የእስራኤል አምላክ ተናገረ፤ የእስራኤልም ጠባቂ በምሳሌ እንዲህ አለኝ፦ “እግዚአብሔርን መፍራት ታጸኑ ዘንድ፥ በሰዎች መካከል ተናገርሁ፥”
ኤርምያስ 22:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ፤ የተነጠቀውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ፤ መጻተኛውንና ድሃአደጉን፥ ባልቴቲቱንም አትበድሉ፤ አታምፁባቸውም፤ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን አታፍስሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ፍትሕንና ጽድቅን አድርጉ፤ የተበዘበዘውን ከጨቋኙ እጅ አድኑት፤ መጻተኛውን፣ ወላጅ የሌለውንና መበለቲቱን አትበድሉ፤ አትግፏቸውም፤ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደም አታፍስሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ይላል፦ ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ የተበዘበዘውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ፤ መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም አትበድሉ፥ አታምፁባቸውም፥ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን አታፍስሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔ እግዚአብሔር ትክክለኛ ፍርድና እውነት የሆነውን ነገር እንድታደርጉ አዛችኋለሁ፤ አንዱ ሌላውን በመቀማት ግፍ እንዳይሠራ ጠብቁ፤ መጻተኞችን፥ እናትና አባት የሞቱባቸውን ልጆችና፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በመጨቈን አታንገላቱ፤ በዚህም በተቀደሰ ስፍራ የንጹሕ ሰው ደም አታፍስሱበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ የተበዘበዘውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ፥ መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም አትበድሉ፥ አታምፁባቸውም፥ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን አታፍስሱ። |
የእስራኤል አምላክ ተናገረ፤ የእስራኤልም ጠባቂ በምሳሌ እንዲህ አለኝ፦ “እግዚአብሔርን መፍራት ታጸኑ ዘንድ፥ በሰዎች መካከል ተናገርሁ፥”
አለቆችሽ ዐመፀኞችና የሌቦች ባልንጀሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወድዳሉ፤ ፍርድንም ሊያጣምሙ ይፈልጋሉ፤ ለሙት ልጅ አይፈርዱም፤ የመበለቲቱንም አቤቱታ አያዳምጡም።
ይህን ጾም የመረጥሁ አይደለም ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን የበደልን እስራት ፍታ፤ ጠማማውን ሁሉ አቅና፤ የተጨነቀውንም ሁሉ አድን፤ የዐመፃ ደብዳቤንም ተው።
ለተራበውም እንጀራህን አጥግበው፤ ድሆችን ወደ ቤትህ አስገብተህ አሳድራቸው፤ የተራቈተውንም ብታይ አልብሰው፤ ከሥጋ ዘመድህ አትሸሽግ።
ትተውኛልና፥ ይህንም ስፍራ እንግዳ አድርገውታልና፥ እነርሱና አባቶቻቸውም ለማያውቋቸው ለሌሎች አማልክት ዐጥነዋልና፥ የይሁዳም ነገሥታት ይህን ስፍራ በንጹሓን ደም ሞልተዋልና፥
የዳዊት ቤት ሆይ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይነድድና ማንም ሳያጠፋው እንዳያቃጥል፥ በማለዳ ፍርድን አድርጉ፤ የተነጠቀውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ።
እነሆ ዐይንህና ልብህ መልካም አይደለም፤ ነገር ግን ለቅሚያ፥ ንጹሕ ደምንም ለማፍሰስ፥ ግድያንና ግፍንም ለመሥራት ብቻ ነው።”
አለቆቹና ሕዝቡም ሁሉ ለካህናትና ለነቢያተ ሐሰት፥ “ይህ ሰው በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ተናግሮናልና ሞት አይገባውም” አሉ።
ነገር ግን፦ ቃሌን ስሙ፤ እኔ አምላክ እሆናችኋለሁ፤ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤ መልካምም ይሆንላችሁ ዘንድ ባዘዝኋችሁ መንገድ ሂዱ ብዬ በዚህ ነገር አዘዝኋቸው።
ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን፥ ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኘኝ ይህ ነውና፥” ይላል እግዚአብሔር።
ድሀውንና ችግረኛውን ቢያስጨንቅ፥ ቢቀማም፥ መያዣውንም ባይመልስ፥ ዐይኖቹንም ወደ ጣዖታት ቢያነሣ፥ ርኩስንም ነገር ቢያደርግ፥
ሰውንም ባያስጨንቅ፥ ለባለ ዕዳም መያዣውን ቢመልስ፥ ፈጽሞም ባይቀማ፥ ከእንጀራውም ለተራበ ቢሰጥ፥ የተራቈተውንም ከልብሱ ቢያለብስ፤
በአንቺ ውስጥ አባትንና እናትን አቃለሉ፤ በመካከልሽ በመጻተኛው ላይ በደልን አደረጉ፤ በአንቺ ውስጥ ድሀ አደጉንና መበለቲቱን አስጨነቁ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የእስራኤል አለቆች ሆይ! ይብቃችሁ፤ ግፍንና ዐመፅን አስወግዱ፤ ፍርድንና ጽድቅንም አድርጉ፤ ቅሚያችሁን ከሕዝቤ ላይ አርቁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
በሀገራቸው ንጹሑን ደም አፍስሰዋልና በይሁዳ ልጆች ላይ ስለ አደረጉት ግፍ ግብፅ ምድረ በዳ፥ ኤዶምያስም በረሃ ይሆናል።
ክፉውን ጥሉ፤ መልካሙንም ውደዱ፤ በበሩም አደባባይ ፍርድን አጽኑ፤ ምናልባት ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር ለዮሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆናል።
አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፥ ከዚህም ጋር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።
ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?
ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር።
“የመጻተኛውንና የድሃ-አደጉን፥ የመበለቲቱንም ፍርድ አታጣምምባቸው፤ የመበለቲቱንም ልብስ ለመያዣ አትውሰድባት።
“ማንም ሰው ከእስራኤል ልጆች ከወንድሞቹ ሰውን አፍኖ ሲሰርቅና ሲሸጥ ቢገኝ ያን የሰረቀውን ሰው ይግደሉት፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከላችሁ አርቁ።
ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።