የአሞንም ልጆች የዳዊት ወገኖች እንደ አፈሩ ባዩ ጊዜ፥ የአሞን ልጆች ልከው ከቤትሮዖብ ሶርያውያንና ከሱባ ሶርያውያን ሃያ ሺህ እግረኞችን፥ ከአማሌቅ ንጉሥም አንድ ሺህ ሰዎችን፥ ከአስጦብም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ።
ኤርምያስ 40:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የናታንያ ልጅ እስማኤል፥ የቃርሔም ልጆች ዮሐናንና ዮናታን፥ የተንሁሜትም ልጅ ሠራያ፥ የነጦፋዊውም የዮፌ ልጆች፥ የመከጢ ልጅ አዛንያም ከሰዎቻቸው ጋር ወደ ጎዶልያስ ወደ መሴፋ መጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ምጽጳ፣ ጎዶልያስ ዘንድ መጡ፤ የናታንያ ልጅ እስማኤል፣ የቃሬያ ልጆች ዮሐናንና ዮናታን፣ የተንሑሜት ልጅ ሠራያ፤ የነጦፋዊው የዮፌ ልጆች፣ የማዕካታዊ ልጅ ያእዛንያን ሰዎቻቸውም ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የናታንያ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬያም ልጆች ዮሐናንና ዮናታን፥ የተንሑሜትም ልጅ ሠራያ፥ የነጦፋዊውም የዮፌ ልጆች የማዕካታዊውም ልጅ ያእዛንያ ከሰዎቻቸው ጋር ወደ ጎዶልያስ ወደ ምጽጳ መጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የነታንያ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬሐ ልጆች ዮሐናንና ዮናታን፥ የታንሑሜት ልጅ ሠራያ፥ ከነጦፋ የዔፋይ ልጆች፥ ከማዕካም የዛንያ ከሰዎቻቸው ሁሉ ጋር በምጽጳ ወደሚገኘው ወደ ገዳልያ መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቃሬያም ልጅ ዮሐናንና ዮናታን፥ የተንሑሜትም ልጅ ሠራያ፥ የነጦፋዊውም የዮፌ ልጆች የማዕካታዊውም ልጅ ያእዛንያ ከሰዎቻቸው ጋር ወደ ጎዶልያስ ወደ ምጽጳ መጡ። |
የአሞንም ልጆች የዳዊት ወገኖች እንደ አፈሩ ባዩ ጊዜ፥ የአሞን ልጆች ልከው ከቤትሮዖብ ሶርያውያንና ከሱባ ሶርያውያን ሃያ ሺህ እግረኞችን፥ ከአማሌቅ ንጉሥም አንድ ሺህ ሰዎችን፥ ከአስጦብም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ።
የአሞንም ልጆች ወጥተው በበሩ መግቢያ ፊት ለፊት ይዋጉ ጀመሩ፤ የሱባና የሮዖብ ሶርያውያን፥ የአስጦብና የአማሌቅም ሰዎች ለብቻቸው በሰፊ ሜዳ ላይ ነበሩ።
የሠራዊቱም አለቆች ሁሉ ሰዎቻቸውም፥ የናታንዩ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬያን ልጅ ዮሐናን፥ የነጦፋዊውም የተንሑሜት ልጅ ሴሪያ፥ የማዕካታዊው ልጅ አዛንያ፥ ሰዎቻቸውም የባቢሎን ንጉሥ ጎዶልያን እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ ወደ ጎዶልያ ወደ መሴፋ መጡ።
በሰባተኛው ወር ግን የመንግሥት ዘር የነበረ የኤልሴማ ልጅ የናታንዩ ልጅ እስማኤል መጣ፤ ከእርሱም ጋር ዐሥር ሰዎች ነበሩ፤ ጎዶልያንም መታው፤ ሞተም፤ ከእርሱም ጋር በመሴፋ የነበሩትን አይሁድንና ከለዳውያንንም ገደላቸው።
ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከሠራያ፥ ከሮሃልያ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበላሳን፥ ከመሴፋር፥ ከበጎዋይ፥ ከሬሁም፥ ከበዓና ጋር መጡ። የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤
በሞዓብና በአሞንም ልጆች መካከል፥ በኤዶምያስም፥ በምድርም ሁሉ ላይ የነበሩ አይሁድ ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የይሁዳን ቅሬታ እንዳስቀረ፥ የሳፋንንም ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በላያቸው እንደ ሾመው ሰሙ።
“የአሞን ልጆች ንጉሥ በኣሊስ ይገድልህ ዘንድ የናታንያን ልጅ እስማኤልን እንደ ላከ ታውቃለህን?” አሉት። የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን አላመናቸውም።
የቃርሔም ልጅ ዮሐናን፥ “እባክህ፥ ልሂድ፤ ማንም ሳያውቅ የናታንያን ልጅ እስማኤልን ልግደለው፤ ወደ አንተ የተሰበሰቡ አይሁድ ሁሉ እንዲበተኑ፥ የይሁዳም ቅሬታ እንዲጠፋ ነፍስህን ስለ ምን ይገድላል?” ብሎ በመሴፋ በቈይታ ለጎዶልያስ ተናገረ።
ኤርምያስም የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ወደ አለበት ወደ መሴፋ ሄደ፤ ከእርሱም ጋር በሀገሩ ውስጥ በቀሩት ሕዝብ መካከል ተቀመጠ።
እንዲህም ሆነ፤ በሰባተኛው ወር ከመንግሥት ወገንና ከንጉሡ ዋና ዋና አለቆች አንዱ የኤሊሳማ ልጅ የናታንያ ልጅ እስማኤል ከዐሥር ሰዎች ጋር ወደ መሴፋ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ መጣ፤ በዚያም በመሴፋ በአንድ ላይ እንጀራ በሉ።
የቃርሔም ልጅ ዮሐናን፥ ከእርሱም ጋር የነበሩ የጭፍራ አለቆች ሁሉ የናታንያ ልጅ እስማኤል ያደረገውን ክፋት ሁሉ ሰሙ።
የናታንያም ልጅ እስማኤል ከእርሱም ጋር የነበሩት ዐሥሩ ሰዎች ተነሥተው የሳፋንን ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሰይፍ መቱ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በሀገሩ ላይ የሾመውን ገደሉ።
የጭፍራ አለቆችም ሁሉ፥ የቃርሔም ልጅ ዮሐናን፥ የሐናንያ ልጅ ኢዛንያስ ሕዝቡም ሁሉ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ መጡ።
የቃርሔምንም ልጅ ዮሐናንን፥ ከእርሱም ጋር የነበሩትን የጭፍራ አለቆች ሁሉ፥ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሕዝቡንም ሁሉ ጠራ፤
የኢዮስያስ ልጅ ኣዛርያስ፥ የቃርሔም ልጅ ዮሐናን፥ ትዕቢተኞችም ሰዎች ሁሉ ኤርምያስን፥ “ሐሰት ተናግረሃል፤ አምላካችን እግዚአብሔር፦ በዚያ ትቀመጡ ዘንድ ወደ ግብፅ አትግቡ ብሎ አልላከህም፤
የቃርሔም ልጅ ዮሐናን፥ የጭፍራ አለቆችም ሁሉ በይሁዳ ምድር ለመቀመጥ ከተሰደዱባቸው ከአሕዛብ ሁሉ የተመለሱትን የይሁዳን ቅሬታ ሁሉ ወሰዱ።
የምናሴ ልጅ ኢያዕር እስከ ጌርጋሴና እስከ መካቲ ዳርቻ ድረስ የአርጎብን አውራጃ ሁሉ ወሰደ፤ ይህችንም የባሳንን ምድር እስከዚች ቀን ድረስ በስሙ አውታይ ኢያዕር ብሎ ጠራ።
የአርሞንኤምን ተራራ፥ ካሴኪን፥ ባሳንንም ሁሉ እስከ ጌርጌሲና እስከ መከጢ ዳርቻ፥ የገለዓድንም እኩሌታ እስከ ሐሴቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ዳርቻ ድረስ የገዛው የባሳን ንጉሥ ዐግ፤