Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 19:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ ተቈ​ጡና ድም​ፃ​ቸ​ውን ከፍ አድ​ር​ገው፥ “የኤ​ፌ​ሶን አር​ጤ​ምስ ክብ​ርዋ ታላቅ ነው” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ሰዎቹም ይህን በሰሙ ጊዜ ክፉኛ ተቈጥተው፣ “የኤፌሶኗ አርጤምስ ታላቅ ናት!” እያሉ ይጮኹ ጀመር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ይህንም በሰሙ ጊዜ ቁጣ ሞላባቸው “የኤፌሶን አርጤምስ ታላቅ ናት!” እያሉም ጮኹ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ሰዎቹም ይህን በሰሙ ጊዜ ተቈጥተው፥ “የኤፌሶን አርጤሚስ ታላቅ ናት!” እያሉ ጮኹ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ይህንም በሰሙ ጊዜ ቍጣ ሞላባቸው፦ የኤፌሶን አርጤምስ ታላቅ ናት እያሉም ጮኹ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 19:28
15 Referencias Cruzadas  

የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ተነሡ፥ አለ​ቆ​ችም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በመ​ሲሑ ላይ እን​ዲህ ሲሉ በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​በ​ሰቡ።


እር​ስዋ የተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎች ምድር ናትና፥ እነ​ር​ሱም በደ​ሴ​ቶ​ችዋ ይመ​ካ​ሉና ሰይፍ በው​ኆ​ችዋ ላይ አለ፤ እነ​ር​ሱም ይደ​ር​ቃሉ።


ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።


ወደ ኤፌ​ሶ​ንም ደረሱ፤ በዚ​ያም ተዋ​ቸ​ውና እርሱ ብቻ​ውን ወደ ምኵ​ራብ ገብቶ አይ​ሁ​ድን ተከ​ራ​ከ​ራ​ቸው።


በዚ​ያም ብር ሠሪ የሆነ ድሜ​ጥ​ሮስ የሚ​ባል አንድ ሰው ነበር፤ ለአ​ር​ጤ​ም​ስም ከብር የቤተ መቅ​ደስ ምስል ይሠራ ነበር፤ አን​ጥ​ረ​ኞ​ች​ንም እያ​ሠራ ብዙ ገን​ዘብ ይሰ​ጣ​ቸው ነበር።


ይህ​ንም ሰም​ተው ተበ​ሳጩ፤ ልባ​ቸ​ውም ተና​ደደ፤ ጥር​ሳ​ቸ​ው​ንም አፋ​ጩ​በት።


ስለዚህ ሰማይና በውስጡ የምታድሩ ሆይ! ደስይበላችሁ፤ ለምድርና ለባሕር ወዮላቸው፤ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና።”


ለዘንዶውም ሰገዱለት፤ ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና፤ ለአውሬውም “አውሬውን ማን ይመስለዋል? እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል?” እያሉ ሰገዱለት።


እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፤ ኀይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos