Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 13:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ካህ​ኑም ያያል፤ እነ​ሆም፥ ምል​ክቱ በቆ​ዳው ላይ ቢሰፋ ካህኑ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለ​ዋል፤ ለምጽ ነውና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ካህኑም ይመርምረው፤ ችፍታው በቈዳው ላይ ተስፋፍቶ ከተገኘ፣ ካህኑ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቅ፤ ተላላፊ የቈዳ በሽታ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ካህኑም ያያል፤ እነሆም፥ እከኩ በቆዳው ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ እርሱ የለምጽ ደዌ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ካህኑም እንደገና ይመርምረው፤ ቊስሉም ተስፋፍቶ ከተገኘ የሥጋ ደዌ በሽታ ስለ ሆነ የረከሰ የሥጋ ደዌ በሽተኛ መሆኑን ያስታውቅ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ካህኑም ያያል፤ እነሆም፥ እከኩ በቁርበቱ ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ ለምጽ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 13:8
9 Referencias Cruzadas  

“ሰው በሥ​ጋው ቆዳ ላይ እባጭ ብት​ወ​ጣ​በት፥ ብት​ነ​ጣም፥ በሥ​ጋ​ውም ቆዳ እንደ ለምጽ ደዌ ብት​መ​ስል፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ከካ​ህ​ናቱ ልጆች ወደ አንዱ ያም​ጡት።


ካህ​ኑም በሥ​ጋው ቆዳ ያለ​ች​ውን ያችን ደዌ ይያት፤ ጠጕ​ሯም ተለ​ውጣ ብት​ነጣ በሥ​ጋው ቆዳ ያለች የዚ​ያች ደዌ መልክ ቢከፋ፥ ደዌ​ውም ወደ ሥጋው ቆዳ ቢጠ​ልቅ፥ እር​ስዋ የለ​ምጽ ደዌ ናት፤ ካህ​ኑም አይቶ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይበ​ለው።


ስለ መን​ጻቱ በካ​ህኑ ዘንድ ከታየ በኋላ ምል​ክቱ በቆ​ዳው ላይ ቢሰፋ፥ እን​ደ​ገና ሊታይ ወደ ካህኑ ይቀ​ር​ባል።


“የለ​ምጽ ደዌ በሰው ላይ ቢወጣ እርሱ ወደ ካህኑ ይሄ​ዳል።


“የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለም​ጻ​ሙን ሁሉ ፈሳሽ ነገ​ርም ያለ​በ​ትን ሁሉ በሰ​ው​ነቱ የረ​ከ​ሰ​ውን ሁሉ ከሰ​ፈሩ እን​ዲ​ያ​ወጡ እዘ​ዛ​ቸው፤


በዚህ ነገር ዕድ​ልና ርስት የለ​ህም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ልብህ የቀና አይ​ደ​ለ​ምና።


ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው “አርነት ትወጣላችሁ፤” እያሉ ተስፋ ይሰጡአቸዋል፤ ሰው ለተሸነፈበት ለእርሱ ተገዝቶ ባሪያ ነውና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos