Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ሐዋርያት ሥራ 19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ጳው​ሎስ ወደ ኤፌ​ሶን ስለ መም​ጣቱ

1 ከዚ​ህም በኋላ አጵ​ሎስ በቆ​ሮ​ን​ቶስ ሳለ፥ ጳው​ሎስ ላይ ላዩን ሄዶ ወደ ኤፌ​ሶን መጣ፤ በዚ​ያም ጥቂት ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትን አገኘ።

2 “ካመ​ና​ችሁ ጀምሮ በውኑ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተቀ​ብ​ላ​ች​ኋ​ልን?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “አል​ተ​ቀ​በ​ል​ንም መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዳለ ስንኳ አል​ሰ​ማ​ንም” አሉት።

3 እር​ሱም፥ “እን​ኪያ በምን ተጠ​መ​ቃ​ችሁ?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “በዮ​ሐ​ንስ ጥም​ቀት” አሉት።

4 ጳው​ሎ​ስም፥ “ዮሐ​ንስ ከእ​ርሱ በኋላ በሚ​መ​ጣው በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እን​ዲ​ያ​ምኑ እየ​ሰ​በከ የን​ስሓ ጥም​ቀ​ትን አጠ​መቀ” አላ​ቸው።

5 እነ​ር​ሱም ይህን በሰሙ ጊዜ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ተጠ​መቁ።

6 ጳው​ሎ​ስም እጁን በጫ​ነ​ባ​ቸው ጊዜ መን​ፈስ ቅዱስ በእ​ነ​ርሱ ላይ ወረደ፤ ያን​ጊ​ዜም በሀ​ገሩ ሁሉ ቋንቋ ተና​ገሩ፤ ትን​ቢ​ትም ተና​ገሩ።

7 ሰዎ​ቹም ሁሉ ዐሥራ ሁለት ያህሉ ነበር።

8 ጳው​ሎ​ስም ወደ ምኵ​ራብ ገብቶ በግ​ልጥ አስ​ተ​ማረ፤ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥት እያ​ስ​ተ​ማ​ራ​ቸ​ውና እያ​ሳ​መ​ና​ቸው ሦስት ወር ቈየ።

9 በተ​ሰ​በ​ሰ​በ​ውም ሕዝብ ፊት አን​ዳ​ን​ዶች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትም​ህ​ርት ላይ ክፉ እየ​ተ​ና​ገሩ ባላ​መኑ ጊዜ፥ ጳው​ሎስ ከእ​ነ​ርሱ ተለየ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱ​ንም ይዞ ጢራ​ኖስ በሚ​ባል መም​ህር ቤት ሁል​ጊዜ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ነበር።

10 በእ​ስ​ያም ያሉ አይ​ሁ​ድና አረ​ማ​ው​ያን ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እስ​ኪ​ሰሙ ድረስ እን​ደ​ዚሁ ሁለት ዓመት ኖረ።


ለጳ​ው​ሎስ ስለ ተሰ​ጠው ሀብተ ፈውስ

11 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጳ​ው​ሎስ እጅ ታላ​ላቅ ሥራን ይሠራ ነበር።

12 ከል​ብሱ ዘር​ፍና ከመ​ጠ​ም​ጠ​ሚ​ያዉ ጫፍ ቈር​ጠው እየ​ወ​ሰዱ በድ​ው​ያኑ ላይ ያኖ​ሩት ነበር፤ እነ​ር​ሱም ይፈ​ወሱ ነበር፤ ክፉ​ዎች መና​ፍ​ስ​ትም ይወጡ ነበር።

13 ከአ​ይ​ሁ​ድም አስ​ማት እያ​ደ​ረጉ የሚ​ዞሩ ሰዎች ክፉ​ዎች መና​ፍ​ስት ባሉ​ባ​ቸው ላይ “ጳው​ሎስ በሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ር​በት በኢ​የ​ሱስ ስም እና​ም​ላ​ች​ኋ​ለን” እያሉ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ስም ይጠ​ሩ​ባ​ቸው ነበር።

14 እኒህ እን​ዲህ ያደ​ርጉ የነ​በ​ሩ​ትም የካ​ህ​ናቱ አለቃ የአ​ይ​ሁ​ዳ​ዊው የአ​ስ​ቂዋ ልጆች ናቸው፤ እነ​ር​ሱም ሰባት ነበሩ።

15 ያም ክፉ መን​ፈስ፥ “በኢ​የ​ሱስ አም​ና​ለሁ፥ ጳው​ሎ​ስ​ንም አው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲህ እና​ንተ እነ​ማን ናችሁ?” ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው።

16 ያም ክፉ መን​ፈስ የያ​ዘው ሰው ተነ​ሣ​ባ​ቸው፤ አየ​ለ​ባ​ቸ​ውም፤ አሸ​ነ​ፋ​ቸ​ውም፤ አቍ​ስ​ሎም ከዚያ ቤት አስ​ወ​ጥቶ አባ​ረ​ራ​ቸው።

17 ይህም ነገር በኤ​ፌ​ሶን በሚ​ኖሩ በአ​ይ​ሁ​ድና በአ​ረ​ማ​ው​ያን ሁሉ ዘንድ ተሰማ፤ ሁሉም ፈሩ፤ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስ​ንም ስም ከፍ ከፍ አደ​ረጉ።

18 ያመ​ኑ​ትም ሁሉ እየ​መጡ ስለ ሠሩት ንስሓ ይገቡ ነበር።

19 ብዙ​ዎች አስ​ማ​ተ​ኞ​ችም መጽ​ሐ​ፎ​ቻ​ቸ​ውን እየ​ሰ​በ​ሰቡ እያ​መጡ በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት በእ​ሳት ያቃ​ጥሉ ነበር፤ ያቃ​ጠ​ሏ​ቸው የመ​ጽ​ሐ​ፎች ዋጋም አምሳ ሺህ ብር ነበር።

20 እን​ዲ​ህም እያለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በኀ​ይል ያድ​ግና ይበ​ረታ ነበር።

21 ይህም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ ጳው​ሎስ በመ​ቄ​ዶ​ን​ያና በአ​ካ​ይያ በኩል አልፎ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሊሄድ በልቡ ዐሰበ፥ “እዚ​ያም ከደ​ረ​ስሁ በኋላ ሮሜን ላያት ይገ​ባ​ኛል” አለ።

22 ከሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​ትም ሁለ​ቱን ጢሞ​ቴ​ዎ​ስ​ንና አር​ስ​ጦ​ስን ወደ መቄ​ዶ​ንያ ላከ፤ እርሱ ራሱ ጳው​ሎስ ግን ብዙ ቀን በእ​ስያ ተቀ​መጠ።


በኤ​ፌ​ሶን ስለ ተደ​ረ​ገው ሁከት

23 በዚ​ያም ወራት ስለ​ዚህ ትም​ህ​ርት ብዙ ሁከት ሆነ።

24 በዚ​ያም ብር ሠሪ የሆነ ድሜ​ጥ​ሮስ የሚ​ባል አንድ ሰው ነበር፤ ለአ​ር​ጤ​ም​ስም ከብር የቤተ መቅ​ደስ ምስል ይሠራ ነበር፤ አን​ጥ​ረ​ኞ​ች​ንም እያ​ሠራ ብዙ ገን​ዘብ ይሰ​ጣ​ቸው ነበር።

25 አን​ጥ​ረ​ኞ​ች​ንና ይህን የመ​ሰ​ለ​ውን ሥራ የሚ​ሠ​ሩ​ት​ንም ሁሉ ሰብ​ስቦ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰዎች ሆይ፥ ጥቅም የም​ና​ገ​ኘው በዚህ ሥራ​ችን እንደ ሆነ እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።

26 አሁን ግን እን​ደ​ም​ታ​ዩ​ትና እን​ደ​ም​ት​ሰ​ሙት ይህ ጳው​ሎስ ኤፌ​ሶ​ንን ብቻ ሳይ​ሆን መላ​ውን እስ​ያን አሳተ፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንም መለሰ፤ በሰው እጅ የሚ​ሠ​ሩ​ት​ንም ሁሉ አማ​ል​ክት አይ​ደ​ሉም አላ​ቸው።

27 አሁን የም​ን​ቸ​ገር በዚህ ነገር ብቻ አይ​ደ​ለም፤ እስ​ያና መላው ዓለም የሚ​ያ​መ​ል​ካት የታ​ላቋ የአ​ር​ጤ​ም​ስም መቅ​ደስ ክብር ይቀ​ራል፤ ገና​ና​ነ​ቷም ይሻ​ራል።”

28 ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ ተቈ​ጡና ድም​ፃ​ቸ​ውን ከፍ አድ​ር​ገው፥ “የኤ​ፌ​ሶን አር​ጤ​ምስ ክብ​ርዋ ታላቅ ነው” አሉ።

29 ከተ​ማ​ውም ሁሉ ታወከ፤ የመ​ቄ​ዶ​ን​ያን ሰዎች የጳ​ው​ሎ​ስን ወዳ​ጆች ጋይ​ዮ​ስ​ንና አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮ​ስ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ጋር እየ​ጐ​ተ​ቱ​በ​አ​ን​ድ​ነት ወደ ጨዋ​ታው ቦታ ሮጡ።

30 ጳው​ሎ​ስም ወደ አሕ​ዛብ መካ​ከል ሊገባ ወድዶ ነበር፤ ነገር ግን ደቀ መዛ​ሙ​ርት ከለ​ከ​ሉት።

31 ከእ​ስ​ያም የሆኑ ታላ​ላ​ቆች ወዳ​ጆቹ ወደ ጨዋ​ታው ቦታ እን​ዳ​ይ​ገባ ልከው ማለ​ዱት።

32 በዚ​ያም በጨ​ዋ​ታው ቦታ የነ​በሩ ሰዎች እየ​ጮኹ ቈዩ፤ በሌ​ላም ቋንቋ የሚ​ጮሁ ነበሩ፤ በጉ​ባ​ኤው ታላቅ ድብ​ል​ቅ​ልቅ ሆኖ ነበ​ርና፤ ከእ​ነ​ርሱ የሚ​በ​ዙት ግን በምን ምክ​ን​ያት እንደ ተሰ​በ​ሰቡ አያ​ው​ቁም ነበር።

33 በዚያ የነ​በሩ አይ​ሁ​ድም እስ​ክ​ን​ድ​ሮስ የሚ​ባል አይ​ሁ​ዳዊ ሰውን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አስ​ነሡ፤ እር​ሱም ተነ​ሥቶ በእጁ ምል​ክት ሰጠና ለሕ​ዝቡ ሊከ​ራ​ከ​ር​ላ​ቸው ወደደ።

34 አይ​ሁ​ዳዊ እን​ደ​ሆ​ነም ባወቁ ጊዜ “የኤ​ፌ​ሶን አር​ጤ​ምስ ክብ​ርዋ ታላቅ ነው” እያሉ ሁለት ሰዓት ያህል ሁሉም በአ​ንድ ድምፅ ጮሁ።

35 ከዚ​ህም በኋላ የከ​ተ​ማው ጸሓፊ ተነ​ሥቶ ሕዝ​ቡን ጸጥ አሰ​ኝቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የኤ​ፌ​ሶን ሰዎች ሆይ፥ ስሙ፤ የኤ​ፌ​ሶን ከተማ ታላ​ቂ​ቱን አር​ጤ​ም​ስ​ንና ከሰ​ማይ የወ​ረ​ደ​ውን ጣዖ​ት​ዋን እን​ደ​ም​ት​ጠ​ብቅ የማ​ያ​ውቅ ማነው?

36 ስለ​ዚ​ህም እር​ስ​ዋን መቃ​ወም የሚ​ቻ​ለው ያለ አይ​መ​ስ​ለ​ኝም፤ አሁ​ንም ይህን በጠ​ብና በክ​ር​ክር ሳይ​ሆን በቀ​ስታ ልና​ደ​ር​ገው ይገ​ባ​ናል።

37 የአ​ማ​ል​ክ​ትን ቤት ያል​ዘ​ረ​ፉ​ት​ንና በአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ችን ላይ ክፉ ቃልን ያል​ተ​ና​ገ​ሩ​ትን እነ​ዚ​ህን ሰዎች እነሆ ወደ እዚህ አም​ጥ​ታ​ች​ኋ​ቸ​ዋል።

38 ድሜ​ጥ​ሮ​ስና ከእ​ርሱ ጋር ያሉ አን​ጥ​ረ​ኞች ግን በማ​ንም ላይ ጠብ እን​ዳ​ላ​ቸው እርስ በር​ሳ​ቸው ይከ​ራ​ከሩ፤ እነ​ሆም በከ​ተ​ማው ውስጥ ፍርድ ቤት አለ፤ ዳኞ​ችም አሉ።

39 ነገር ግን ይህ የም​ት​ከ​ራ​ከ​ሩ​በት ነገር ሌላ ከሆነ በሕግ ሸንጎ ይፈ​ታል።

40 ዛሬም በደል ሳይ​ኖር በአ​መ​ጣ​ች​ሁ​ብን ክር​ክር እኛ እን​ቸ​ገ​ራ​ለ​ንና ስለ​ዚህ ክር​ክር የም​ን​ወ​ቃ​ቀ​ሰው ነገር የለም፥” ይህ​ንም ብሎ ሸን​ጎ​ውን ፈታ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos