ነህምያ 7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 እንዲህም ሆነ፤ ቅጥሩ ከተሠራ በኋላ፥ ሳንቃዎቹን አቆምሁ፤ በረኞቹንና መዘምራኑን፥ ሌዋውያኑንም ሾምሁ፤ 2 ወንድሜን ሃናኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያንም በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኋቸው፤ እርሱም እውነተኛ ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ። 3 እኔም፥ “ፀሐይ እስኪሞቅ ድረስ የኢየሩሳሌም በሮች አይከፈቱ፤ እነርሱም ቆመው ሳሉ ደጆቹን ይዝጉ፤ ይቈልፉም፤ ከኢየሩሳሌምም ሰዎች አንዳንዱን በየተራው፥ አንዳንዱንም በየቤቱ አንጻር ጠባቂዎችን አስቀምጡ” አልኋቸው። 4 ከተማዪቱም ሰፊና ታላቅ ነበረች፤ በውስጥዋ የነበሩ ሕዝብ ግን ጥቂቶች ነበሩ፤ ቤቶቹም ገና አልተሠሩም ነበር። ከስደት የተመለሱ አይሁድ ስም ዝርዝር 5 እግዚአብሔርም ታላላቆቹንና ሹሞቹን፥ ሕዝቡንም ሰብስቤ በየትውልዳቸው እቈጥራቸው ዘንድ ልቤን አነሣሣ፤ አስቀድመው የመጡትንም ሰዎች የትውልድ መጽሐፋቸውን አገኘሁ፤ በእርሱም እንደዚህ ተጽፎ አገኘሁ። 6 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የሀገር ልጆች እነዚህ ናቸው። 7 ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከአዛርያስ፥ ከረዓምያ፥ ከሄሜኔስ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበልሰማ፥ ከሚስፌሬት፥ ከዕዝራ፥ ከበጉዋይ፥ ከነሑም፥ ከበዓና፥ ከመስፈር ጋር መጡ። ከእስራኤልም ሕዝብ የወንዶች ቍጥር ይህ ነው፥ 8 የፋሮስ ልጆች ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሰባ ሁለት። 9 የሰፋጥያስ ልጆች ሦስት መቶ ሰባ ሁለት። 10 የኤራ ልጆች ስድስት መቶ አምሳ ሁለት። 11 ከኢያሱና ከኢዮአብ ልጆች የሆኑ የፈሐት ሞዓብ ልጆች ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ዐሥራ ስምንት። 12 የኤላም ልጆች ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። 13 የዘቱዕ ልጆች ስምንት መቶ አርባ አምስት። 14 የዘካይ ልጆች ሰባት መቶ ስድሳ። 15 የበኑይ ልጆች ስድስት መቶ አርባ ስምንት። 16 የቤባይ ልጆች ስድስት መቶ ሃያ ስምንት። 17 የአዝጌድ ልጆች ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ሃያ ሁለት። 18 የአዶኒቃም ልጆች ስድስት መቶ ስድሳ ሰባት። 19 የበጉዋይ ልጆች ሁለት ሺህ ስድሳ ሰባት። 20 የዓዴን ልጆች ስድስት መቶ አምሳ አምስት። 21 የሕዝቅያስ ወገን የአጤር ልጆች ዘጠና ስምንት። 22 የሐሱም ልጆች ሦስት መቶ ሃያ ስምንት። 23 የቤሳይ ልጆች ሦስት መቶ ሃያ አራት። 24 የሐሪፍ ልጆች መቶ ዐሥራ ሁለት። 25 የገባዖን ልጆች ዘጠና አምስት። 26 የቤተ ልሔምና የነጦፍያ ሰዎች መቶ ሰማንያ ስምንት። 27 የዓናቶት ሰዎች መቶ ሃያ ስምንት። 28 የቤትአዝሞት ሰዎች አርባ ሁለት። 29 የቂርያትይዓሪምና የቃፌር፥ የቤሮትም ሰዎች ሰባት መቶ አርባ ሦስት። 30 የሐራማና የገቢኣ ሰዎች ስድስት መቶ ሃያ አንድ። 31 የማኬማስ ሰዎች መቶ ሃያ ሁለት። 32 የቤቴልና የጋይ ሰዎች መቶ ሃያ ሦስት። 33 የናብያ ሰዎች መቶ አምሳ ሁለት። 34 የኤላም ሰዎች ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። 35 የኤራም ልጆች ሦስት መቶ ሃያ። 36 የኢያሪኮ ልጆች ሦስት መቶ አርባ አምስት። 37 የሎድና ሐዲድ የሐኖም ልጆች ሰባት መቶ ሃያ አንድ። 38 የሴናዓ ልጆች ሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ። 39 ካህናቱ ከኢያሱ ወገን፦ የዮዳሔ ልጆች ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት። 40 የኤሜር ልጆች ሺህ አምሳ ሁለት። 41 የፋስኮር ልጆች ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት። 42 የሐራም ልጆች ሺህ ዐሥራ ሰባት። 43 ሌዋውያኑም ከሆዳይዋ ወገን የኢያሱና የቀድምኤል ልጆች ሰባ አራት። 44 መዘምራኑ የአሳፍ ልጆች መቶ አርባ ስምንት። 45 በረኞቹ የሴሎምያ ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጤልማና ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሶባይ ልጆች መቶ አርባ ስምንት። 46 ናታኒም የሲአ ልጆች፥ የሐሡፋ ልጆች፥ የጠብዓት ልጆች፤ 47 የቄራስ ልጆች፥ የአሲያ ልጆች፥ የፋዶን ልጆች፤ 48 የልባና ልጆች፥ የአጋባ ልጆች፥ የሰልማይ ልጆች፤ 49 የሐናን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፥ የጋኤር ልጆች፤ 50 የርአያ ልጆች፥ የረአሶን ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፤ 51 የጋሴም ልጆች፥ የኡዚ ልጆች፥ የፋሴሓ ልጆች፤ 52 የቤሳይ ልጆች፥ የምዑናውያን ልጆች፥ የኔፋሴስም ልጆች፤ 53 የበቅቡቅ ልጆች፥ የሐቀፋ ልጆች፥ የሐሩር ልጆች፤ 54 የበስሎት ልጆች፥ የምሒዳ ልጆች፥ የሐርሳ ልጆች፤ 55 የበርቆስ ልጆች፥ የሲሣራ ልጆች፥ የታማህ ልጆች፥ 56 የነስያ ልጆች፥ የሐጤፋ ልጆች። 57 የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች፤ የሦጠይ ልጆች፥ የሰፋሬት ልጆች፥ የፈሪዳ ልጆች፥ 58 የየዕላ ልጆች፥ የደርቆን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፤ 59 የሰፋጥያስ ልጆች፥ የሐጢል ልጆች፥ የፈከራት ልጆች፥ የሰባይም ልጆች፥ የአሞን ልጆች። 60 ናታኒም ሁሉና የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ። 61 ከቲልሜል፥ ከቲላሬስ፥ ከኪሩብ፥ ከአዶን፥ ከኢሜር የወጡ እነዚህ ናቸው፤ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤቶችና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ያስታውቁ ዘንድ አልቻሉም፤ 62 የዳላያ ልጆች፥ የጦብያ ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች ስድስት መቶ አርባ ሁለት። 63 ከካህናቱም የአብያ ልጆች፥ የአቆስ ልጆች፥ ከገለዓዳዊው ከቤርዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ፥ በስሙም የተጠራ የቤርዜሊ ልጆች። 64 እነዚህ በትውልድ መጽሐፍ ትውልዳቸውን ፈለጉ፤ ነገር ግን አልተገኘም፤ ከክህነትም ተከለከሉ። 65 ሐቴርሰታም፥ “በኡሪምና በቱሚም የሚፈርድ ካህን እስኪነሣ ድረስ ከተቀደሰው ነገር አትበሉም” አላቸው። 66 ጉባኤውም ሁሉ አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ ነበሩ፤ 67 ይኸውም ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ከነበሩ ከሎሌዎቻቸውና ከገረዶቻቸው ሌላ ሁለት መቶም አርባ አምስት ወንዶች መዘምራንና ሴቶች መዘምራት ነበሩአቸው። 68 ፈረሶቻቸውም ሰባት መቶ ሠላሳ ስድስት፥ በቅሎዎቻቸውም ሁለት መቶ አርባ አምስት፤ 69 ግመሎቻቸውም አራት መቶ ሠላሳ አምስት፥ አህዮቻቸውም ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ ነበሩ። 70 ከአባቶች ቤቶች አለቆችም ስለ ሥራው ስጦታ ሰጡ። ሐቴርሰታም አንድ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ አምሳም ድስቶች፥ አምስት መቶ ሠላሳም የካህናት ልብስ በቤተ መዛግብት ውስጥ ሰጠ። 71 ከአባቶች ቤቶች አለቆችም ዐያሌዎቹ በሥራው ቤተ መዛግብት ውስጥ ሃያ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ ሁለት ሺህ ሁለት መቶም ምናን ብር ሰጡ። 72 የቀሩትም ሕዝብ የሰጡት ሃያ ሺህ የወርቅ ዳሪክና ሁለት ሺህ ምናን ብር፥ ስድሳ ሰባትም የካህናት ልብስ ነበረ። 73 ካህናቱና ሌዋውያኑም፥ በረኞቹና መዘምራኑም፥ ከሕዝቡም ዐያሌዎቹ፥ ናታኒምም፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ። |