Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 22:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 መበ​ለ​ቶ​ችን ባዶ​አ​ቸ​ውን ሰድ​ደ​ሃ​ቸ​ዋል፥ ድሃ​አ​ደ​ጎ​ች​ንም አስ​ጨ​ን​ቀ​ሃ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 መበለቶችን ባዶ እጃቸውን ሰድደሃል፤ የድኻ አደጎችንም ክንድ ሰብረሃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 መበለቶችን ባዶ እጃቸውን ሰድደሃቸዋል፥ የወላጅ አልቦችም ክንዶች ተሰብረዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች ባዶ እጃቸውን ሰደሃል፤ የሙት ልጆችንም መተዳደሪያ አጥፍተሃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 መበለቲቱን አንዳች አልባ ሰድደሃታል፥ የድሀ አደጎችም ክንድ ተሰብሮአል።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 22:9
20 Referencias Cruzadas  

ለማ​ት​ወ​ል​ደው ለመ​ካ​ኒቱ በጎ​ነ​ትን አላ​ደ​ረ​ገ​ላ​ትም፤ ለም​ት​ወ​ል​ደ​ውም አል​ራ​ራም።


የድ​ሃ​አ​ደ​ጎ​ቹን አህያ ይነ​ዳሉ የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም በሬ ስለ መያዣ ይወ​ስ​ዳሉ።


በአ​ንቺ ውስጥ አባ​ት​ንና እና​ትን አቃ​ለሉ፤ በመ​ካ​ከ​ልሽ በመ​ጻ​ተ​ኛው ላይ በደ​ልን አደ​ረጉ፤ በአ​ንቺ ውስጥ ድሀ አደ​ጉ​ንና መበ​ለ​ቲ​ቱን አስ​ጨ​ነቁ።


መበ​ለ​ቶች ቅሚ​ያ​ቸው እን​ዲ​ሆኑ፥ የሙት ልጆ​ች​ንም ብዝ​በ​ዛ​ቸው እን​ዲ​ያ​ደ​ርጉ፥ የድ​ሃ​ውን ፍርድ ያጣ​ምሙ ዘንድ፥ የች​ግ​ረ​ኛ​ው​ንም ሕዝ​ቤን ፍርድ ያጐ​ድሉ ዘንድ የግ​ፍን ትእ​ዛ​ዛት ለሚ​ያ​ዝዙ ወዮ​ላ​ቸው!


ብዙ ረዳት እን​ዳ​ለኝ ተማ​ምኜ በድ​ሃ​አ​ደጉ ላይ እጄን አን​ሥቼ እንደ ሆነ፥


ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ላይ ነኝ የጸ​ና​ች​ው​ንና የተ​ሰ​በ​ረ​ች​ው​ንም ክን​ዱን እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ ሰይ​ፉ​ንም ከእጁ አስ​ጥ​ለ​ዋ​ለሁ።


አለ​ቆ​ችሽ ዐመ​ፀ​ኞ​ችና የሌ​ቦች ባል​ን​ጀ​ሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወ​ድ​ዳሉ፤ ፍር​ድ​ንም ሊያ​ጣ​ምሙ ይፈ​ል​ጋሉ፤ ለሙት ልጅ አይ​ፈ​ር​ዱም፤ የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም አቤ​ቱታ አያ​ዳ​ም​ጡም።


መል​ካም መሥ​ራ​ትን ተማሩ፤ ፍር​ድን ፈልጉ፤ የተ​ገ​ፋ​ውን አድኑ፤ ለድ​ሃ​አ​ደጉ ፍረ​ዱ​ለት፤ ስለ መበ​ለ​ቲ​ቱም ተሙ​አ​ገቱ።”


ኑ፥ እን​ስ​ገድ ለእ​ር​ሱም እን​ገዛ፤ በእ​ርሱ በፈ​ጠ​ረን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እና​ል​ቅስ፤


እኔ​ንስ ይገ​ር​ፉኝ ዘንድ አቈ​ዩኝ፥ ቍስሌ ሁል​ጊዜ በፊቴ ነውና።


“በመ​ጻ​ተኛ፥ በድሃ-አደ​ጉም፥ በመ​በ​ለ​ቲ​ቱም ላይ ፍር​ድን የሚ​ያ​ጣ​ምም ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።


በድሃ አደጉ ላይ ትስ​ቃ​ላ​ች​ሁና፥ ወዳ​ጃ​ች​ሁ​ንም ትሰ​ድ​ባ​ላ​ች​ሁና።


የሞ​አብ ቀንድ ተሰ​በረ፤ እጁም ተቀ​ጠ​ቀጠ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! በጸሎት ርዝመት እያመካኛችሁ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ፥ ወዮላችሁ፤ ስለዚህ የባሰ ፍርድ ትቀበላላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios