Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ገላትያ 6:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ለሰው ፊት ሊያ​ደሉ የሚ​ወዱ እነ​ዚያ እን​ድ​ት​ገ​ዘሩ ያስ​ገ​ድ​ዱ​አ​ች​ኋል፤ ነገር ግን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን መስ​ቀል እን​ዳ​ት​ከ​ተሉ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ውጫዊ በሆነ ነገር ለመታየት የሚፈልጉ ሰዎች ትገረዙ ዘንድ ሊያስገድዷችሁ ይጥራሉ፤ ይህንም የሚያደርጉት ስለ ክርስቶስ መስቀል እንዳይሰደዱ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በሥጋ መልካም ሆነው መታየት የሚፈልጉ ሁሉ እንድትገረዙ አስገደዱአችሁ፤ ይህን ያደረጉት ስለ ክርስቶስ መስቀል እንዳይሰደዱ ብቻ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እንድትገረዙ የሚያስገድዱአችሁ በውጭ መልካም መስለው ለመታየት የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው። ይህን የሚያደርጉትም በክርስቶስ መስቀል ምክንያት ስደት እንዳይደርስባቸው ብለው ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በሥጋ መልካም ሆነው ሊታዩ የሚወዱ ሁሉ እንድትገረዙ ግድ አሉአችሁ፥ ነገር ግን ስለ ክርስቶስ መስቀል እንዳይሰደዱ ብቻ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ገላትያ 6:12
22 Referencias Cruzadas  

“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጡ ግን የሙታን አጥንት ርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ፥ ወዮላችሁ።


እንዲሁ እናንተ ደግሞ በውጭ ለሰው እንደ ጻድቃን ትታያላችሁ፤ በውስጣችሁ ግን ግብዝነትና ዐመፀኝነት ሞልቶባችኋል።


ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ፤ ዘርፉንም ያስረዝማሉ፤


ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፤መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።


“ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።


“እንግዲህ ምጽዋት ስታደርግ፥ ግብዞች በሰው ዘንድ ሊከበሩ በምኩራብ በመንገድም እንደሚያደርጉ በፊትህ መለከት አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።


“ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።


እር​ሱም፥ “እና​ን​ተስ ለሰው ይም​ሰል ትመ​ጻ​ደ​ቃ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልቡ​ና​ች​ሁን ያው​ቃል፤ በሰው ዘንድ የከ​በረ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ናቀ ይሆ​ና​ልና።


የመ​በ​ለ​ቶ​ችን ገን​ዘብ የሚ​በሉ፥ ለም​ክ​ን​ያት ጸሎ​ት​ንም የሚ​ያ​ስ​ረ​ዝሙ እነ​ዚህ ታላቅ ፍር​ድን ይቀ​በ​ላሉ።”


ከራሱ የሚ​ና​ገር የራ​ሱን ክብር ይሻል፤ የላ​ከ​ውን ያከ​ብር ዘንድ የሚ​ፈ​ልግ ግን እው​ነ​ተኛ ነው፤ ሐሰ​ትም የለ​በ​ትም።


ከይ​ሁዳ ሀገ​ርም የወ​ረዱ ሰዎች፥ “እንደ ሙሴ ሕግ ካል​ተ​ገ​ዘ​ራ​ችሁ ልት​ድኑ አት​ች​ሉም” እያሉ ወን​ድ​ሞ​ችን ያስ​ተ​ምሩ ነበር።


ነገር ግን ካመ​ኑት ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወገን አን​ዳ​ን​ዶች ተነ​ሥ​ተው፥ “ትገ​ዝ​ሩ​አ​ቸው ዘን​ድና የሙ​ሴን ሕግ እን​ዲ​ጠ​ብቁ ታዝ​ዙ​አ​ቸው ዘንድ ይገ​ባል” አሉ።


እነ​ርሱ ራሳ​ቸ​ውን በአ​ሰ​ቡ​ትና በገ​መ​ገ​ሙት መጠን ራሳ​ቸ​ውን ከሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑት ሰዎች ጋር ራሳ​ች​ንን ልን​ቈ​ጥር፥ ወይም ራሳ​ች​ንን ልና​ስ​ተ​ያይ አን​ደ​ፍ​ርም፤ እነ​ርሱ ራሳ​ቸ​ውም የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን ትር​ጕ​ሙን አያ​ው​ቁ​ትም።


የሚ​ተ​ነ​ኰሉ፥ ራሳ​ቸ​ውን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ሐዋ​ር​ያት የሚ​ያ​ስ​መ​ስሉ፥ ዐመ​ፅ​ንም የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሐሰ​ተ​ኞች ሐዋ​ር​ያት አሉና።


ነገር ግን ወደ እው​ነ​ተ​ኛው ወን​ጌል እግ​ራ​ቸ​ውን እን​ዳ​ላ​ቀኑ ባየሁ ጊዜ፥ በሰው ሁሉ ፊት ኬፋን እን​ዲህ አል​ሁት፥ “አንተ አይ​ሁ​ዳዊ ስት​ሆን በአ​ይ​ሁድ ሥር​ዐት ያይ​ደለ፥ በአ​ረ​ማ​ው​ያን ሥር​ዐት የም​ት​ኖር ከሆነ እን​ግ​ዲህ አይ​ሁድ እን​ዲ​ሆኑ አረ​ማ​ው​ያ​ንን ለምን ታስ​ገ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለህ?”


አብ​ሮኝ የነ​በ​ረው ቲቶም አረ​ማዊ ሲሆን እን​ዲ​ገ​ዘር ግድ አላ​ል​ሁ​ትም።


ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እኔ ግዝ​ረ​ትን ገና የም​ሰ​ብክ ከሆነ፥ እን​ግ​ዲህ ለምን ያሳ​ድ​ዱ​ኛል? እን​ግ​ዲህ የክ​ር​ስ​ቶስ የመ​ስ​ቀሉ ተግ​ዳ​ሮት እን​ዲ​ያው ቀር​ቶ​አል።


የተ​ገ​ዘ​ሩ​ትም ቢሆኑ በሰ​ው​ነ​ታ​ችሁ እን​ደ​ም​ት​መኩ ልት​ገ​ዘሩ ይወ​ዳሉ እንጂ ኦሪ​ትን አል​ጠ​በ​ቁም።


ከእ​ነ​ርሱ አን​ዳ​ን​ዶች በቅ​ና​ታ​ቸ​ውና በክ​ር​ክ​ራ​ቸው፥ ሌሎ​ችም በበጎ ፈቃድ ስለ ክር​ስ​ቶስ ሊሰ​ብ​ኩና ሊያ​ስ​ተ​ምሩ የወ​ደዱ አሉ።


ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ች​ሁም እንጂ ለየ​ራ​ሳ​ችሁ ብቻ አታ​ስቡ።


ዘወ​ትር እን​ደ​ም​ነ​ግ​ራ​ችሁ፥ ልዩ አካ​ሄድ የሚ​ሄዱ ብዙ​ዎች አሉና፤ አሁ​ንም እነ​ርሱ የክ​ር​ስ​ቶስ የመ​ስ​ቀሉ ጠላ​ቶች እንደ ሆኑ በግ​ልጥ እያ​ለ​ቀ​ስሁ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።


ይህም ስለ ልብ ትሕ​ት​ናና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስለ መፍ​ራት፥ ለሥጋ ስለ አለ​ማ​ዘን ጥበ​ብን ይመ​ስ​ላል፤ ነገር ግን ከሥጋ በላይ ነው እንጂ ምንም ክብር የለ​ውም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos