ኤርምያስ 14:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ይሁዳ በሐዘን ላይ ነች፤ ከተሞችዋም በሞት ጣዕር ላይ ናቸው፤ ሕዝብዋም በሐዘን ምክንያት በመሬት ላይ ተቀምጠው ያለቅሳሉ፤ ኢየሩሳሌም ወደ እግዚአብሔር ትጮኻለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይሁዳ ታለቅሳለች፤ ከተሞቿም ይማቅቃሉ፤ በምድር ላይ ተቀምጠው ይቈዝማሉ፤ ጩኸትም ከኢየሩሳሌም ወጥቶ ይሰማል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ይሁዳ አለቀሰች፥ ደጆችዋም ባዶ ሆኑ፤ ስለ ምድሪቱም አለቀሱ፤ የኢየሩሳሌም ጩኸት ከፍ ከፍ ብሏል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይሁዳ አለቀሰች፤ ደጆችዋም ባዶ ሆኑ፤ በምድርም ላይ ጨለሙ፤ የኢየሩሳሌምም ጩኸት ከፍ ከፍ ብሎአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሁዳ አለቀሰች፥ ደጆችዋም ባዶ ሆኑ በምድርም ላይ ጨለሙ፥ የኢየሩሳሌም ጩኸት ከፍ ከፍ ብሎአል። |
ስለ ሞአብ ከልቤ አለቅሳለሁ፤ ሕዝቡ ወደ ጾዓርና ወደ ዔግላት ሸሊሺያ ኰበለሉ፤ ጥቂቶችም ወደ ሉሒት አቀበት ወጡ፤ በሚወጡበትም ጊዜ ያለቅሱ ነበር፤ ሌሎች ደግሞ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ስለ ጥፋታቸው እያለቀሱ ወደ ሖሮናይም ለማምለጥ ይሞክራሉ።
ምድሪቱም ደርቃለች፤ ባድማ ሆናለች፤ የሊባኖስ ደኖች ደርቀዋል፤ ለሙ የሳሮን ሸለቆ ወደ በረሓነት ተለውጦአል፤ በባሳንና በቀርሜሎስ ተራራዎች የሚገኙ ዛፎች ቅጠላቸው ረግፎአል።
ይህም የሠራዊት አምላክ የወይን ቦታ የተባለው የእስራኤል ሕዝብ ነው፤ እርሱም የይሁዳ ሕዝብ ደስ የሚሰኝበት ተክል ነው። መልካም ሥራ እንዲሠሩ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ በዚህ ፈንታ ነፍሰ ገዳዮች ሆኑ፤ ቅን ፍርድ ይሰጣሉ ብሎ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ እነርሱ ግን ፍርድን በማጓደላቸው የሕዝቡ ጩኸት በዛ።
ስለዚህም እነሆ እኔ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፤ ከጥፋቱም ማምለጥ አይችሉም፤ የእኔን ርዳታ ለማግኘት ቢጮኹም እንኳ አልሰማቸውም።
“እኛ የምናደርገውን ሁሉ እግዚአብሔር አያይም” ከሚሉት ሕዝባችን ክፋት የተነሣ፥ ምድራችንን ድርቅ የሚያጠቃውና በየመስኩ ያለውስ ሣር እንደ ደረቀ የሚቀረው እስከ መቼ ነው? በዚህም ምክንያት እንስሶችና ወፎች ሁሉ ተጠራርገው ጠፍተዋል።
ምድር ታለቅሳለች፤ ሰማይም በጨለማ ይጋረዳል፤ ይህን እግዚአብሔር ተናግሮአል፤ ሐሳቡም አይለወጥም፤ ቊርጥ ውሳኔ አድርጎአል፤ ወደ ኋላም አይመለስም።
ሕዝቦች ሁሉ ስለ ኀፍረትሽ ሰምተዋል፤ የዓለምም ሕዝብ ሁሉ ጩኸትሽን አድምጠዋል፤ አንዱ ወታደር ሌላውን ወታደር ሲያደናቅፈው ሁሉም ተያይዞ መሬት ይወድቃል።
እግዚአብሔር የኢየሩሳሌምን ከተማ ቅጽር ለማፍረስ ወስኖ ገመዱን ዘረጋ፤ ከማጥፋት አልተመለሰም፤ የመጠበቂያ ግንቡና ቅጽሩ ተፈረካከሱ፤ በአንድነትም ፈረሱ።
የቅጽር በሮች ከመሬት በታች ተቀበሩ፤ መወርወሪያዎቻቸውም ተሰባብረው ወደቁ፤ ንጉሡና መሳፍንቱ አሁን በአሕዛብ መካከል በስደት ላይ ናቸው፤ የኦሪት ሕግ ትምህርት ከእንግዲህ ወዲህ አይሰጥም፤ ነቢያትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ራእይ አይገለጥላቸውም።
የተለየ የጾም ቀን ዐውጁ! መንፈሳዊ ስብስባ ጥሩ! ሽማግሌዎችንና ሌሎችንም የአገሪቱን ኗሪዎች ሁሉ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ በዚያም ወደ እግዚአብሔር ጩኹ።
እነሆ በዚህ ምክንያት በተራሮች ላይ በእህል፥ በወይን፥ በዘይት፥ ምድር በምታበቅለው ሁሉ ላይ፥ በሰዎችና በእንስሶች፥ በሥራቸውም ውጤት ሁሉ ላይ ድርቅን አመጣለሁ።”
“ነገ በዚህ ሰዓት ከብንያም አገር አንድ ሰው እልክልሃለሁ፤ ጩኸታቸው ወደ እኔ ስለ ደረሰ ወደ ሕዝቤ ተመልክቼአለሁና ከፍልስጥኤማውያን ጭቈና ሕዝቤን ስለሚያድን በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ አድርገህ ቀባው።”