Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 16:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ሰዎ​ችም ስለ ሞቱት ለማ​ጽ​ና​ናት የእ​ዝን እን​ጀራ አይ​ቈ​ር​ሱ​ላ​ቸ​ውም፤ ስለ አባ​ታ​ቸ​ውና ስለ እና​ታ​ቸ​ውም የመ​ጽ​ና​ናት ጽዋ አያ​ጠ​ጡ​አ​ቸ​ውም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ሐዘንተኞችን ለማጽናናት የዕዝን እንጀራ የሚያመጣ አይኖርም፤ አባትም ሆነ እናት የሞተባቸውንም ለማጽናናት መጠጥ የሚያቀርብ አይገኝም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ሰዎችም ስለ ሞቱት ለማጽናናት የኀዝን እንጀራ አይቈርሱላቸውም፥ ስለ አባታቸውና ስለ እናታቸውም የመጽናናት ጽዋ አያጠጡአቸውም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ወዳጁ የሞተበትን ሰው ለማጽናናት የእዝን እንጀራ በመውሰድ አብሮት የሚበላና የሚጠጣ አይኖርም፤ ሌላው ቀርቶ እናትም አባትም የሞቱበትን የሚያጽናና አይገኝም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ሰዎችም ስለ ሞቱት ለማጽናናት የእዝን እንጀራ አይቈርሱላቸውም፥ ስለ አባታቸውና ስለ እናታቸውም የመጽናናት ጽዋ አያጠጡአቸውም።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 16:7
8 Referencias Cruzadas  

ወን​ድ​ሞ​ቹና እኅ​ቶቹ ቀድ​ሞም ያው​ቁት የነ​በ​ሩት ሁሉ የሆ​ነ​ውን ሁሉ በሰሙ ጊዜ ወደ እርሱ መጡ፥ በቤ​ቱም ከእ​ርሱ ጋር እን​ጀራ በሉ፥ ጠጡም፤ አጽ​ና​ኑ​ትም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባመ​ጣ​በት ክፉ ነገር ሁሉ አደ​ነቁ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም ጥማድ በሬ፥ አራት ድራ​ህማ የሚ​መ​ዝን ወር​ቅና ብር ሰጡት።


እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ እነ​ሆም፥ የተ​ገ​ፉት ሰዎች እንባ ነበረ፤ የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ቸ​ውም አል​ነ​በ​ረም፤ በሚ​ገ​ፉ​አ​ቸ​ውም እጅ ኀይል ነበረ። እነ​ር​ሱን ግን የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ቸው አል​ነ​በ​ረም።


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​መ​ለ​ስ​ምና፥ የተ​ወ​ለ​ደ​ባ​ት​ንም ሀገር አያ​ይ​ምና ለሚ​ወጣ እጅግ አል​ቅሱ እንጂ ለሞተ አታ​ል​ቅሱ፤ አት​ዘ​ኑ​ለ​ትም።


ጤት። ግዳ​ጅዋ ከእ​ግ​ርዋ በታች ነበረ፤ ፍጻ​ሜ​ዋን አላ​ሰ​በ​ችም፤ ከባድ ሸክ​ምን ተሸ​ከ​መች፤ የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ትም የለም፤ አቤቱ! ጠላት ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና መከ​ራ​ዬን ተመ​ል​ከት።


በቀ​ስታ ተክዝ፤ ነገር ግን የሙ​ታ​ንን ልቅሶ አታ​ል​ቅስ፤ መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያ​ህን በራ​ስህ ላይ አድ​ርግ፤ ጫማ​ህ​ንም በእ​ግ​ርህ አጥ​ልቅ፤ ከን​ፈ​ሮ​ች​ህ​ንም አት​ሸ​ፍን፤ የዕ​ዝን እን​ጀ​ራ​ንም አት​ብላ።”


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የወ​ይን ጠጅን ቍር​ባን አያ​ቀ​ር​ቡም፤ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውም ደስ አያ​ሰ​ኘ​ውም፤ እንደ ኀዘ​ንም እን​ጀራ ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል፤ የሚ​በ​ላ​ውም ሁሉ ይረ​ክ​ሳል፤ እን​ጀ​ራ​ቸ​ውም ለሰ​ው​ነ​ታ​ቸው ይሆ​ናል እንጂ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ገ​ባም።


በኀ​ዘ​ኔም ጊዜ እኔ ከእ​ርሱ አል​በ​ላ​ሁም፤ ለር​ኩ​ስም ነገር ከእ​ርሱ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት አል​ሠ​ዋ​ሁም፤ ከእ​ር​ሱም አን​ዳች ለሞተ ሰው አል​ሰ​ጠ​ሁም፤ የአ​ም​ላ​ኬ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰም​ቼ​አ​ለሁ፤ ያዘ​ዝ​ኸ​ኝ​ንም ሁሉ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos