ኤርምያስ 18:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁን እንግዲህ ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ ክፉ ነገር እፈጥርባችኋለሁ፤ ምክርንም እመክርባችኋለሁ፤ አሁንም ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ መንገዳችሁንና ሥራችሁንም አቅኑ ብለህ ተናገራቸው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሁንም እንግዲህ ለይሁዳ ሕዝብና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ እንዲህ በላቸው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ጥፋትን እያዘጋጀሁላችሁ ነው፤ ክፋትንም እየጠነሰስሁላችሁ ነው። ስለዚህ ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ መንገዳችሁንና ተግባራችሁን አቅኑ።” ’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁን እንግዲህ ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚቀመጡ፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ክፉ ነገር እፈጥርባችኋለሁ፥ አሳብንም አስብባችኋለሁ፤ አሁንም ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ መንገዳችሁንና ሥራችሁንም አስተካክሉ’ ብለህ ተናገራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እኔ እነርሱን ለመቅጣት በእነርሱ ላይ ክፉ ነገር የማደርግ መሆኔን ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሕዝብ ንገራቸው፤ ኃጢአት መሥራትን እንዲተዉና አካሄዳቸውንና አሠራራቸውን ሁሉ እንዲለውጡ ምከራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁን እንግዲህ ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚቀመጡ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ክፉ ነገር እፈጥርባችኋለሁ፥ አሳብንም አስብባችኋለሁ፥ አሁንም ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ መንገዳችሁንና ሥራችሁንም አቅኑ ብለህ ተናገራቸው። |
አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር በእነዚህ በነቢያትህ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ አድርጎአል፤ እግዚአብሔርም በላይህ ክፉ ተናግሮብሃል።”
እግዚአብሔርም፥ “ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ለአባቶቻችሁም እንዳዘዝሁት፥ በባሪያዎቼ በነቢያት የላክሁላችሁን ትእዛዜንና ሥርዐቴን፥ ሕጌንም ሁሉ ጠብቁ” ብሎ በነቢዩ ሁሉና በባለ ራእዩ አፍ ሁሉ በእስራኤልና በይሁዳ መሰከረ።
“አባቶቻችን በእርስዋ የተጻፈውን ሁሉ ይሠሩ ዘንድ የዚህችን መጽሐፍ ቃል ስላልሰሙ በላያችን የነደደ የእግዚአብሔር ቍጣ እጅግ ነውና ሄዳችሁ ስለ እኔና ስለ ሕዝቡ ስለ ይሁዳም ሁሉ ስለዚችም ስለተገኘችው መጽሐፍ ቃል ሁሉ እግዚአብሔርን ጠይቁ።
የሶርያም ንጉሥ ንዕማንን፥ “ሂድ፥ ለእስራኤል ንጉሥ ደብዳቤ እልካለሁ” አለው። እርሱም ሄደ፤ ዐሥርም መክሊት ብር፥ ስድስት ሺህም ወቄት ወርቅ፥ ዐሥርም መለወጫ ልብስ በእጁ ወሰደ።
አሁንም በወይኔ ላይ የማደርገውን እነግራችኋለሁ፤ አጥሩን እነቅላለሁ፤ ለብዝበዛም ይሆናል፤ ቅጥሩንም አፈርሳለሁ፤ ለመራገጫም ይሆናል።
ጻድቅ ሰው እንደጠፋ አያችሁ፤ ይህንም በልባችሁ አላሰባችሁም፤ ጻድቃን ሰዎች ይወገዳሉ፤ ጻድቅም ከክፋት ፊት እንደ ተወገደ ማንም አያስተውልም።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ሊያመልጡት የማይችሉትን ክፉ ነገር በዚህ ሕዝብ ላይ አመጣለሁ፤ ወደ እኔም ይጮኻሉ፤ እኔ ግን አልሰማቸውም።
እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ ጠቦት በግ ሆንሁ፤ እነርሱም በእንጀራው ዕንጨት እንጨምር ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰብ ከሕያዋን ምድር እናጥፋው ብለው ክፉ ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።
እነርሱም፥ “ሕግ ከካህን፥ ምክርም ከጠቢብ፥ ቃልም ከነቢይ አይጠፋምና ኑ፤ በኤርምያስ ላይ ምክርን እንምከር። ኑ፤ በምላስ እንምታው፤ ቃሉንም ሁሉ አናዳምጥ” አሉ።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ቃሌን እንዳይሰሙ አንገታቸውን አደንድነዋልና እነሆ በዚች ከተማና በመንደሮችዋ ሁሉ ላይ የተናገርሁባትን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣለሁ።”
“የይሁዳ ነገሥታትና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በዚህ ስፍራ ክፉ ነገርን አመጣለሁ፤ የሰማውም ሰው ሁሉ ይደነግጣል፤ ጆሮዎቹንም ይይዛል።
እርሱም፥ “ሁላችሁ እናንተ ከክፉ መንገዳችሁና ከሥራችሁ ክፋት ተመለሱ፤ እግዚአብሔርም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣችሁ ምድር ትቀመጣላችሁ አለ።
አሁንም መንገዳችሁንና ሥራችሁን አሳምሩ፤ የአምላካችሁንም የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እግዚአብሔርም የተናገረባችሁን ክፉ ነገር ይተዋል።
ምናልባት እያንዳንዳቸው ይሰሙ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም ስለ ሥራቸው ክፋት ያሰብሁባቸውን ክፉ ነገር እተዋለሁ።”
“ሰው ሚስቱን ቢፈታ፥ ከእርሱም ዘንድ ሄዳ ሌላ ወንድ ብታገባ፥ በውኑ ደግሞ ወደ እርሱ ትመለሳለችን? ያች ሴት እጅግ የረከሰች አይደለችምን? አንቺም ከብዙ እረኞች ጋር አመንዝረሻል፤ ወደ እኔም ትመለሻለሽን? ይላል እግዚአብሔር።
“ከዳተኞች ልጆች ሆይ! ተመለሱ፤ ቍስላችሁንም እፈውሳለሁ። እነሆ እኛ አገልጋዮችህ እንሆናለን፤ አንተ አምላካችን እግዚአብሔር ነህና።
ደግሞም፦ እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ሥራችሁንም አሳምሩ፤ ታገለግሉአቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፤ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠሁት ምድር ትቀመጣላችሁ እያልሁ ባሪያዎችን ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር፤ እናንተ ግን ጆሮአችሁን አላዘነበላችሁም፤ እኔንም አልሰማችሁኝም።
ምናልባት የይሁዳ ቤት ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ዘንድ፥ እኔም በደላቸውንና ኀጢአታቸውን ይቅር እል ዘንድ፥ እኔ አደርግባቸዋለሁ ያልሁትንና ያሰብሁትን ክፉ ነገር ሁሉ ይሰሙ ይሆናል።”
እግዚአብሔር በዚህ ሕዝብ ላይ የተናገረው ቍጣውና መዓቱ ታላቅ ነውና ምናልባት ልመናቸው በእግዚአብሔር ፊት ትደርስ ይሆናል፤ ሁሉም ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ይሆናል።”
“ፍላጾችን አዘጋጁ፤ ጕራንጕሬዎችንም ሙሉ፤ እግዚአብሔር ያጠፋት ዘንድ ቍጣው በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ንጉሥ መንፈስ አስነሥቶአል፤ የእግዚአብሔር በቀል የመቅደሱ በቀል ነውና።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ መንገዳችሁንና ሥራችሁን አቅኑ፤ በዚህም ስፍራ አሳድራችኋለሁ።
እኔም ያልመለስሁትን የጻድቁን ልብ ወደ ዐመፃ መልሳችኋልና፥ በሕይወትም ይኖር ዘንድ ከክፉ መንገድ እንዳይመለስ የኀጢአተኛውን እጅ አበርትታችኋልና፤
በውኑ ኀጢአተኛ ይሞት ዘንድ መፍቀድን እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከክፉ መንገዱ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ ነው እንጂ።
ሰዎችና እንስሶችም ማቅ ይልበሱ፤ ወደ እግዚአብሔርም በአንድነት ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ከአለው ግፍ ይመለሱ።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህ ወገን ላይ በክፉ አስባለሁ፥ ከዚያም አንገታችሁን አታነሡም፥ ዘመኑም ክፉ ነውና ቀጥ ብላችሁ አትሄዱም።
ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ እኔ ተመለሱ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
አስቀድሜ በኢየሩሳሌምና በደማስቆ ላሉት፥ ለይሁዳ አውራጃዎችም ሁሉ ነገርኋቸው፤ ለአሕዛብም ንስሓ ገብተው ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ ዘንድ፥ ለንስሓቸውም የሚገባ ሥራን ይሠሩ ዘንድ አስተማርኋቸው።
አሁንም “ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን፤ በዚያም ዓመት እንኖራለን፤ እንነግድማለን፤ እናተርፍማለን፤” የምትሉ እናንተ! ተመልከቱ፤ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና።