Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 144:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከብቶቻችን የሰቡ ይሁኑ፤ ሳይጨነግፉም በመርባት ይብዙ፤ በመንገዶቻችን የሐዘን ጩኸት ከቶ አይሰማ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከብቶቻችን ይክበዱ፤ አይጨንግፉ፤ አይጥፉም። እኛም በምርኮ አንወሰድ፤ በአደባባዮቻችንም ዋይታ አይሰማ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ላሞቻቸንም የሰቡ ይሁኑ፥ ቅጥራቸውም መፍረሻና መውጫ አይኑረው፥ በአደባባዮቻችንም ዋይታ አይኑር፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቃሉ ሁሉ የታ​መነ ነው፥ በሥ​ራ​ውም ሁሉ ጻድቅ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ፍ​ገ​መ​ገ​ሙ​ትን ሁሉ ይደ​ግ​ፋ​ቸ​ዋል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የወ​ደ​ቁ​ትን ያነ​ሣ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 144:14
16 Referencias Cruzadas  

ስለ ብርቱ ጥንካሬው በእርሱ ትተማመናለህን? ከባድ ሥራህንስ ለእሱ ትተውለታለህን?


ዳግመኛ የወይን ጠጅ ስለማይገኝ ሰዎች በየአደባባዩ ይጮኻሉ፤ ደስታ ለዘለዓለም ጠፍቶአል፤ ሐሴትም በምድር ላይ አይገኝም፤


እኔም ራሴ በኢየሩሳሌምና በሕዝቤ ደስ ይለኛል፤ ከዚያም በኋላ ለቅሶም ሆነ የዋይታ ድምፅ አይኖርም።


ወደየመስኩ ብወጣ በጦርነት የተገደሉ ሰዎችን ሬሳ አያለሁ፤ ወደ ከተማም ብገባ በራብ ለመሞት የሚያጣጥሩ ሰዎችን አያለሁ፤ ነቢያትና ካህናት የራሳቸውን ጉዳይ ይከታተላሉ፤ ነገር ግን የሚያደርጉትን አያውቁም።”


“ይሁዳ በሐዘን ላይ ነች፤ ከተሞችዋም በሞት ጣዕር ላይ ናቸው፤ ሕዝብዋም በሐዘን ምክንያት በመሬት ላይ ተቀምጠው ያለቅሳሉ፤ ኢየሩሳሌም ወደ እግዚአብሔር ትጮኻለች።


“በምድራችሁ ሰላምን እሰጣችኋለሁ፤ ማንንም ሳትፈሩ ያለ ስጋት ትተኛላችሁ፤ አደገኞች የሆኑ አራዊትን ከምድራችሁ አስወግዳለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ጦርነት በዚያ አይኖርም።


“እግዚአብሔር ለጠላቶችህ በአንተ ላይ ድልን ይሰጣቸዋል፤ በአንድ በኩል ትመጣባቸዋለህ፤ ነገር ግን ከእነርሱ ለማምለጥ በሰባት አቅጣጫ ትሸሻለህ፤ በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ላይ የሚደርሰውን ነገር በሚያዩበት ጊዜ በፍርሃት ይሸበራሉ፤


“ጠላቶችህ በአንተ ላይ አደጋ በሚጥሉበት ጊዜ እግዚአብሔር እነርሱን ድል ያደርግልሃል፤ በአንድ አቅጣጫ ይመጡብሃል፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫ ይሸሻሉ።


እስራኤላውያን ቀድሞ የማያውቁአቸውን ባዕዳን አማልክትን በመረጡ ጊዜ፥ በምድሪቱ ላይ ጦርነት ሆነ፤ ከአርባ ሺህ እስራኤላውያን ጋሻና ጦር የያዘ አንድ ሰው እንኳ አልነበረም!


እስራኤላውያን ዘር በሚዘሩበት ጊዜ ምድያማውያን፥ ከዐማሌቃውያንና የምሥራቅ ሰዎች እየመጡ አደጋ ይጥሉባቸው ነበር።


ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ በምድያማውያን ምክንያት ችግር ደረሰባቸው፤ እንዲረዳቸውም ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።


ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅና በኢይዝራኤል ሸለቆ ማዶ የነበሩ እስራኤላውያንም የእስራኤል ሠራዊት መሸሹን፥ ሳኦልና ልጆቹም መገደላቸውን ሰምተው ከተሞቻቸውን እየጣሉ ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ከተሞቹን ያዙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos