ኢዮብ 6:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 እነሆ፥ የእግዚአብሔር ፍላጻ በሥጋዬ ላይ ነው፤ መርዙም ደሜን ይመጥጣል። ለመናገር ስጀምርም ይወጋኛል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ሁሉን ቻይ አምላክ ፍላጻ በውስጤ ነው፤ መንፈሴም መርዙን ትጠጣለች፤ የእግዚአብሔር ማስደንገጥ ተሰልፎብኛል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ሁሉን የሚችል የአምላክ ፍላጻ በሥጋዬ ውስጥ ነው፥ መርዙንም ነፍሴ ትጠጣለች፥ የእግዚአብሔር ሽብሮች በኔ ላይ ተሰልፈዋል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ሁሉን የሚችል አምላክ በፍላጻዎቹ ወግቶኛል፤ መርዛቸውም በሰውነቴ ተሠራጭቶአል፤ የሚያስደነግጥ የእግዚአብሔር መቅሠፍት ዙሪያዬን ከቦኛል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ሁሉን የሚችል የአምላክ ፍላጻ በሥጋዬ ውስጥ ነው፥ መርዙንም ነፍሴ ትጠጣለች፥ የእግዚአብሔር ድንጋጤ በላዬ ተሰልፎአል። Ver Capítulo |