ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እሳትን ላከ፤ ያም እሳት መሥዋዕቱን፥ እንጨቱንና ድንጋዩን አቃጠለ፤ ምድሩንም ለበለበ፤ በጒድጓዱ የነበረውንም ውሃ አደረቀ፤
ዘሌዋውያን 10:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናዳብና አቢሁ የተባሉት ሁለቱ የአሮን ልጆች እያንዳንዳቸው ጥናቸውን ወስደው፥ የእሳት ፍም ጭረው ጨመሩበት፤ በእርሱም ላይ ዕጣን አድርገው ወደ እግዚአብሔር አቀረቡ፤ ያን ዐይነት እሳት ያቀርቡ ዘንድ እግዚአብሔር ስላላዘዛቸው፤ ያ እሳቱ የተቀደሰ አልነበረም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአሮን ልጆች ናዳብና አብዩድ እያንዳንዳቸው ጥናዎቻቸውን ወስደው ፍም አደረጉባቸው፤ ዕጣንም ጨመሩባቸው፤ እርሱ ያላዘዛቸውን፣ ያልተፈቀደውን እሳት በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአሮንም ልጆች ናዳብና አብዩድ እያንዳንዳቸው ጥናቸውን ወስደው እሳት አደረጉበት፥ በላዩም ዕጣን አኖሩበት፥ በጌታም ፊት እርሱ ያላዘዛቸውን ያልተፈቀደውን እሳት አቀረቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሮንም ልጆች ናዳብና አብዩድ በየራሳቸው ጥናውን ወስደው እሳት አደረጉበት፤ በላዩም ዕጣን ጨመሩበት፤ በእግዚአብሔርም ፊት እግዚአብሔር ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት አቀረቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሮንም ልጆች ናዳብና አብዩድ በየራሳቸው ጥናውን ወስደው እሳት አደረጉበት፥ በላዩም ዕጣን አኖሩበት፥ በእግዚአብሔርም ፊት እርሱ ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት አቀረቡ። |
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እሳትን ላከ፤ ያም እሳት መሥዋዕቱን፥ እንጨቱንና ድንጋዩን አቃጠለ፤ ምድሩንም ለበለበ፤ በጒድጓዱ የነበረውንም ውሃ አደረቀ፤
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አንተ ራስህ፥ አሮን፥ ናዳብ፥ አቢሁና ከእስራኤል መሪዎች ሰባ የሚሆኑት ጭምር እኔ ወዳለሁበት ተራራ ውጡ፤ በሩቅ ሳላችሁም ተንበርክካችሁ ስገዱ፤
ዐመድ የሚጠራቀምባቸውን ድስቶችን፥ የእሳት መጫሪያዎችን፥ ጐድጓዳ ሳሕኖችን፥ ሜንጦዎችንና ማንደጃዎችን አዘጋጅ፤ ሁሉም ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ።
“ወንድምህን አሮንንና ልጆቹን ናዳብን፥ አቢሁን፥ አልዓዛርንና ኢታማርን ወደ አንተ አቅርብ፤ ካህናት ሆነው ያገለግሉኝም ዘንድ ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ለያቸው።
የቅባቱ ዘይትና ለተቀደሰው ስፍራ የሚሆነው መዓዛው ጣፋጭ የሆነ ዕጣን፤ ልክ እኔ አንተን ባዘዝኩት ዐይነት እነዚህን ሁሉ ነገሮች ይሠራሉ።”
በመሠዊያው ላይ ያሉትንም የመገልገያ ዕቃዎች፥ ድስቶችንም፥ የእሳት መጫሪያዎቹንም፥ ጐድጓዳ ሳሕኖችንም፥ ሜንጦዎቹንም፥ ማንደጃዎቹንም ከነሐስ ሠራ፤
አሮን የነአሶን እኅት የሆነችውን የዓሚናዳብን ልጅ ኤሊሼባን አገባ፤ እርስዋም ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር የተባሉትን ወንዶች ልጆች ወለደችለት።
ልጆቻቸውንም መሥዋዕት አድርገው በእሳት ለማቃጠል ለባዓል መሠዊያዎችን ሠርተዋል፤ ይህን እንዲያደርጉ አላዘዝኳቸውም፤ ከቶም ስለዚህ ነገር አላሰብኩም።
ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ሞሌክ ለተባለው ጣዖት መሥዋዕት አድርገው ለማቅረብ በሄኖም ሸለቆ ውስጥ ለበዓል ጣዖት መሠዊያ ሠርተዋል፤ እኔ ይህን እንዲያደርጉ አላዘዝኳቸውም የይሁዳንም ሕዝብ ወደ ኃጢአት ለመምራት ይህን ያደርጋሉ ብዬ አልጠበቅሁም ነበር።”
ሚስቶቻቸው ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት የሚያቀርቡ መሆናቸውን የሚያውቁ ወንዶች ሁሉ፥ በግብጽ ደቡባዊ ክፍል የሚኖሩት እስራኤላውያንና በዚያ ቆመው የነበሩት ሴቶች ሁሉ በአንድነት ተሰብስበው በመቅረብ እንዲህ አሉኝ፦
መጥታችሁ በምትኖሩባት በዚህችስ በግብጽ ምድር ለጣዖቶች በመስገድና ለባዕዳን አማልክት መሥዋዕት በማቅረብ ስለምን ታስቈጡኛላችሁ? ወይስ በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ እንዲዘባበቱባችሁና ስማችሁንም መራገሚያ ያደርጉት ዘንድ ራሳችሁን በራሳችሁ ማጥፋት ትፈልጋላችሁን?
ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት እያቃጠሉ መሥዋዕት አድርገው ለማቅረብ በሂኖም ሸለቆ ውስጥ ‘ቶፌት’ ተብሎ የሚጠራ መሠዊያ ሠርተዋል፤ ይህም እኔ ያላዘዝኳቸውና በፍጹምም ያላሰብኩት ነገር ነው።
ከመሠዊያው የሚቃጠል የእሳት ፍም በጥናው ሞልቶም ሁለት እፍኝ ጣፋጭ ሽታ ያለውን የተወቀጠ ደቃቅ ዕጣን በመውሰድ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ያግባ፤
“ካህናት ሁሉ እኔ የሰጠኋቸውን የሥርዓት መመሪያዎች ይጠብቁ፤ ይህን ባያደርጉ ግን ለተቀደሱት የትእዛዝ መመሪያዎች ባለመታዘዛቸው በደል ሆኖባቸው ይሞታሉ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
እሳትም በድንገት ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ፥ በመሠዊያው ላይ የነበረውን መሥዋዕትና ስብ ሁሉ በላ፤ ሕዝቡ ሁሉ ይህን ባዩ ጊዜ እልል አሉ፤ በምድር ላይም በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱ።
ሙሴም አሮንን እንዲህ አለው፦ “የአንተን ጥና ወስደህ ከመሠዊያው የእሳት ፍም ጨምርበት፤ በፍሙም ላይ ዕጣን አድርግበት፤ ከዚያም ወደ ሕዝቡ በፍጥነት በመሄድ አስተስርይላቸው፤ ፍጠን! እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቊጣ ከመገለጡ የተነሣ በሕዝቡ መካከል መቅሠፍት ጀምሮአል።”
በምሰጣችሁ ሕግ ላይ ምንም ነገር አትጨምሩ፤ ወይም ከእርሱ ምንም ነገር አታጒድሉ፤ ነገር ግን እኔ ለምሰጣችሁ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ትእዛዞች ታዛዦች ሁኑ።
በዚህችኛዋ ክፍል ውስጥ የወርቅ ማዕጠንትና በወርቅ የተለበጠች የኪዳን ታቦት ነበሩባት፤ ከዚህችም የኪዳን ታቦት ውስጥ መና ያለባት የወርቅ መሶብ፥ ለምልማ የነበረችው የአሮን በትር፥ ዐሥሩ ትእዛዞች የተጻፉባት ጽላት ነበሩ።