ሰቈቃወ 1:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጤት። ግዳጅዋ ከእግርዋ በታች ነበረ፤ ፍጻሜዋን አላሰበችም፤ ከባድ ሸክምን ተሸከመች፤ የሚያጽናናትም የለም፤ አቤቱ! ጠላት ከፍ ከፍ ብሎአልና መከራዬን ተመልከት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርኩሰቷ በቀሚሷ ላይ ታየ፤ ወደ ፊት የሚሆንባትን አላሰበችም፤ አወዳደቋ አስደንጋጭ ሆነ፤ የሚያጽናናትም አልነበረም፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ መከራዬን ተመልከት፤ ጠላት ድል አድርጓልና!” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጤት። አደፍዋ በልብስዋ ዘርፍ ነበረ፥ ፍጻሜዋን አላሰበችም፥ ስለዚህ በድንቅ ተዋርዳለች፥ የሚያጽናናትም የለም፥ አቤቱ፥ ጠላት ከፍ ከፍ ብሏልና መከራዬን ተመልከት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አደፍዋ በቀሚስዋ ላይ ይታያል፤ ለወደፊት ምን እንደሚደርስባት አላሰበችም፤ አወዳደቅዋ የሚያሰቅቅ ነው፤ የሚያጽናናት ከቶ የለም፤ ጠላቶችዋ ድል ስላደረግዋት፥ መከራዋን እንዲመለከትላት ወደ እግዚአብሔር ጸለየች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጤት። አደፍዋ በልብስዋ ዘርፍ ነበረ፥ ፍጻሜዋን አላሰበችም፥ ስለዚህ በድንቅ ተዋርዳለች፥ የሚያጽናናትም የለም፥ አቤቱ፥ ጠላት ከፍ ከፍ ብሎአልና መከራዬን ተመልከት። |
በቍጥር እንዳነሱ፥ የታሰረውና የተለቀቀውም እንደ ጠፋ፥ እስራኤልንም የሚረዳ እንዳልነበረ እግዚአብሔር እጅግ የመረረውን የእስራኤልን ጭንቀት አየ።
“አሁንም አምላካችን ሆይ፥ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ ታላቅና ኀያል ጽኑዕና የተፈራኸው አምላክ ሆይ፥ ከአሦር ነገሥታት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ በእኛና በነገሥታቶቻችን፥ በአለቆቻችንም፥ በካህናቶቻችንም፥ በነቢያቶቻችንም፥ በአባቶቻችንም፥ በሕዝብህ ሁሉ ላይ የደረሰው መከራ ሁሉ በፊትህ ጥቂት መስሎ አይታይህ።
እንዲህም አልሁ፦ ከግብፅ መከራ ወደ ከነዓናውያን፥ ወደ ኬጤዎናውያን፥ ወደ አሞሬዎናውያን፥ ወደ ፌርዜዎናውያን፥ ወደ ጌርጌሴዎናውያን፥ ወደ ኤዌዎናውያን፥ ወደ ኢያቡሴዎናውያን ሀገር፥ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ሀገር አወጣችኋለሁ፤
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “በግብፅ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፦ ከአሠሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም ዐውቄአለሁ፤
ሕዝቡም አመኑ፤ ደስም አላቸው፤ እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች ጐብኝቶአልና፤ ጭንቀታቸውንም አይቶአልና፤ ሕዝቡም ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሰገዱ።
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሓይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ እነሆም፥ የተገፉት ሰዎች እንባ ነበረ፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፤ በሚገፉአቸውም እጅ ኀይል ነበረ። እነርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።
ኢየሩሳሌም ተፈትታለችና፥ ይሁዳም ወድቃለችና፥ አንደበታቸውም ዐመፅን ስለሚናገር ለእግዚአብሔር አልታዘዙም።
አቤቱ፥ ጆሮህን አዘንብልና ስማ፤ አቤቱ፥ ዐይንህን ክፈትና በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ የላከውን የሰናክሬምን ቃል ተመልከት።
የተገዳደርኸው፥ የሰደብኸውስ ማንን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደረግህበት፥ ዐይንህንስ ወደ ላይ ያነሣህበት ማን ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ አይደለምን?
የተቈጣኸው ቍጣና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአልና ሰለዚህ ስናጋዬን በአፍንጫህ፥ ልጓሜንም በከንፈርህ አደርጋለሁ፤ በመጣህበትም መንገድ እመልስሃለሁ።
ምናልባት በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ ጌታው የአሦር ንጉሥ የላከውን የራፋስቂስን ቃል አምላክህ እግዚአብሔር ይሰማ እንደ ሆነ፥ አምላክህ እግዚአብሔርም ስለ ሰማው ቃል ይገሥጸው እንደ ሆነ፥ ስለዚህ ለቀረው ቅሬታ ጸልይ” አሉት።
ካህናት ሆይ፥ ለኢየሩሳሌም ወደ ልቧ የሚገባ ነገርን ተናገሩ፤ ውርደቷ እንደ ተፈጸመ፥ ኀጢአቷም እንደ ተሰረየ፥ ከእግዚአብሔርም እጅ ስለ ኀጢአቷ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች አጽናኑአት።
አንቺም፥ “እኔ ለዘለዓለም እመቤት እሆናለሁ” ብለሻል፤ ይህንም በልብሽ አላሰብሽም፤ ፍጻሜውንም አላስታወስሽም።
አሁንም እነዚህ ሁለቱ ይጠብቁሻል፤ ማን ያስተዛዝንሻል? እነርሱም ጥፋትና ውድቀት ራብና ሰይፍ ናቸው፤ እንግዲህ የሚያጽናናሽ ማን ነው?
አንቺ የተቸገርሽ የተናወጥሽ ያልተጽናናሽም፥ እነሆ፥ ድንጋዮችሽን የሚያበሩ አደርጋለሁ፤ መሠረትሽንም የሰንፔር አደርገዋለሁ።
አስጸያፊ ሥራሽን፥ ምንዝርናሽን፥ ማሽካካትሽን፥ የዝሙትሽንም መዳራት በኮረብቶች ላይ፥ በሜዳም ላይ አይቻለሁ። ኢየሩሳሌም ሆይ! ወዮልሽ! ለመንጻት እንቢ ብለሻል፤ ይህስ እስከ መቼ ነው?
ሰዎችም ስለ ሞቱት ለማጽናናት የእዝን እንጀራ አይቈርሱላቸውም፤ ስለ አባታቸውና ስለ እናታቸውም የመጽናናት ጽዋ አያጠጡአቸውም።
በእጆችሽም የንጹሓን ድሆች ደም ተገኝቶአል፤ በዛፍ ሁሉ ላይ በግልጥ አገኘሁት እንጂ በጕድጓድ ፈልጌ አላገኘሁትም።
“በእግዚአብሔር ላይ ኰርቶአልና፥ አስክሩት፤ ሞአብም በትፋቱ ላይ ይንከባለላል፤ በእጁም ያጨበጭባል፤ ደግሞ መሳቂያ ይሆናል።
ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእጃቸው ያጨበጭባሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?
“ቀስትን የሚገትሩ ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩአቸው፤ በዙሪያዋ ስፈሩባት፤ ከእርስዋም ሰዎች አንድ አያምልጥ፤ የእስራኤልን ቅዱስ እግዚአብሔርን ተቃውማለችና እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፤ እንዳደረገችም ሁሉ አድርጉባት።
ፌ። ጽዮን እጅዋን ዘረጋች፤ የሚያጽናናትም የለም፤ እግዚአብሔር በያዕቆብ ዙሪያ ያሉትን እንዲያስጨንቁት አዘዘ፤ ኢየሩሳሌም በመካከላቸው እንደ ረከሰች ሆናለች።
ሣን። እኔ እንደማለቅስ ሰምተዋል፤ የሚያጽናናኝ የለም፤ ጠላቶች ሁሉ መከራዬን ሰምተዋል፤ አንተ አድርገኸዋልና ደስ አላቸው፤ ስለ እርሱ የተናገርኸውን ቃል ታመጣለህ፤ እነርሱም እንደ እኔ ይሆናሉ።
ሜም። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ማን ያድንሻል? ማንስ ያጽናናሻል? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፤ የሚፈውስሽ ማን ነው?
ወደ አባቶቻችንም አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ቃላችንን ሰማ፤ ጭንቀታችንንም፥ ድካማችንንም፥ ግፋችንንም አየ፤
ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንዳይታበዩ፦ እጃችን ከፍ ከፍ አለች እንጂ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ አላደረገም እንዳይሉ፥ በቍጣ ጠላት ሆኑኝ።
ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?
እርስዋም፥ “አዶናይ፥ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! የባርያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለባርያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ ዕድሜውን ሁሉ ለአንተ እሰጠዋለሁ፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥም አይጠጣም። ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም” ብላ ስእለት ተሳለች።