Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 6:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 አሮ​ንም የአ​ሚ​ና​ዳ​ብን ልጅ የነ​አ​ሶ​ንን እኅት ኤል​ሳ​ቤ​ጥን አገባ። እር​ስ​ዋም ናዳ​ብ​ንና አብ​ዩ​ድን፥ አል​ዓ​ዛ​ር​ንና ኢታ​ም​ርን ወለ​ደ​ች​ለት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 አሮንም የአሚናዳብን ልጅ፣ የነአሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ፤ እርሷም ናዳብንና አብዩድን፣ አልዓዛርንና ኢታምርን ወለደችለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 አሮንም የዓሚናዳብን ልጅ የናሕሾንን እኅት ኤሊሼባን አገባ፥ እርሷም ናዳብ፥ አቢሁ፥ ኤልዓዛርንና ኢታማርን ወለደችለት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 አሮን የነአሶን እኅት የሆነችውን የዓሚናዳብን ልጅ ኤሊሼባን አገባ፤ እርስዋም ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር የተባሉትን ወንዶች ልጆች ወለደችለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 አሮንም የአሚናዳብን የነአሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ፤ እርስዋም ዮናዳብንና አብድን አልዓዛርንና ኢታምርን ወለደችለት።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 6:23
19 Referencias Cruzadas  

በመ​ጀ​መ​ሪያ በም​ሥ​ራቅ በኩል የሚ​ሰ​ፍ​ሩት ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር የይ​ሁዳ ሰፈር ሰዎች ይሆ​ናሉ፤ የይ​ሁዳ ልጆ​ችም አለቃ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነአ​ሶን ነበረ።


የእ​ን​በ​ረ​ምም ልጆች፤ አሮን፥ ሙሴ፥ ማር​ያም። የአ​ሮ​ንም ልጆች፤ ናዳብ፥ አብ​ዩድ፥ አል​ዓ​ዛር፥ ኢታ​ምር።


አራ​ምም አሚ​ና​ዳ​ብን ወለደ፤ አሚ​ና​ዳ​ብም የይ​ሁ​ዳን ልጆች አለቃ ነአ​ሶ​ንን ወለደ፤


ከይ​ሁዳ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነአ​ሶን፥


ኤስሮምም አራምን ወለደ፤ አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤


አሮ​ን​ንና ልጁን አል​ዓ​ዛ​ርን ይዘህ በማ​ኅ​በሩ ሁሉ ፊት ወደ ሖር ተራራ ላይ አም​ጣ​ቸው፤


ሙሴም፥ አሮ​ንም፥ ናዳ​ብም፥ አብ​ዩ​ድም፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰባ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወጡ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “አንተ፥ አሮ​ንም፥ ናዳ​ብም፥ አብ​ዩ​ድም፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰባ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ውጡ፤ በሩ​ቁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስገዱ፤


በይ​ሁዳ ንጉሥ በሄ​ሮ​ድስ ዘመን ከአ​ብያ ክፍል የሆነ ዘካ​ር​ያስ የሚ​ባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስ​ቱም ከአ​ሮን ልጆች ወገን ነበ​ረች፤ ስም​ዋም ኤል​ሳ​ቤጥ ነበረ።


ሙሴም አሮ​ንን፥ የተ​ረ​ፉ​ለ​ትን ልጆ​ቹን አል​ዓ​ዛ​ር​ንና ኢታ​ም​ርን አላ​ቸው፥ “ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነውና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆ​ነው ከእ​ሳት ቍር​ባን የቀ​ረ​ውን የስ​ን​ዴ​ውን ቍር​ባን ውሰዱ፤ ቂጣም አድ​ር​ጋ​ችሁ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ብሉት፤


“አን​ተም ወን​ድ​ም​ህን አሮ​ንን ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆ​ቹን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለይ​ተህ በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ወደ አንተ አቅ​ርብ፤ አሮ​ንን የአ​ሮ​ን​ንም ልጆች፥ ናዳ​ብን፥ አብ​ዩ​ድ​ንም፥ አል​ዓ​ዛ​ር​ንም ኢታ​ም​ር​ንም አቅ​ርብ።


ሙሴም አሮ​ንን፥ ልጆ​ቹ​ንም አል​ዓ​ዛ​ር​ንና ኢታ​ም​ርን፥ “እን​ዳ​ት​ሞቱ፥ በማ​ኅ​በ​ሩም ላይ ሁሉ ቍጣ እን​ዳ​ይ​ወ​ርድ ራሳ​ች​ሁን አት​ንጩ፤ ልብ​ሳ​ች​ሁ​ንም አት​ቅ​ደዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስላ​ቃ​ጠ​ላ​ቸው ማቃ​ጠል ግን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ያል​ቅሱ።


ሙሴም የአ​ሮ​ንን ልብስ አወጣ፤ ልጁ​ንም አል​ዓ​ዛ​ርን አለ​በ​ሰው፤ አሮ​ንም በዚያ በተ​ራ​ራው ራስ ላይ ሞተ፤ ሙሴና አል​ዓ​ዛ​ርም ከተ​ራ​ራው ራስ ላይ ወረዱ።


የአ​ሮ​ንም ልጅ ሊቀ ካህ​ናቱ አል​ዓ​ዛር ሞተ፤ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ለልጁ ለፊ​ን​ሐስ በተ​ሰ​ጠ​ችው በጊ​ብ​ዓት መሬት ቀበ​ሩት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios