በእጃችሁ ሥራ ሁሉ ታስቈጡኝ ዘንድ ትታችሁኛልና፥ ለሌሎች አማልክትም ዐጥናችኋልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነድዳል፥ አይጠፋምም።
ኤርምያስ 17:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን የሰንበትን ቀን እንድትቀድሱ፥ በሰንበትም ቀን ሸክምን ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች እንዳትገቡ የነገርኋችሁን ባትሰሙኝ፥ በበሮችዋ ላይ እሳትን አነድዳለሁ፤ የኢየሩሳሌምንም ግንቦች ትበላለች፤ አትጠፋምም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን የሰንበትን ቀን ሳትቀድሱ፣ በሰንበት ቀን ሸክም ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች በመግባት ትእዛዜን ብትጥሱ፣ በኢየሩሳሌም በሮች ላይ ምሽጎቿን የሚበላ፣ የማይጠፋ እሳት እጭራለሁ።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን የሰንበትን ቀን እንድትቀድሱ፥ በሰንበትም ቀን ሸክምን ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች እንዳትገቡ የነገርኋችሁን ባትሰሙኝ፥ በበሮችዋ ላይ እሳትን አነድዳለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች፥ አትጠፋምም።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ለእኔ መታዘዝና ሰንበትንም የተቀደሰ ቀን አድርገው ማክበር ይገባቸዋል፤ በዚህ ዕለት በኢየሩሳሌም የቅጽር በሮች ምንም ዐይነት ሸክም ይዘው መግባት የለባቸውም፤ ትእዛዜን ባለመቀበል ይህን ቢያደርጉ ግን የኢየሩሳሌም ቅጽር በሮች በእሳት እንዲጋዩ አደርጋለሁ፤ የኢየሩሳሌም ቤተ መንግሥቶችም በእሳት ይነዳሉ፤ እሳቱንም ሊያጠፋ የሚችል የለም።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን የሰንበትን ቀን እንድትቀድሱ፥ በሰንበትም ቀን ሸክምን ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች እንዳትገቡ የነገርኋችሁን ባትሰሙኝ፥ በበሮችዋ ላይ እሳትን አነድዳለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም አዳራሾች ትበላለች፥ አትጠፋም። |
በእጃችሁ ሥራ ሁሉ ታስቈጡኝ ዘንድ ትታችሁኛልና፥ ለሌሎች አማልክትም ዐጥናችኋልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነድዳል፥ አይጠፋምም።
የንጉሡም የአበዛዎች አለቃ የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት አቃጠለ። የኢየሩሳሌምንም ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ።
የእግዚአብሔርንም ቤተ መቅደስ አቃጠለ፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር አፈረሰ፤ አዳራሾችዋንም በእሳት አቃጠለ፤ መልካሙንም ዕቃዋን ሁሉ አጠፋ።
ኀይላቸውም እንደ መቃ መስዬ፥ ሥራቸውም እንደ ጠለሸት ይሆናል፤ ኃጥአንና ዐማፅያንም አብረው ይቃጠላሉ፤ እሳቱንም የሚያጠፋላቸው ያጣሉ።”
እኔን ፈጽሞ ብትሰሙ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በሰንበትም ቀን በዚህች ከተማ በሮች ሸክም ባታገቡ፥ የሰንበትንም ቀን ብትቀድሱ፥ ሥራንም ሁሉ ባትሠሩባት፥
አንተም የሰጠሁህን ርስት ትለቅቃለህ፤ ለዘለዓለምም በማታውቃት ምድር ለጠላቶችህ አስገዛሃለሁ፤ ቍጣዬ ለዘለዓለም እንደ እሳት ትነድዳለችና።
የዳዊት ቤት ሆይ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይነድድና ማንም ሳያጠፋው እንዳያቃጥል፥ በማለዳ ፍርድን አድርጉ፤ የተነጠቀውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ።
እንደ ሥራችሁም ፍሬ እቀጣችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር በዱርዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፤ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል።”
ይችን ከተማ የሚወጉ ከለዳውያን ይመጣሉ፤ ከተማዋንም በእሳት ያነድዱአታል፤ ያስቈጡኝም ዘንድ በሰገነታቸው ላይ ለበዓል ያጠኑባቸውን፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቍርባን ያፈሰሱባቸውን ቤቶች ያቃጥሉአቸዋል።
የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት አቃጠለ፤ የኢየሩሳሌምንም ቤቶች ሁሉ ፥ ታላላቆችን ቤቶች ሁሉ፥ በእሳት አቃጠለ።
እንግዲህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ቍጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ፥ በሰውና በእንስሳ ላይ፥ በዱር ዛፎችና በምድር ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።”
ዋው። ማደሪያውን እንደ ወይን ጋረደ፤ በዓሉን ሁሉ አጠፋ፤ እግዚአብሔር በጽዮን ያደረገውን በዓሉንና ሰንበቱን አስረሳ፤ በቍጣውም መዓት ነገሥታቱን፥ አለቆቹንና ካህናቱን አጠፋ።
ካፍ። እግዚአብሔር መዓቱን ፈጽሞአል፤ ጽኑ ቍጣውንም አፍስሶአል፤ እሳትን በጽዮን ውስጥ አቃጠለ፤ መሠረቷንም በላች።
ቤቶችሽንም በእሳት ያቃጥላሉ፤ በብዙም ሴቶች ፊት ይበቀሉሻል፤ ግልሙትናሽንም አስተውሻለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ዋጋ አትሰጪም።
ልባቸው እንዲቀልጥ፥ መሰናክላቸውም እንዲበዛ የሚገድለውን ሰይፍ በበሮቻቸው ሁሉ ላይ አድርጌአለሁ፤ ወዮ! ያብረቀርቅ ዘንድ ተሰንግሏል፤ ይገድልም ዘንድ ተስሏል።
ለእስራኤልም ምድር እንዲህ በል፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፤ ሰይፌንም ከሰገባው እመዝዘዋለሁ፤ ጻድቁንና ኃጥኡን ከአንቺ ዘንድ አጠፋለሁ።
እስራኤል ፈጣሪውን ረስቶአል፤ መስገጃዎችንም ሠርቶአል፤ ይሁዳም የተመሸጉትን ከተሞች አብዝቶአል፤ እኔ ግን በከተሞች ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፤ መሠረቶቻቸውንም ትበላለች።
በራባ ቅጥር ላይ እሳትን አነድዳለሁ፤ በጦርነት ቀን በጩኸት መሠረቶችዋን ትበላለች፤ በፍጻሜዋም ቀን ትናወጣለች።
በሞዓብ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፤ የከተሞችዋንም መሠረቶች ትበላለች፤ ሞዓብም በድካምና በውካታ፥ በመለከትም ድምፅ ይሞታል፤
እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና፥ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፤ ምድርንም ከፍሬዋ፤ ጋር ትበላለች፤ የተራሮችን መሠረት ታነድዳለች።
ለሚናገረው እንቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነርሱ በደብረ ሲና የተገለጠላቸውን እንቢ ስለ አሉት ካልዳኑ፥ ከሰማይ ከመጣው ፊታችንን ብንመልስ እኛማ እንዴታ?