Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 18:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 “ፍርሀት በዙሪያው ከቦታል፤ በኋላው እየተከተለም ያሳድደዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ድንጋጤ በዙሪያው ያስፈራራዋል፤ ተከትሎም ያሳድደዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ድንጋጤ በዙሪያው ታስፈራዋለች፥ በስተ ኋላውም ሆና ታባርራቸዋለች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 መከራ በዙ​ሪ​ያው ታጠ​ፋ​ዋ​ለች፤ ብዙ ጠላ​ቶ​ችም ከእ​ግሩ በታች ይመ​ጣሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ድንጋጤ በዙሪያው ታስፈራዋለች፥ በስተ ኋላውም ሆና ታባርራቸዋለች።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 18:11
22 Referencias Cruzadas  

የሽብርን ድምፅ በጆሮው ይሰማል፤ ሁሉ ነገር ሰላም መስሎ በሚታይበት ጊዜ አጥፊው ይመጣበታል።


በመሬት ላይ የሸምቀቆ ገመድ ተዘርግቶለታል፤ በመንገዱም ወጥመድ ተዘጋጅቶአል።


ከብርሃን ወደ ጨለማ ይባረራል፤ ከሕያዋን ምድርም ይወገዳል።


ፍላጻውም ዘልቆ በስተጀርባው ይወጣል፤ የሚያብለጨልጨው ጫፉ ጒበቱን በጣጥሶ ያልፋል፤ በታላቅ ፍርሀትም ልቡ ይሸበራል።


እንደ ሕልም ብን ብሎ ስለሚጠፋ አይገኝም፤ እንደ ሌሊት ራእይም ይጠፋል።


በዚህም ምክንያት እነሆ፥ ዙሪያህን በወጥመድ ተከበሃል፤ ድንገተኛ አደጋም ያሸብርሃል፤


ድንጋጤ እንደ ጐርፍ በድንገት ይደርስበታል፤ በሌሊትም ዐውሎ ነፋስ ይነጥቀዋል።


ሁሉን የሚችል አምላክ በፍላጻዎቹ ወግቶኛል፤ መርዛቸውም በሰውነቴ ተሠራጭቶአል፤ የሚያስደነግጥ የእግዚአብሔር መቅሠፍት ዙሪያዬን ከቦኛል።


እግዚአብሔር የሕዝቡን ጠላቶች ስለ ሰባበራቸው ከምንጊዜውም ይልቅ በፍርሃት ተጨነቁ፤ እግዚአብሔርም ስለ ጠላቸው ፈጽሞ ያፍራሉ።


በቅጽበት ተደመሰሱ፤ መጨረሻቸውም አስደንጋጭ ሆነ።


ኃጢአተኞች ማንም ሳያሳድዳቸው ይሸሻሉ፤ ደግ ሰዎች ግን እንደ አንበሳ ደፋሮች ናቸው።


እርሱም ባለፈ ቊጥር ይወስዳችኋል፤ እርሱም በየማለዳው በቀንና በሌሊት ያልፋል፤ ይህን መልእክት መረዳት የሚያመጣው ሽብርን ብቻ ነው።


“ነገር ግን ይህ የማየው ነገር ምንድን ነው? ከፍርሃት የተነሣ ወደ ኋላ በመመለስ ላይ ናቸው፤ ወታደሮቻቸው ድል ሆኑ፤ በየአቅጣጫው ፍርሀትና ሽብር ስላለ ወደ ኋላ መለስ ብለው ሳያዩም ወደ ፊት ሸሹ።


ድንኳኖቻቸውን፥ መንጋዎቻቸውን፥ መጋረጃዎቻቸውንና ዕቃዎቻቸውን ሁሉ ውሰዱ፤ ግመሎቻቸውን ለራሳችሁ ውሰዱ። ‘በዙሪያው ሽብር ተነሥቷል’ ብለው ይጮኻሉ።”


ወደ እርሻ አትውጡ፤ በመንገድ ላይም አትዘዋወሩ፤ በየአቅጣጫው ሽብር ስለ ሆነ ከጠላት ሰይፍ ተጠንቀቁ።”


ንጉሥ ብልጣሶር እጅግ ስለ ጨነቀው ፊቱ ይብሱን እየገረጣ ሄደ፤ መኳንንቱም ግራ ገብቶአቸው የሚያደርጉትን አጡ።


“ከስደት የቀሩት ሁሉ ነፋስ የሚነካውን የቅጠል ኮሽታ በሰሙ ቊጥር በድንጋጤ በርግገው እንዲሸሹ አደርጋለሁ፤ በጦርነት ላይ ልክ ጠላት እንደሚያሳድዳቸው ያኽል ሆነው ይሸሻሉ፤ ምንም ዐይነት ጠላት በአጠገባቸው ሳይኖር ተደናቅፈው ይወድቃሉ፤


ጌታን መፍራት ምን መሆኑን ስለምናውቅ ሰዎችን እናስረዳለን፤ እኛ ምን መሆናችንንም እግዚአብሔር ያውቃል፤ እናንተም በልቡናችሁ ምን መሆናችንን እንደምታውቁ ተስፋ አደርጋለሁ።


ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ብዛት ባየ ጊዜ ፈራ፤ ልቡም ተሸበረ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos