Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ዕዝራ 2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ወደ ሀገ​ራ​ቸው የተ​መ​ለሱ የአ​ይ​ሁድ ስም ዝር​ዝር
( ነህ. 7፥4-73 )

1 የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወደ ባቢ​ሎን ከማ​ረ​ካ​ቸው ምር​ኮ​ኞች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየ​ከ​ተ​ማ​ቸው የተ​መ​ለ​ሱት የሀ​ገር ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።

2 ከዘ​ሩ​ባ​ቤል፥ ከኢ​ያሱ፥ ከነ​ህ​ምያ፥ ከሠ​ራያ፥ ከሮ​ሃ​ልያ፥ ከመ​ር​ዶ​ክ​ዮስ፥ ከበ​ላ​ሳን፥ ከመ​ሴ​ፋር፥ ከበ​ጎ​ዋይ፥ ከሬ​ሁም፥ ከበ​ዓና ጋር መጡ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤

3 የፋ​ሮስ ልጆች ሁለት ሺህ መቶ ሰባ ሁለት።

4 የሰ​ፋ​ጥ​ያስ ልጆች ሦስት መቶ ሰባ ሁለት።

5 የኤ​ራስ ልጆች ሰባት መቶ ሰባ አም​ስት።

6 ከያ​ሱ​ኤና ከዮ​አብ ልጆች የሆ​ኑት የፈ​ሐት ሞዓብ ልጆች ሁለት ሺህ ስም​ንት መቶ ዐሥራ ሁለት።

7 የኤ​ላም ልጆች ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት።

8 የዛ​ቱዕ ልጆች ዘጠኝ መቶ አርባ አም​ስት።

9 የዘ​ካይ ልጆች ሰባት መቶ ስድሳ።

10 የባኒ ልጆች ስድ​ስት መቶ አርባ ሁለት።

11 የቢ​ባይ ልጆች ስድ​ስት መቶ ሃያ ሦስት።

12 የዓ​ዝ​ጋድ ልጆች ሺህ ሁለት መቶ ሃያ ሁለት።

13 የአ​ዶ​ኒ​ቃም ልጆች ስድ​ስት መቶ ስድሳ ስድ​ስት።

14 የበ​ጕ​ዋይ ልጆች ሁለት ሺህ አምሳ ስድ​ስት።

15 የዓ​ዲን ልጆች አራት መቶ አምሳ አራት።

16 ከሕ​ዝ​ቅ​ያስ ወገን የአ​ጤር ልጆች ዘጠና ስም​ንት።

17 የቤ​ሳይ ልጆች ሦስት መቶ ሃያ ሦስት።

18 የዮራ ልጆች መቶ ዐሥራ ሁለት።

19 የሐ​ሱም ልጆች ሁለት መቶ ሃያ ሦስት።

20 የጋ​ቤር ልጆች ዘጠና አም​ስት።

21 የቤተ ልሔም ልጆች መቶ ሃያ ሦስት።

22 የነ​ጦፋ ልጆች አምሳ ስድ​ስት።

23 የዓ​ና​ቶት ልጆች መቶ ሃያ ስም​ንት።

24 የዓ​ዝ​ሞት ልጆች አርባ ሁለት።

25 የቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪ​ምና የቃ​ፌር፥ የብ​ኤ​ሮ​ትም ልጆች ሰባት መቶ አርባ ሦስት።

26 የራ​ማና የጋ​ባዕ ልጆች ስድ​ስት መቶ ሃያ አንድ።

27 የመ​ኪ​ማስ ሰዎች መቶ ሃያ ሁለት።

28 የቤ​ቴ​ልና የጋይ ሰዎች ሁለት መቶ ሃያ ሦስት።

29 የና​ባው ልጆች አምሳ ሁለት።

30 የመ​ጌ​ባስ ልጆች መቶ አምሳ ስድ​ስት።

31 የኤ​ላ​ማር ልጆች ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት።

32 የኤ​ላም ልጆች ሦስት መቶ ሃያ።

33 የሎድ፥ የሐ​ዲ​ድና የኦ​ኖም ልጆች ሰባት መቶ ሃያ አም​ስት።

34 የኢ​ያ​ሪኮ ልጆች ሦስት መቶ አርባ አም​ስት።

35 የሴ​ዓ​ናህ ልጆች ሦስት ሺህ ስድ​ስት መቶ ሠላሳ።

36 ካህ​ናቱ ከኢ​ያሱ ወገን የዮ​ዳኤ ልጆች ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት።

37 የኢ​ሜር ልጆች ሺህ አምሳ ሁለት።

38 የፋ​ስ​ኮር ልጆች ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት።

39 የኤ​ረም ልጆች ሺህ ዐሥራ ሰባት።

40 ሌዋ​ው​ያኑ፤ ከሁ​ድያ ልጆች ወገን የኢ​ዮ​ስ​ስና የቀ​ዳ​ም​ሔል ልጆች ሰባ አራት።

41 መዘ​ም​ራኑ የአ​ሳፍ ልጆች መቶ ሃያ ስም​ንት።

42 የበ​ረ​ኞች ልጆች፥ የሰ​ሎም ልጆች፥ የአ​ጤር ልጆች፥ የጤ​ል​ሞን ልጆች፥ የዓ​ቁብ ልጆች፥ የሐ​ጢጣ ልጆች፥ የሰ​በ​ዋይ ልጆች ሁሉ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ።

43 ናታ​ኒም፤ የሲሓ ልጆች፥ የሐ​ሡፊ ልጆች፥ የጠ​ብ​ዖት ልጆች፤

44 የቃ​ዴስ ልጆች፥ የሲ​ሔል ልጆች፥ የፋ​ዶን ልጆች፤

45 የል​ባና ልጆች፥ የአ​ጋባ ልጆች፥ የዓ​ቁብ ልጆች፥

46 የአ​ጋብ ልጆች፥ የሰ​ላሚ ልጆች፥ የሐ​ናን ልጆች፤

47 የጋ​ዱል ልጆች፥ የጋ​ሐር ልጆች፥ የራ​እያ ልጆች፤

48 የረ​አ​ሶን ልጆች፥ የኒ​ቆዳ ልጆች፥ የጋ​ሴም ልጆች፤

49 የዓ​ዝ​ያት ልጆች፥ የፋ​ሒስ ልጆች፥ የባሲ ልጆች፤

50 የአ​ሲና ልጆች፥ የም​ዑ​ና​ው​ያን ልጆች፥ የና​ፌ​ሶን ልጆች፤

51 የበ​ቅ​ቡቅ ልጆች፥ የሐ​ቁፋ ልጆች፥ የሐ​ር​ሑር ልጆች፤

52 የበ​ስ​ሎት ልጆች፥ የማ​ሁድ ልጆች፥ የአ​ሪስ ልጆች፤

53 የበ​ር​ቆስ ልጆች፥ የሲ​ሣራ ልጆች፥ የቴማ ልጆች፥

54 የን​ስያ ልጆች፥ የአ​ጡፋ ልጆች።

55 የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ልጆች፤ የሳጢ ልጆች፥ የሰ​ፌ​ርታ ልጆች፥ የፋ​ዱ​ርሓ ልጆች፤

56 የኢ​ያ​ሔል ልጆች፥ የደ​ር​ቆን ልጆች፥ የጌ​ዴል ልጆች፤

57 የሰ​ፋ​ጥ​ያስ ልጆች፥ የአ​ጤል ልጆች፥ የፎ​ኬ​ርት ልጆች፥ የሐ​ፂ​ባ​ይም ልጆች፥ የአሚ ልጆች።

58 እነ​ዚህ ናታ​ኒም ሁሉና የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ።

59 ከቲ​ል​ሜላ፥ ከቴ​ላ​ርሳ፥ ከክ​ሩብ፥ ከሐ​ዳን፥ ከኤ​ሜር የወጡ እነ​ዚህ ነበሩ፤ ነገር ግን የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ቤቶ​ችና ዘራ​ቸ​ውን ወይም ከእ​ስ​ራ​ኤል ወገን መሆ​ና​ቸ​ውን ያስ​ታ​ውቁ ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤

60 የዳ​ላያ ልጆች፥ የጦ​ብያ ልጆች፥ የኒ​ቆዳ ልጆች፥ ስድ​ስት መቶ አምሳ ሁለት ነበሩ።

61 ከካ​ህ​ና​ቱም ልጆች፤ የአ​ብያ ልጆች፥ የአ​ቆስ ልጆች፥ ከገ​ለ​ዓ​ዳ​ዊው ከቤ​ር​ዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ፥ በስ​ማ​ቸ​ውም የተ​ጠራ የቤ​ር​ዜሊ ልጆች።

62 እነ​ዚህ በት​ው​ልድ መጽ​ሐፍ ትው​ል​ዳ​ቸ​ውን ፈለጉ፤ ነገር ግን አል​ተ​ገ​ኘም፤ ከክ​ህ​ነ​ትም ተከ​ለ​ከሉ።

63 ሐቲ​ር​ሰ​ስ​ታም፥ “በኡ​ሪ​ምና በቱ​ሚም የሚ​ፈ​ርድ ካህን እስ​ኪ​ነሣ ድረስ ከቅ​ዱሰ ቅዱ​ሳኑ አት​በ​ሉም” አላ​ቸው።

64 ጉባ​ኤው ሁሉ አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ ነበሩ።

65 ይኸ​ውም ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ከነ​በሩ ከሎ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውና ከገ​ረ​ዶ​ቻ​ቸው ሌላ ሁለት መቶ ወን​ዶች መዘ​ም​ራ​ንና ሴቶች መዘ​ም​ራ​ትም ነበ​ሩ​አ​ቸው።

66 ፈረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ሰባት መቶ ሠላሳ ስድ​ስት፥ በቅ​ሎ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ሁለት መቶ አርባ አም​ስት፥

67 ግመ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም አራት መቶ ሠላሳ አም​ስት፥ አህ​ዮ​ቻ​ቸ​ውም ስድ​ስት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ ነበሩ።

68 በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወዳ​ለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በመጡ ጊዜ ከአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች አያ​ሌ​ዎች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በስ​ፍ​ራው ይሠ​ሩት ዘንድ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ሰጡ።

69 ስድሳ አንድ ሺህም የወ​ርቅ ዳሪክ፥ አም​ስት ሺህም ምናን ብር፥ አንድ መቶም የካ​ህ​ናት ልብስ እንደ ችሎ​ታ​ቸው ወደ ሥራው ቤተ መዛ​ግ​ብት አቀ​ረቡ።

70 ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ ከሕ​ዝ​ቡም አያ​ሌ​ዎች፥ መዘ​ም​ራ​ኑና በረ​ኞ​ቹም፥ ናታ​ኒ​ምም በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ተቀ​መጡ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos