Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ገላትያ 5:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 አስ​ቀ​ድሜ እንደ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት አያ​ይም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ምቀኛነት፣ ስካር፣ ዘፋኝነት፣ እንዲሁም እነዚህን የመሰለው ነው። አስቀድሜ እንዳልሁ፣ አሁንም አስጠነቅቃችኋለሁ፤ በእንዲህ ሁኔታ የሚኖሩ ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ መሶልሶል፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜ እንደ ነገርኋችሁ፥ አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ምቀኝነት፥ ስካር፥ ቅጥ ያጣ ፈንጠዝያ እነዚህን የመሳሰሉ ናቸው፤ ከዚህ በፊት እንዳስጠነቀቅኋችሁ አሁንም ደግሜ አስጠነቅቃችኋለሁ፤ እንደ እነዚህ ያሉትን ነገሮች የሚያደርጉ ሰዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

Ver Capítulo Copiar




ገላትያ 5:21
19 Referencias Cruzadas  

በቀን እን​ደ​ሚ​ሆን በጽ​ድቅ ሥራ እን​መ​ላ​ለስ፤ በዘ​ፈ​ንና በስ​ካር፥ በዝ​ሙ​ትና በመ​ዳ​ራ​ትም አይ​ሁን፤ በክ​ር​ክ​ርና በቅ​ና​ትም አይ​ሁን።


እንደ ሥጋ ፈቃድ ብት​ኖሩ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን በመ​ን​ፈ​ሳዊ ሥራ የሥ​ጋ​ች​ሁን ፈቃድ ብት​ገ​ድሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።


መዳ​ራት ነውና ወይን በመ​ጠ​ጣት አት​ስ​ከሩ፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተመሉ እንጂ።


አሁ​ንም ከወ​ን​ድ​ሞች መካ​ከል ዘማዊ፥ ወይም ገን​ዘ​ብን የሚ​መኝ፥ ወይም ጣዖ​ትን የሚ​ያ​መ​ልክ፥ ወይም ዐመ​ፀኛ፥ ወይም ተራ​ጋሚ፥ ወይም ሰካ​ራም፥ ወይም የሚ​ቀማ ቢኖር እን​ደ​ዚህ ካለ ሰው ጋር አንድ እን​ዳ​ት​ሆኑ ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ፥ እን​ደ​ዚህ ካለው ሰው ጋር መብ​ልም እንኳ አት​ብሉ፤


ለበጉም በሆነው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት በቀር፥ ጸያፍ ነገር ሁሉ ርኵሰትና ውሸትም የሚያደርግ ወደ እርስዋ ከቶ አይገባም።


የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።


በእ​ነ​ር​ሱም ምክ​ን​ያት በማ​ይ​ታ​ዘዙ ልጆች ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ጣል።


የሚያንቀላፉ በሌሊት ያንቀላፋሉና፤ የሚሰክሩም በሌሊት ይሰክራሉና፤


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ይህን እን​ነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለን፦ ሥጋ​ዊና ደማዊ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት አይ​ወ​ር​ስም፥ የሚ​ፈ​ር​ሰው የማ​ይ​ፈ​ር​ሰ​ውን አይ​ወ​ር​ስም።


ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።


ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል ‘እናንተ የአባቴ ቡሩካን! ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።


እንደ እጁ ሥራ ፍዳው ይደ​ረ​ግ​በ​ታ​ልና ለበ​ደ​ለኛ ወዮ! ክፉም ይደ​ር​ስ​በ​ታል።


“ራሳ​ች​ሁን ጠብቁ፤ በመ​ብ​ልና በመ​ጠጥ፥ በመ​ቀ​ማ​ጠ​ልና የዓ​ለ​ምን ኑሮ በማ​ሰብ ልባ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ፤ ያቺ ቀንም በድ​ን​ገት ትደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋ​ለች።


የከ​ተ​ማ​ዉ​ንም ሰዎች፦ ‘ይህ ልጃ​ችን ትዕ​ቢ​ተ​ኛና ዐመ​ፀኛ ነው፥ ቃላ​ች​ን​ንም አይ​ሰ​ማም፤ ስስ​ታ​ምና ሰካ​ራም ነው’ ይበ​ሉ​አ​ቸው።


መጋ​ባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፥ ለመ​ኝ​ታ​ቸ​ውም ርኵ​ሰት የለ​ውም፤ ሴሰ​ኞ​ች​ንና አመ​ን​ዝ​ሮ​ችን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋል።


ገና ከእናንተ ጋር ሳለሁ ይህን እንዳልኋችሁ ትዝ አይላችሁምን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios