Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 6:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 አሮን የነአሶን እኅት የሆነችውን የዓሚናዳብን ልጅ ኤሊሼባን አገባ፤ እርስዋም ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር የተባሉትን ወንዶች ልጆች ወለደችለት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 አሮንም የአሚናዳብን ልጅ፣ የነአሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ፤ እርሷም ናዳብንና አብዩድን፣ አልዓዛርንና ኢታምርን ወለደችለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 አሮንም የዓሚናዳብን ልጅ የናሕሾንን እኅት ኤሊሼባን አገባ፥ እርሷም ናዳብ፥ አቢሁ፥ ኤልዓዛርንና ኢታማርን ወለደችለት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 አሮ​ንም የአ​ሚ​ና​ዳ​ብን ልጅ የነ​አ​ሶ​ንን እኅት ኤል​ሳ​ቤ​ጥን አገባ። እር​ስ​ዋም ናዳ​ብ​ንና አብ​ዩ​ድን፥ አል​ዓ​ዛ​ር​ንና ኢታ​ም​ርን ወለ​ደ​ች​ለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 አሮንም የአሚናዳብን የነአሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ፤ እርስዋም ዮናዳብንና አብድን አልዓዛርንና ኢታምርን ወለደችለት።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 6:23
19 Referencias Cruzadas  

አራም የአሚናዳብ አባት ነበር፤ አሚናዳብም የይሁዳ ልጆች አለቃ የሆነው ነአሶንን ወለደ።


ዓምራምም አሮንና ሙሴ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችና ማርያም ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት ልጅ ወለደ። አሮንም ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር ተብለው የሚጠሩ ወንዶች ልጆች ነበሩት።


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አንተ ራስህ፥ አሮን፥ ናዳብ፥ አቢሁና ከእስራኤል መሪዎች ሰባ የሚሆኑት ጭምር እኔ ወዳለሁበት ተራራ ውጡ፤ በሩቅ ሳላችሁም ተንበርክካችሁ ስገዱ፤


ሙሴ፥ አሮን፥ ናዳብ፥ አቢሁና ከእስራኤልም መሪዎች ሰባዎቹ ወደ ተራራው ወጡ፤


“ወንድምህን አሮንንና ልጆቹን ናዳብን፥ አቢሁን፥ አልዓዛርንና ኢታማርን ወደ አንተ አቅርብ፤ ካህናት ሆነው ያገለግሉኝም ዘንድ ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ለያቸው።


ሙሴም አሮንንና ከሞት የተረፉትን ሁለቱን ልጆቹን አልዓዛርንና ኢታማርን እንዲህ አላቸው፦ “ለእግዚአብሔር ከቀረበው የምግብ መባ የተረፈውን ወስዳችሁ እርሾ ያልነካው ቂጣ ጋግሩ፤ እርሱም እጅግ የተቀደሰ መባ ስለ ሆነ በመሠዊያው አጠገብ ብሉት።


ከዚህ በኋላ ሙሴ አሮንን፥ እንዲሁም አልዓዛርና ኢታማር የተባሉትን ሁለቱን የአሮንን ልጆች እንዲህ አላቸው፤ “ለሐዘን ብላችሁ ጠጒራችሁን አትላጩ፤ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፤ ይህን ብታደርጉ ግን ትሞታላችሁ፤ እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ቊጣውን ያወርዳል፤ ነገር ግን ወንድሞቻችሁ እስራኤላውያን ከእግዚአብሔር በተላከ እሳት ስለሞቱት ልጆች እንዲያለቅሱ ተፈቅዶላቸዋል።


ከይሁዳ የዓሚናዳብ ልጅ ነአሶን


ፀሐይ በሚወጣበት በስተምሥራቅ በኩል የሚሰፍሩት በይሁዳ ሥር የተመደቡት ነገዶች ናቸው። የይሁዳ ነገድ መሪም የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነው።


አሮንንና ልጁን አልዓዛርን ይዘህ ወደ ሖር ተራራ ውጣ።


ሙሴም የአሮንን የክህነት ልብስ አውልቆ አልዓዛርን አለበሰው፤ እዚያም በተራራው ጫፍ ላይ አሮን ሞተ፤ ሙሴና አልዓዛርም ተመልሰው ከተራራው ወረዱ፤


አራም ዓሚናዳብን ወለደ፤ ዓሚናዳብ ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤


ሄሮድስ በይሁዳ ምድር ንጉሥ በነበረበት ዘመን፥ ከአብያ የክህነት አገልግሎት ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል ካህን ነበር። እርሱም ከአሮን ዘር የምትወለድ ኤልሳቤጥ የምትባል ሚስት ነበረችው።


የአሮን ልጅ አልዓዛርም ሞተ፤ በጊብዓም ተቀበረ፤ እርስዋም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር የምትገኝና ለልጁ ለፊንሐስ መኖሪያ የተሰጠች ትንሽ ከተማ ናት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos