ፊልጵስዩስ 3:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘወትር እንደምነግራችሁ፥ ልዩ አካሄድ የሚሄዱ ብዙዎች አሉና፤ አሁንም እነርሱ የክርስቶስ የመስቀሉ ጠላቶች እንደ ሆኑ በግልጥ እያለቀስሁ እነግራችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም ከዚህ በፊት ደጋግሜ እንደ ነገርኋችሁ፣ አሁንም እንደ ገና፣ ያውም በእንባ እነግራችኋለሁ፤ ብዙዎች የክርስቶስ መስቀል ጠላቶች ሆነው ይመላለሳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ ነገርኋችሁ፤ አሁንም እያነባሁ ስለ እነርሱ እነግራችኋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአሁን በፊት ብዙ ጊዜ እንደ ነገርኳችሁና አሁንም እንባዬን እያፈሰስኩ እንደምነግራችሁ ሁሉ ብዙዎቹ በአካሄዳቸው የክርስቶስ መስቀል ጠላቶች ሆነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ። |
ይህን ባትሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ በስውር ታለቅሳለች፤ የእግዚአብሔርም መንጋ ተሰብሮአልና ዐይኔ ታነባለች፤ እንባንም ታፈስሳለች።
እግዚአብሔርን እያገለገልሁ በፍጹም መከራና በልቅሶ ከአይሁድም ሴራ የተነሣ በደረሰብኝ ፈተና እየተጋደልሁ፥
ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? አያስቱአችሁ፤ ሴሰኞች፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ፥ ወይም አመንዝራዎች፥ ወይም ቀላጮች፥ ወይም በወንድ ላይ ዝሙትን የሚሠሩ፥ የሚሠሩባቸውም ቢሆኑ፤
የሚተነኰሉ፥ ራሳቸውን የክርስቶስን ሐዋርያት የሚያስመስሉ፥ ዐመፅንም የሚያደርጉ ሐሰተኞች ሐዋርያት አሉና።
ከብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት የተነሣ በብዙ እንባ ይህን ጽፌላችኋለሁ፤ ነገር ግን እጅግ እንደምወዳችሁ እንድታውቁ ነው እንጂ እንድታዝኑ አይደለም።
ነገር ግን ወደ እውነተኛው ወንጌል እግራቸውን እንዳላቀኑ ባየሁ ጊዜ፥ በሰው ሁሉ ፊት ኬፋን እንዲህ አልሁት፥ “አንተ አይሁዳዊ ስትሆን በአይሁድ ሥርዐት ያይደለ፥ በአረማውያን ሥርዐት የምትኖር ከሆነ እንግዲህ አይሁድ እንዲሆኑ አረማውያንን ለምን ታስገድዳቸዋለህ?”
ለሰው ፊት ሊያደሉ የሚወዱ እነዚያ እንድትገዘሩ ያስገድዱአችኋል፤ ነገር ግን የክርስቶስን መስቀል እንዳትከተሉ ነው።
እኔ ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንጂ በሌላ አልመካም፤ በእኔ ዘንድ ዓለሙ የሞተ ነው፥ እኔም በዓለሙ ዘንድ የሞትሁ ነኝ።
እንግዲህ በልባቸው ከንቱ አሳብ እንደሚኖሩ እንደ አሕዛብ እንዳትኖሩ ይህን እላለሁ፤ በእግዚአብሔርም እመሰክራለሁ።
አስቀድመን ደግሞ እንዳልናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።