​ድር ሁሉ እጅግ ተመ​ሰ​ገነ፥ ምስ​ጋ​ናህ በሰ​ማ​ዮች ላይ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና።

2 ከሕ​ፃ​ና​ትና ከሚ​ጠቡ ልጆች አፍ ምስ​ጋ​ናን አዘ​ጋ​ጀህ፥ ስለ ጠላት፥ ጠላ​ት​ንና ግፈ​ኛን ታጠ​ፋው ዘንድ።

3 የጣ​ቶ​ች​ህን ሥራ ሰማ​ዮ​ችን፥ አንተ የሠ​ራ​ሃ​ቸ​ውን፥ ጨረ​ቃ​ንና ከዋ​ክ​ብ​ትን እና​ያ​ለ​ንና።

4 ታስ​በው ዘንድ ሰው ምን​ድን ነው? ትጐ​በ​ኘ​ውም ዘንድ የሰው ልጅ ምን​ድን ነው?

5 ከመ​ላ​እ​ክት ጥቂት አሳ​ነ​ስ​ኸው፤ በክ​ብ​ርና በም​ስ​ጋና ዘውድ ከለ​ል​ኸው።

6 በእ​ጆ​ች​ህም ሥራ ሁሉ ላይ ሾም​ኸው፤ ሁሉን ከእ​ግ​ሮቹ በታች አስ​ገ​ዛ​ህ​ለት፥

7 በጎ​ች​ንም በሬ​ዎ​ች​ንም ሁሉ፥ ደግ​ሞም የም​ድረ በዳ​ውን እን​ስ​ሶች፥

8 የሰ​ማ​ይ​ንም ወፎች፥ የባ​ሕ​ር​ንም ዓሦች፥ በባ​ሕር መን​ገድ የሚ​ሄ​ደ​ው​ንም ሁሉ።

9 አቤቱ፥ ጌታ​ችን፥ ስምህ በም​ድር ሁሉ እጅግ ተመ​ሰ​ገነ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos