Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 17:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እን​ዲሁ እና​ን​ተም ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁን ሁሉ አድ​ር​ጋ​ችሁ ‘እኛ ሥራ ፈቶች አገ​ል​ጋ​ዮች ነን፤ ለመ​ሥ​ራ​ትም የሚ​ገ​ባ​ንን ሠራን’ በሉ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ስለዚህ እናንተም የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፣ ‘ከቍጥር የማንገባ ባሮች ነን፤ ልናደርገው የሚገባንን ተግባር ፈጽመናል’ በሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ ‘የማንጠቅም አገልጋዮች ነን፤ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል፤’ በሉ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እናንተም እንዲሁ የታዘዛችሁትን ሁሉ በፈጸማችሁ ጊዜ፥ ‘የማንጠቅም አገልጋዮች ነን፤ የፈጸምነውም ግዳጃችንን ብቻ ነው’ በሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 17:10
20 Referencias Cruzadas  

ብድ​ሩን ይከ​ፍል ዘንድ ለእ​ርሱ አስ​ቀ​ድሞ ማን አበ​ደ​ረው?”


ሁላ​ችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነ​ናል፤ ጽድ​ቃ​ች​ንም ሁሉ እንደ መር​ገም ጨርቅ ነው፤ በኀ​ጢ​አ​ታ​ችን ምክ​ን​ያት እንደ ቅጠል ረግ​ፈ​ናል፤ እን​ዲ​ሁም ነፋስ ጠራ​ርጎ ወስ​ዶ​ናል።


ሁሉም ተባ​ብሮ በደለ፤ በጎ ሥራ​ንም የሚ​ሠራ የለም፤ አንድ ስንኳ ቢሆን የለም።


የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።’


እኔም፥ “ከን​ፈ​ሮች የረ​ከ​ሱ​ብኝ ሰው በመ​ሆኔ፥ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸው በረ​ከ​ሱ​ባ​ቸው ሕዝብ መካ​ከል በመ​ቀ​መጤ ዐይ​ኖች የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ ንጉ​ሡን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ አዩ ጠፍ​ቻ​ለ​ሁና ወዮ​ልኝ!” አልሁ።


እን​ግ​ዲህ ጌታው ያዘ​ዘ​ውን ሥራ​ውን ቢሠራ ለዚያ አገ​ል​ጋይ ምስ​ጋና አለ​ውን?


ከዚህ በኋላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሲሄድ በሰ​ማ​ር​ያና በገ​ሊላ መካ​ከል ዐለፈ።


እነ​ር​ሱም ገብ​ተው ወረ​ሱ​አት፤ ነገር ግን ቃል​ህን አል​ሰ​ሙም፤ በሕ​ግ​ህም አል​ሄ​ዱም፤ ያደ​ር​ጉም ዘንድ ካዘ​ዝ​ሃ​ቸው ሁሉ ምንም አላ​ደ​ረ​ጉም፤ ስለ​ዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመ​ጣ​ህ​ባ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios