Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


1 ሳሙኤል 28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዚያ ወራት ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ይዋጉ ዘንድ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጭፍ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ለሰ​ልፍ ሰበ​ሰቡ፤ አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን፥ “አን​ተና ሰዎ​ችህ ከእኔ ጋር ወደ ሰልፍ እን​ድ​ት​ወጡ በር​ግጥ ዕወቅ” አለው።

2 ዳዊ​ትም አን​ኩ​ስን፥ “አሁን አገ​ል​ጋ​ይህ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ንገ​ረው” አለው። አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን፥ “እን​ግ​ዲህ በዘ​መኑ ሁሉ ራሴን ጠባቂ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ” አለው።


ሳኦል የመ​ና​ፍ​ስት ጠሪን እንደ ጠየቀ

3 ሳሙ​ኤል ግን ሞቶ ነበር፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አል​ቅ​ሰ​ው​ለት ነበር፤ በከ​ተ​ማ​ውም በአ​ር​ማ​ቴም ቀብ​ረ​ውት ነበር። ሳኦ​ልም መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን ከም​ድር አጥ​ፍቶ ነበር።

4 ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ተሰ​ብ​ስ​በው መጡ፤ በሱ​ነ​ምም ሰፈሩ፤ ሳኦ​ልም እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ በጌ​ላ​ቡ​ሄም ሰፈሩ።

5 ሳኦ​ልም የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ጭፍራ ባየ ጊዜ ፈራ፤ ልቡም እጅግ ተን​ቀ​ጠ​ቀጠ።

6 ሳኦ​ልም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ልም አላ​ሚ​ዎች፥ ወይም በነ​ጋ​ሪ​ዎች፥ ወይም በነ​ቢ​ያት አል​መ​ለ​ሰ​ለ​ትም።

7 ሳኦ​ልም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “ወደ እር​ስዋ ሄጄ እጠ​ይቅ ዘንድ መና​ፍ​ስ​ትን የም​ት​ጠራ ሴት ፈል​ጉ​ልኝ” አላ​ቸው፤ ብላ​ቴ​ኖ​ቹም፥ “እነሆ፥ መና​ፍ​ስ​ትን የም​ት​ጠራ አን​ዲት ሴት በዓ​ይ​ን​ዶር አለች” አሉት።

8 ሳኦ​ልም መል​ኩን ለውጦ፥ ሌላ ልብ​ስም ለብሶ ሄደ፤ ሁለ​ትም ሰዎች ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ፤ በሌ​ሊ​ትም ወደ ሴቲቱ መጡ። ሳኦ​ልም፥ “እባ​ክሽ በመ​ና​ፍ​ስት አም​ዋ​ር​ቺ​ልኝ፤ የም​ል​ሽ​ንም አስ​ነ​ሽ​ልኝ” አላት።

9 ሴቲ​ቱም፥ “እነሆ፥ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን ከም​ድር እን​ዳ​ጠፋ ሳኦል ያደ​ረ​ገ​ውን ታው​ቃ​ለህ፤ ስለ​ምን እኔን ለማ​ስ​ገ​ደል ለነ​ፍሴ ወጥ​መድ ታደ​ር​ጋ​ለህ?” አለ​ችው።

10 ሳኦ​ልም ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በዚህ ነገር ክፉ አያ​ገ​ኝ​ሽም ብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማለ​ላት።

11 ሴቲ​ቱም፥ “ማንን ላስ​ነ​ሣ​ልህ?” አለ​ችው፤ እር​ሱም፥ “ሳሙ​ኤ​ልን አስ​ነ​ሽ​ልኝ” አላት።

12 ሴቲ​ቱም ሳሙ​ኤ​ልን ባየች ጊዜ በታ​ላቅ ድምፅ ጮኸች፤ ሴቲ​ቱም ሳኦ​ልን፥ “አንተ ሳኦል ስት​ሆን ለምን አታ​ለ​ል​ኸኝ?” ብላ ተና​ገ​ረ​ችው።

13 ንጉ​ሡም፥ “አት​ፍሪ ፤ ንገ​ሪኝ፤ ማንን አየሽ?” አላት። ሴቲ​ቱም፥ “አማ​ል​ክት ከም​ድር ሲወጡ አየሁ” አለ​ችው።

14 እር​ሱም፥ “ምን አየሽ?” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “ቀጥ ያለ ሽማ​ግሌ ሰው ከም​ድር ወጣ፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያም ተጐ​ና​ጽ​ፎ​አል” አለች። ሳኦ​ልም ሳሙ​ኤል እንደ ሆነ ዐወቀ፤ በፊ​ቱም ወደ ምድር ጐን​በስ ብሎ ሰገ​ደ​ለት።

15 ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን፥ “ለምን አወ​ክ​ኸኝ? ለም​ንስ አስ​ነ​ሣ​ኸኝ?” አለው። ሳኦ​ልም መልሶ፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ይወ​ጉ​ኛ​ልና እጅግ ተጨ​ን​ቄ​አ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእኔ ርቆ​አል፤ በነ​ቢ​ያት ወይም በሕ​ልም አላ​ሚ​ዎች አል​መ​ለ​ሰ​ል​ኝም፤ ስለ​ዚ​ህም የማ​ደ​ር​ገ​ውን ታስ​ታ​ው​ቀኝ ዘንድ ጠራ​ሁህ” አለው።

16 ሳሙ​ኤ​ልም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከራ​ቀህ፥ ወደ ባል​ን​ጀ​ራ​ህም ከተ​መ​ለሰ ለምን ትጠ​ይ​ቀ​ኛ​ለህ?

17 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቃሌ እንደ ተና​ገረ አድ​ር​ጎ​አል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥ​ት​ህን ከእ​ጅህ ነጥቆ ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ ለዳ​ዊት ሰጥ​ቶ​ታል።

18 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ህ​ምና፥ በአ​ማ​ሌ​ቅም ላይ ታላቅ የሆነ ቍጣ​ውን አላ​ደ​ረ​ግ​ህ​ምና ስለ​ዚህ ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ነገር አድ​ር​ጎ​ብ​ሃል።

19 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስ​ራ​ኤ​ልን ከአ​ንተ ጋር በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል፤ ነገም አን​ተና ከአ​ንተ ጋር ያሉ ልጆ​ችህ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጭፍራ ደግሞ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል።

20 ሳኦ​ልም በዚያ ጊዜ በቁ​መቱ ሙሉ በም​ድር ላይ ወደቀ፤ ከሳ​ሙ​ኤ​ልም ቃል የተ​ነሣ እጅግ ፈራ። በዚ​ያም ቀን ሁሉ፥ በዚ​ያም ሌሊት ሁሉ እን​ጀራ አል​በ​ላ​ምና ኀይል አል​ቀ​ረ​ለ​ትም።

21 ሴቲ​ቱም ወደ ሳኦል መጣች፤ እጅ​ግም ደን​ግጦ እንደ ነበር አይታ፥ “እነሆ፥ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ቃል​ህን ሰማሁ፤ ነፍ​ሴ​ንም በእጄ ጣልሁ፤ የነ​ገ​ር​ኸ​ኝ​ንም ቃል ሰማሁ።

22 አሁን እን​ግ​ዲህ አንተ ደግሞ የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ቃል እን​ድ​ት​ሰማ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ በፊ​ት​ህም ቁራሽ እን​ጀራ ላኑ​ር​ልህ፤ መን​ገ​ድም ትሄ​ዳ​ለ​ህና ትበ​ረታ ዘንድ ብላ” አለ​ችው።

23 እርሱ ግን፥ “አል​በ​ላም” ብሎ እንቢ አለ፤ ነገር ግን ብላ​ቴ​ኖ​ቹና ሴቲቱ አስ​ገ​ደ​ዱት፤ ቃላ​ቸ​ው​ንም ሰማ፤ ከም​ድ​ርም ተነ​ሥቶ በአ​ልጋ ላይ ተቀ​መጠ።

24 ለሴ​ቲ​ቱም የሰባ ጥጃ በቤት ነበ​ራት፤ ፈጥና አረ​ደ​ችው፤ ዱቄ​ቱ​ንም ወስዳ ለወ​ሰ​ችው፤ ቂጣም እን​ጀራ አድ​ርጋ ጋገ​ረ​ችው።

25 በሳ​ኦ​ልና በብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም ፊት አቀ​ረ​በ​ችው፤ በል​ተ​ውም ተነሡ፤ በዚ​ያም ሌሊት ሄዱ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos