Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 17:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ነገር ግን ወደ መን​ገዴ እንደ ምመ​ለስ እተ​ማ​መ​ና​ለሁ፤ እጆ​ችም የነጹ ናቸ​ውና፤ ደስ​ታ​ዬን አገ​ኛ​ታ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ጻድቃን ግን በያዙት መንገድ ይጸናሉ፤ ንጹሕ እጅ ያላቸውም እየበረቱ ይሄዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ጻድቅ ግን መንገዱን ያጠነክራል፥ እጁም ንጹሕ የሆነ ሰው ኃይልን እየጨመረ ይሄዳል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ይሁን እንጂ ጻድቃን ከእውነት መንገድ ፈቀቅ አይሉም፤ ንጹሖችም በብርታት ላይ ብርታትን ይጨምራሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ጻድቅ ግን መንገዱን ያጠንክራል፥ እጁም ንጹሕ የሆነ ሰው ኃይልን እየጨመረ ይሄዳል።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 17:9
26 Referencias Cruzadas  

የጻድቃን መንገዶች ግን እንደ ብርሃን ይበራሉ። ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየጨመሩ ይበራሉ።


ንጹ​ሕን ሰው ያድ​ነ​ዋል፤ በእ​ጅ​ህም ንጽ​ሕና ትድ​ና​ለህ።”


ብልህ ሰው ፈርቶ ከክፉ ይሸሻል፤ አላዋቂ ግን ራሱን ተማምኖ ከኃጥኣን ጋር አንድ ይሆናል።


አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ት​ህን አሳ​የን፥ አቤቱ፥ ማዳ​ን​ህን ስጠን።


እኅቴ ናት ያለኝ እርሱ አይ​ደ​ለ​ምን? እር​ስዋ ደግሞ ራስዋ ወን​ድሜ ነው አለች፤ በልቤ ቅን​ነ​ትና በእጄ ንጹ​ሕ​ነት ይህን አደ​ረ​ግ​ሁት።”


አንተ ባሕ​ርን በኀ​ይ​ልህ አጸ​ና​ሃት፤ አንተ የእ​ባ​ቡን ራስ በውኃ ውስጥ ሰበ​ርህ።


እነሆ፥ አሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጠ​ላ​ቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደ​ረገ፤ ዞርሁ በድ​ን​ኳ​ኑም መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋሁ፥ እል​ልም አል​ሁ​ለት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥ እዘ​ም​ር​ለ​ት​ማ​ለሁ።


ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።


ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንድ በርኵስ ማለት ባልታጠበ እጅ እንጀራ ሲበሉ አዩ።


ቅን​ነት ከም​ድር በቀ​ለች፥ ጽድ​ቅም ከሰ​ማይ ተመ​ለ​ከተ።


አቤቱ፥ መን​ገ​ድ​ህን አመ​ል​ክ​ተኝ፤ ፍለ​ጋ​ህ​ንም አስ​ተ​ም​ረኝ።


ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኀጢአተኞች! እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ! ልባችሁን አጥሩ።


እር​ም​ጃዬ ከመ​ን​ገዱ ፈቀቅ ብሎ እንደ ሆነ፥ ልቤም ዐይ​ኔን ተከ​ትሎ እንደ ሆነ፥ ጉቦም በእጄ ተጣ​ብቆ እንደ ሆነ፥


በሳ​ኦል ቤትና በዳ​ዊት ቤት መካ​ከል ለብዙ ጊዜ ጦር​ነት ሆነ፤ የዳ​ዊት ቤት እየ​በ​ረታ፥ የሳ​ኦል ቤት ግን እየ​ደ​ከመ የሚ​ሄድ ሆነ።


እና​ን​ተን ማጽ​ደቅ ከእኔ ዘንድ ይራቅ፤ እስ​ክ​ሞ​ትም ድረስ ፍጹ​ም​ነ​ቴን ከእኔ አላ​ር​ቅ​ምና።


ጽድ​ቅን እየ​ሠ​ራሁ አል​ጠ​ፋም፤ ያደ​ረ​ግ​ሁት ክፉ ነገር አይ​ታ​ወ​ቀ​ኝ​ምና።


እኔ ንጹሕ ነኝ፥ አል​በ​ደ​ል​ሁ​ምና፤ እኔ ጻድቅ ነኝ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም አል​ሠ​ራ​ሁም።


የሽ​ን​ገ​ላን ከን​ፈ​ሮች ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፥ ታላቅ ነገ​ርን የም​ት​ና​ገ​ረ​ው​ንም ምላስ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኬ የሚ​ና​ገ​ረ​ኝን አደ​ም​ጣ​ለሁ፤ ሰላ​ምን ለሕ​ዝ​ቡና ለጻ​ድ​ቃኑ፥ ልባ​ቸ​ው​ንም ወደ እርሱ ለሚ​መ​ልሱ ይና​ገ​ራ​ልና።


ኃጥእ እንደ ዐውሎ ነፋስ ኅልፈት ይጠፋል፤ ጻድቅ ግን ተሰውሮ ለዘለዓለም ይድናል።


ጻድቃን ለዘለዓለም አይናወጡም፤ ኃጥኣን ግን በምድር ላይ አይቀመጡም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios