እናንተ በእኔ ላይ ክፉ መከራችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲመገብ ለማድረግ ለእኔ መልካም መከረ።
ሐዋርያት ሥራ 27:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ፊስጦስ ወደ ቄሣር ወደ ኢጣልያ በመርከብ እንሄድ ዘንድ ባዘዘ ጊዜ ጳውሎስ ከሌሎች እስረኞች ጋር አብሮ የአውግስጦስ ጭፍራ ለነበረ ዩልዮስ ለሚባል የመቶ አለቃ ተሰጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ኢጣሊያ እንድንሄድ በተወሰነ ጊዜ፣ ጳውሎስንና ሌሎቹን እስረኞች የንጉሠ ነገሥቱ ክፍለ ጦር አባል ለሆነው፣ ዩልዮስ ለተባለ የመቶ አለቃ አስረከቧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ኢጣሊያም በመርከብ እንሄድ ዘንድ በተቆረጠ ጊዜ፥ ጳውሎስንና ሌሎችን እስረኞች ከአውግስጦስ ጭፍራ ለነበረ ዩልዮስ ለሚሉት ለመቶ አለቃ አሳልፈው ሰጡአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ኢጣሊያ በመርከብ እንድንሄድ በተወሰነ ጊዜ ጳውሎስንና ሌሎችንም እስረኞች በአውግስጦስ ክፍለ ጦር ውስጥ ለነበረው ዩልዮስ ለሚባለው መቶ አለቃ አስረከቡአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ኢጣሊያም በመርከብ እንሄድ ዘንድ በተቈረጠ ጊዜ፥ ጳውሎስንና ሌሎችን እስረኞች ከአውግስጦስ ጭፍራ ለነበረ ዩልዮስ ለሚሉት ለመቶ አለቃ አሳልፈው ሰጡአቸው። |
እናንተ በእኔ ላይ ክፉ መከራችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲመገብ ለማድረግ ለእኔ መልካም መከረ።
የመቶ አለቃም ከእርሱም ጋር ኢየሱስን የሚጠብቁ መናወጡንና የሆነውን ነገር አይተው “ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ፤” ብለው እጅግ ፈሩ።
እነርሱም፥ “የመቶ አለቃ ቆርኔሌዎስ እግዚአብሔርን የሚፈራ ጻድቅ ሰው ነው፤ በአይሁድም ወገኖች ሁሉ የተመሰከረለት ነው፤ ቅዱስ መልአክ ተገልጦ አንተን ወደ ቤቱ እንዲጠራህ የምታስተምረውንም እንዲሰማ አዝዞታል፤” አሉት።
ራእዩንም ባየ ጊዜ ወዲያውኑ ወደ መቄዶንያ ልንሄድ ወደድን፤ ወንጌልን እንሰብክላቸው ዘንድ እግዚአብሔር የሚጠራን መስሎናልና።
አቂላ የሚባል አንድ አይሁዳዊም አገኘ፤ የትውልድ ሀገሩም ጳንጦስ ነው፤ እርሱም ከጥቂት ወራት በፊት ከኢጣልያ ተሰዶ መጣ፤ ሚስቱ ጵርስቅላም አብራው ነበረች፤ ቀላውዴዎስ አይሁድ ከሮም እንዲሰደዱ አዝዞ ነበርና ወደ እነርሱ መጣ።
ይህም ከተፈጸመ በኋላ ጳውሎስ በመቄዶንያና በአካይያ በኩል አልፎ ወደ ኢየሩሳሌም ሊሄድ በልቡ ዐሰበ፥ “እዚያም ከደረስሁ በኋላ ሮሜን ላያት ይገባኛል” አለ።
በዚያ ጊዜም ጭፍሮቹን ከአለቆቻቸው ጋር ይዞ ወደ እነርሱ ሄደ፤ እነርሱም የሻለቃውን ጭፍሮች ባዩ ጊዜ ጳውሎስን መምታታቸውን ተዉ።
በሁለተኛዪቱም ሌሊት ጌታችን ለጳውሎስ ተገልጦ፥ “ጽና፥ በኢየሩሳሌም ምስክር እንደ ሆንኸኝ እንዲሁ በሮም ምስክር ትሆነኛለህ” አለው።
የመቶ አለቃውንም ጳውሎስን እንዲጠብቀው፥ በሰፊ ቦታም እንዲያኖረው፥ እንዳያጠብበትም፥ ሊያገለግሉት በመጡ ጊዜም ከወዳጆቹ አንዱን ስንኳ እንዳይከለክልበት አዘዘ።
እኔ ግን ለሞት የሚያደርሰው በደል እንዳልሠራ እጅግ መርምሬ፥ እርሱም ራሱ ወደ ቄሣር ይግባኝ ማለትን ስለወደደ እንግዲህ ልልከው ቈርጫለሁ።
የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስን ሊያድነው ወድዶአልና ምክራቸውን እንቢ አለ፤ ዋና የሚያውቁትንም ዋኝተው ወደ ምድር እንዲወጡ አዘዛቸው።
ወደ ሮሜም በገባን ጊዜ የመቶ አለቃው እስረኞችን ለሠራዊቱ አለቃ አስረከበ፤ ጳውሎስ ግን ከሚጠብቀው አንድ ወታደር ጋር ለብቻው ይቀመጥ ዘንድ ፈቀደለት።