ኢዮብ 18:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መከራ በዙሪያው ታጠፋዋለች፤ ብዙ ጠላቶችም ከእግሩ በታች ይመጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንጋጤ በዙሪያው ያስፈራራዋል፤ ተከትሎም ያሳድደዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንጋጤ በዙሪያው ታስፈራዋለች፥ በስተ ኋላውም ሆና ታባርራቸዋለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ፍርሀት በዙሪያው ከቦታል፤ በኋላው እየተከተለም ያሳድደዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንጋጤ በዙሪያው ታስፈራዋለች፥ በስተ ኋላውም ሆና ታባርራቸዋለች። |
ባለፈም ጊዜ ይወስዳችኋል፤ ማለዳ ማለዳ በቀን ያልፋል፤ በሌሊት ክፉ ተስፋ ይሆናል፤ እናንተ ያዘናችሁ፥ መስማትን ተማሩ።”
ፈርተው ወደ ኋላ ሲመለሱ፥ ኀያላኖቻቸውም ሲደክሙ፥ ወደ ኋላቸውም ሳይመለከቱ ፈጥነው ሲሸሹ ለምን አየሁ? በዙሪያቸውም ይከቡአቸዋል፥” ይላል እግዚአብሔር።
ድንኳናቸውንና በጎቻቸውን ይወስዳሉ፤ መጋረጃዎቻቸውንና ዕቃቸውን ሁሉ፥ ግመሎቻቸውንም ለራሳቸው ይወስዳሉ፤ በዙሪያቸውም ሁሉ ጥፋትን ጥሩባቸው።
በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ ተለይተው በቀሩት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እሰድድባቸዋለሁ፤ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታሸብራቸዋለች፤ ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ ፤
እግዚአብሔርን መፍራት ዐውቀን ሰዎችን እናሳምናለን፤ ለእግዚአብሔር ግን እኛ የተገለጥን ነን፤ እንዲሁም በልቡናችሁ የተገለጥን እንደ ሆን እንታመናለን።