Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 18:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አቂላ የሚ​ባል አንድ አይ​ሁ​ዳ​ዊም አገኘ፤ የት​ው​ልድ ሀገ​ሩም ጳን​ጦስ ነው፤ እር​ሱም ከጥ​ቂት ወራት በፊት ከኢ​ጣ​ልያ ተሰዶ መጣ፤ ሚስቱ ጵር​ስ​ቅ​ላም አብ​ራው ነበ​ረች፤ ቀላ​ው​ዴ​ዎስ አይ​ሁድ ከሮም እን​ዲ​ሰ​ደዱ አዝዞ ነበ​ርና ወደ እነ​ርሱ መጣ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በዚያም የጳንጦስ ተወላጅ የሆነውን፣ አቂላ የተባለውን አይሁዳዊ አገኘ፤ እርሱም አይሁድ ሁሉ ከሮም እንዲወጡ ቀላውዴዎስ ባዘዘው መሠረት፣ ከሚስቱ ከጵርስቅላ ጋራ በቅርብ ጊዜ ከኢጣሊያ የመጣ ነበር። ጳውሎስም ሊያያቸው ወደ እነርሱ ሄደ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በወገኑም የጳንጦስ ሰው የሚሆን አቂላ የሚሉትን አንድ አይሁዳዊ አገኘ፤ እርሱም ከጥቂት ጊዜ በፊት ከሚስቱ ከጵርስቅላ ጋር ከኢጣልያ መጥቶ ነበር፤ አይሁድ ከሮሜ ይወጡ ዘንድ ቀላውዴዎስ አዞ ነበርና፤ ወደ እነርሱ ቀረበ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እዚያ የጳንጦስ ተወላጅ የሆነውን አቂላ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ሰው አገኘ፤ የሮም ንጉሠ ነገሥት ቀላውዴዎስ አይሁድ ሁሉ ከሮም እንዲወጡ አዞ ስለ ነበረ አቂላ ከሚስቱ ከጵርስቅላ ጋር ከኢጣልያ ገና መምጣቱ ነበር፤ ስለዚህ ጳውሎስ ወደ እነርሱ ሄዶ ተዋወቃቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በወገኑም የጳንጦስ ሰው የሚሆን አቂላ የሚሉትን አንድ አይሁዳዊ አገኘ፤ እርሱም ከጥቂት ጊዜ በፊት ከሚስቱ ከጵርስቅላ ጋር ከኢጣልያ መጥቶ ነበር፥ አይሁድ ከሮሜ ይወጡ ዘንድ ቀላውዴዎስ አዞ ነበርና፤ ወደ እነርሱ ቀረበ፥

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 18:2
11 Referencias Cruzadas  

ለጵርስቅላና ለአቂላ ለሄኔሲፎሩም ቤተ ሰዎች ሰላምታ አቅርብልኝ።


በእ​ስያ ያሉ ምእ​መ​ናን ሰላ​ምታ ያቀ​ር​ቡ​ላ​ች​ኋል፤ አቂ​ላና ጵር​ስ​ቅላ በቤ​ታ​ቸው ከእ​ነ​ርሱ ጋር ያሉ ምእ​መ​ና​ንም ሁሉ በጌ​ታ​ችን እጅግ ሰላ​ምታ ያቀ​ር​ቡ​ላ​ች​ኋል።


እር​ሱም በም​ኵ​ራብ በግ​ልጥ ይና​ገር ጀመር፤ ጵር​ስ​ቅ​ላና አቂ​ላም በሰ​ሙት ጊዜ ወደ ማደ​ሪ​ያ​ቸው ወስ​ደው ፍጹም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ አስ​ረ​ዱት።


ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም አጋ​ቦስ የተ​ባለ አንድ ሰው ተነ​ሥቶ በዓ​ለም ሁሉ ጽኑ ረኃብ እን​ደ​ሚ​መጣ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ተገ​ል​ጦ​ለት ተና​ገረ፤ ይህም በቄ​ሣር ቀላ​ው​ዴ​ዎስ ዘመን ሆነ።


ጳው​ሎ​ስም እንደ ገና በወ​ን​ድ​ሞቹ ዘንድ ጥቂት ቀን ተቀ​መጠ፤ በሰ​ላ​ምም ሸኙ​ትና ወደ ሶርያ በባ​ሕር ተጓዘ፤ ጵር​ስ​ቅ​ላና አቂ​ላም አብ​ረ​ውት ነበሩ፤ ስእ​ለ​ትም ነበ​ረ​በ​ትና በክ​ን​ክ​ራ​ኦስ ራሱን ተላጨ።


እኛ በተ​ወ​ለ​ድ​ን​በት በጳ​ርቴ፥ በሜድ፥ በኢ​ላ​ሜጤ፥ በሁ​ለቱ ወን​ዞች መካ​ከል፥ በይ​ሁዳ፥ በቀ​ጰ​ዶ​ቅያ፥ በጳ​ን​ጦ​ስና በእ​ስያ፥


የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ጴጥሮስ፥ እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ እንዳወቃቸው በመንፈስም እንደሚቀደሱ፥ ይታዘዙና በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ይረጩ ዘንድ ለተመረጡት በጳንጦስና በገላትያ በቀጰዶቅያም በእስያም በቢታንያም ለተበተኑ መጻተኞች፤ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።


ከዚ​ህም በኋላ ፊስ​ጦስ ወደ ቄሣር ወደ ኢጣ​ልያ በመ​ር​ከብ እን​ሄድ ዘንድ ባዘዘ ጊዜ ጳው​ሎስ ከሌ​ሎች እስ​ረ​ኞች ጋር አብሮ የአ​ው​ግ​ስ​ጦስ ጭፍራ ለነ​በረ ዩል​ዮስ ለሚ​ባል የመቶ አለቃ ተሰጠ።


በዚ​ያም የመቶ አለ​ቃው ወደ ኢጣ​ልያ የም​ት​ሄድ የእ​ስ​ክ​ን​ድ​ር​ያን መር​ከብ አገኘ፤ ወደ እር​ስ​ዋም አስ​ገ​ባን።


መም​ህ​ሮ​ቻ​ች​ሁን ሁሉና ቅዱ​ሳ​ን​ንም ሁሉ ሰላም በሉ፥ በኢ​ጣ​ልያ ያሉ ሁሉ ሰላም ብለ​ዋ​ች​ኋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios