Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 22:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እና​ንተ በግ​ብፅ ምድር ስደ​ተ​ኞች ነበ​ራ​ች​ሁና ስደ​ተ​ኛ​ውን አት​በ​ድ​ሉት፤ ግፍም አታ​ድ​ር​ጉ​በት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 “መጻተኛውን አትበድሉት ወይም አታስጨንቁት፤ እናንተ በግብጽ መጻተኛ ነበራችሁና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 መበለቲቱንና ድሀ አደጉን አታስጨንቁአቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “እናንተም በግብጽ ምድር መጻተኞች ስለ ነበራችሁ መጻተኛውን በመጨቈን አታጒላሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እናንተ በግብፅ ምድር ስደተኞች ነበራችሁና ስደተኛውን አትበድለው፥ ግፍም አታድርግበት።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 22:21
22 Referencias Cruzadas  

እና​ንተ በግ​ብፅ ሀገር ስደ​ተ​ኞች ነበ​ራ​ች​ሁና ስለ​ዚህ ስደ​ተ​ኛ​ውን ውደዱ።


በስ​ደ​ተ​ኛው ግፍ አታ​ድ​ርጉ፤ እና​ንተ በግ​ብፅ ምድር ስደ​ተ​ኞች ስለ ነበ​ራ​ችሁ የስ​ደ​ተኛ ነፍስ እን​ዴት እንደ ሆነች ዐው​ቃ​ች​ኋ​ልና።


“በሀ​ገ​ራ​ችሁ ውስጥ እን​ግዳ ከእ​ና​ንተ ጋር ቢቀ​መጥ ግፍ አታ​ድ​ር​ጉ​በት።


መጻተኛውንና ችግረኛውን አትበድሉ፣ ከእናንተም ማንም በወንድሙ ላይ ክፉውን ነገር በልቡ አያስብ።


ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


መጻ​ተ​ኛ​ው​ንና ድሃ​አ​ደ​ጉን፥ መበ​ለ​ቲ​ቱ​ንም ባት​ገፉ፥ በዚ​ህም ስፍራ ንጹሕ ደምን ባታ​ፈ​ስሱ፥ ክፉም ሊሆ​ን​ባ​ችሁ እን​ግ​ዶ​ችን አማ​ል​ክት ባት​ከ​ተሉ፤


“ኤዶ​ማ​ዊዉ ወን​ድ​ምህ ነውና አት​ጸ​የ​ፈው፤ ግብ​ፃ​ዊ​ዉ​ንም በሀ​ገሩ ስደ​ተኛ ነበ​ር​ህና አት​ጸ​የ​ፈው።


“ከአ​ንተ ጋር ያለው ወን​ድ​ምህ ቢደ​ኸይ፥ እጁም በአ​ንተ ዘንድ ቢደ​ክም እንደ እን​ግ​ዳና እንደ መጻ​ተኛ ትረ​ዳ​ዋ​ለህ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ይኑር።


“ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ሁህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እኔ ነኝ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን አድ​ርጉ፤ የተ​ነ​ጠ​ቀ​ው​ንም ከአ​ስ​ጨ​ና​ቂው እጅ አድኑ፤ መጻ​ተ​ኛ​ው​ንና ድሃ​አ​ደ​ጉን፥ ባል​ቴ​ቲ​ቱ​ንም አት​በ​ድሉ፤ አታ​ም​ፁ​ባ​ቸ​ውም፤ በዚ​ህም ስፍራ ንጹሕ ደምን አታ​ፍ​ስሱ።


አን​ተም በግ​ብፅ ምድር ባሪያ እንደ ነበ​ርህ፥ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚያ እን​ዳ​ዳ​ነህ ዐስብ፤ ስለ​ዚህ እኔ ዛሬ ይህን ነገር አዝ​ዝ​ሃ​ለሁ።


“በባ​ል​ን​ጀ​ራህ ግፍ አታ​ድ​ርግ፤ አት​ቀ​ማ​ውም። የሞ​ያ​ተ​ኛው ዋጋ እስከ ነገ ድረስ በአ​ንተ ዘንድ አይ​ደ​ር​ብህ።


እና​ንተ በግ​ብፅ ምድር እን​ግ​ዶች ነበ​ራ​ች​ሁና፤ ወደ እና​ንተ የመጣ እን​ግዳ እንደ ሀገር ልጅ ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ እር​ሱን እንደ ራሳ​ችሁ ውደ​ዱት፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።


በዚ​ያን ጊዜ ፈራ​ጆ​ቻ​ች​ሁን አዘ​ዝ​ኋ​ቸው። አል​ኋ​ቸ​ውም፦ የወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ነገር ስሙ፤ በሰ​ውና በወ​ን​ድሙ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ባለው መጻ​ተኛ መካ​ከል በጽ​ድቅ ፍረዱ።


ከአ​ንተ ጋር ይኑር፤ በመ​ካ​ከ​ል​ህም በሚ​ወ​ድ​ዳት በአ​ን​ዲቱ ስፍራ ይቀ​መጥ፤ አን​ተም አታ​ስ​ጨ​ን​ቀው።


“በመ​ጻ​ተኛ፥ በድሃ-አደ​ጉም፥ በመ​በ​ለ​ቲ​ቱም ላይ ፍር​ድን የሚ​ያ​ጣ​ምም ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።


ለእ​ን​ስ​ሶ​ችና ለሚ​ጠ​ሩት ለቍ​ራ​ዎች ጫጩ​ቶች፥ ምግ​ባ​ቸ​ውን የሚ​ሰ​ጣ​ቸው እርሱ ነው።


በአ​ንቺ ውስጥ አባ​ት​ንና እና​ትን አቃ​ለሉ፤ በመ​ካ​ከ​ልሽ በመ​ጻ​ተ​ኛው ላይ በደ​ልን አደ​ረጉ፤ በአ​ንቺ ውስጥ ድሀ አደ​ጉ​ንና መበ​ለ​ቲ​ቱን አስ​ጨ​ነቁ።


ለመ​ጻ​ተኛ፥ ለድሃ አደ​ጉና ለመ​በ​ለ​ቲቱ ይፈ​ር​ዳል፤ መብ​ልና ልብ​ስም ይሰ​ጠው ዘንድ ስደ​ተ​ኛ​ውን ይወ​ድ​ዳል።


“የመ​ጻ​ተ​ኛ​ው​ንና የድሃ-አደ​ጉን፥ የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም ፍርድ አታ​ጣ​ም​ም​ባ​ቸው፤ የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም ልብስ ለመ​ያዣ አት​ው​ሰ​ድ​ባት።


በድሃ አደጉ ላይ ትስ​ቃ​ላ​ች​ሁና፥ ወዳ​ጃ​ች​ሁ​ንም ትሰ​ድ​ባ​ላ​ች​ሁና።


መል​ካም መሥ​ራ​ትን ተማሩ፤ ፍር​ድን ፈልጉ፤ የተ​ገ​ፋ​ውን አድኑ፤ ለድ​ሃ​አ​ደጉ ፍረ​ዱ​ለት፤ ስለ መበ​ለ​ቲ​ቱም ተሙ​አ​ገቱ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios