Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 44:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 “አንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የነ​ገ​ር​ኸ​ንን ቃል አን​ሰ​ማም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 “አንተ በእግዚአብሔር ስም የነገርኸንን መልእክት አንሰማም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 “አንተ በጌታ ስም የነገርኸንን ቃል አንሰማህም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 “አንተ በእግዚአብሔር ስም የተናገርከውን ሁሉ መስማት አንፈልግም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 አንተ በእግዚአብሔር ስም የነገርኸንን ቃል አንሰማህም።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 44:16
24 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን እነ​ዚ​ያን ልነ​ግ​ሥ​ባ​ቸው ያል​ወ​ደ​ዱ​ትን ጠላ​ቶ​ችን ወደ​ዚህ አም​ጡና በፊቴ ውጉ​አ​ቸው።”


የሀ​ገሩ ሰዎች ግን ይጠ​ሉት ነበ​ርና፥ ይህ በእኛ ላይ ሊነ​ግሥ አን​ሻም ብለው አከ​ታ​ት​ለው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላኩ።


አለ​ቆ​ቹም ንጉ​ሡን፥ “ይህን የመ​ሰ​ለ​ውን ቃል ሲነ​ግ​ራ​ቸው በዚ​ያች ከተማ የቀ​ሩ​ትን የሰ​ል​ፈ​ኞ​ቹን እጅ፥ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ሁሉ እጅ ያደ​ክ​ማ​ልና ይህ ሰው ይገ​ደል፤ ለዚህ ሕዝብ ክፋ​ትን እንጂ ሰላ​ምን አይ​መ​ኝ​ለ​ት​ምና” አሉት።


እነ​ር​ሱም፥ “ሕግ ከካ​ህን፥ ምክ​ርም ከጠ​ቢብ፥ ቃልም ከነ​ቢይ አይ​ጠ​ፋ​ምና ኑ፤ በኤ​ር​ም​ያስ ላይ ምክ​ርን እን​ም​ከር። ኑ፤ በም​ላስ እን​ም​ታው፤ ቃሉ​ንም ሁሉ አና​ዳ​ምጥ” አሉ።


ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ ወደ አሉ ወደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ኀጢ​አት ተመ​ለሱ፥ ያመ​ል​ኩ​አ​ቸ​ውም ዘንድ እን​ግ​ዶ​ችን አማ​ል​ክት ተከ​ተሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና የይ​ሁዳ ቤት ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን አፈ​ረሱ።


እነ​ርሱ ሁሉ ግን በክፉ ልባ​ቸው እል​ከ​ኝ​ነት ሄዱ እንጂ አል​ሰ​ሙም፤ ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም አላ​ዘ​ነ​በ​ሉም፤ ስለ​ዚህ ያዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ውን እነ​ር​ሱም ያላ​ደ​ረ​ጉ​ትን የዚ​ህን ቃል ኪዳን ቃል ሁሉ አመ​ጣ​ሁ​ባ​ቸው።”


አስ​ጸ​ያፊ ነገ​ርን ስለ ሠሩ አፍ​ረ​ዋ​ልን? ምንም አላ​ፈ​ሩም፤ እፍ​ረ​ት​ንም አላ​ወ​ቁም፤ ስለ​ዚህ ከሚ​ወ​ድቁ ጋር ይወ​ድ​ቃሉ፤ በጐ​በ​ኘ​ኋ​ቸ​ውም ጊዜ ይዋ​ረ​ዳሉ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


አደ​መ​ጥሁ፤ ሰማ​ሁም፤ ቅንን ነገር አል​ተ​ና​ገ​ሩም፤ ማና​ቸ​ውም፦ ምን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ? ብሎ ከክ​ፋቱ ንስሓ የገባ የለም፤ የሚ​ሮ​ጠ​ውም ወደ ሰልፍ እን​ደ​ሚ​ሮጥ ፈረስ ሲሮጥ ደከመ።


ዛሬም ክብ​ራ​ቸው ተዋ​ር​ዷ​ልና፥ ፊታ​ቸ​ውም አፍ​ሯ​ልና ኀጢ​አ​ታ​ቸው እንደ ሰዶ​ምና እንደ ገሞራ ኀጢ​አት ተቃ​ወ​መ​ቻ​ቸው፤ በላ​ያ​ቸ​ውም ተገ​ልጣ ታወ​ቀች።


“ማሰ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ከእኛ እን​በ​ጥስ፥ ቀን​በ​ራ​ቸ​ው​ንም ከእኛ ላይ እን​ጣል።”


ፈር​ዖ​ንም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እለ​ቅቅ ዘንድ ቃሉን የም​ሰ​ማው እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማን ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ው​ቅም፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ደግሞ አል​ለ​ቅ​ቅም” አለ።


ሕዝቡ ግን የሳ​ሙ​ኤ​ልን ነገር ይሰሙ ዘንድ እንቢ አሉ፥ “እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አን​ግ​ሥ​ልን፤


በጠራሁ ጊዜ አልሰማችሁኝምና እጄን ዘረጋሁ፥ ማንም አላስተዋለም ነገርንም አበዛሁ፥ አልመለሳችሁልኝም፥


ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ የሚሉ፥ በክፉ ልባ​ቸ​ውም እል​ከ​ኝ​ነት የሚ​ሄዱ፥ ያገ​ለ​ግ​ሏ​ቸ​ውና ይሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸው ዘንድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ተከ​ት​ለው የሚ​ሄዱ እነ​ዚህ ክፉ ሕዝብ አን​ዳች እን​ደ​ማ​ት​ረባ እን​ደ​ዚች መታ​ጠ​ቂያ ይሆ​ናሉ።


“እና​ንተ ግን በዚች ምድር አን​ቀ​መ​ጥም ብትሉ፥ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ባት​ሰሙ፥


የኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ ኣዛ​ር​ያስ፥ የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ ትዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችም ሰዎች ሁሉ ኤር​ም​ያ​ስን፥ “ሐሰት ተና​ግ​ረ​ሃል፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በዚያ ትቀ​መጡ ዘንድ ወደ ግብፅ አት​ግቡ ብሎ አል​ላ​ከ​ህም፤


ኤር​ም​ያ​ስም ለሕ​ዝቡ ሁሉ፥ ለሴ​ቶ​ቹም ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “በግ​ብፅ ምድር የም​ት​ኖሩ አይ​ሁድ ሁሉ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በመ​ን​ገድ ላይ ቁሙ ተመ​ል​ከ​ቱም፤ የቀ​ደ​መ​ች​ው​ንም መን​ገድ ጠይቁ፤ መል​ካ​ሚቱ መን​ገድ ወዴት እንደ ሆነች ዕወቁ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ላይ ሂዱ፤ ለነ​ፍ​ሳ​ች​ሁም መድ​ኀ​ኒ​ትን ታገ​ኛ​ላ​ችሁ፤” እነ​ርሱ ግን፥ “አን​ሄ​ድ​ባ​ትም” አሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እና​ን​ተና ሚስ​ቶ​ቻ​ችሁ በአ​ፋ​ችሁ፦ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት እና​ጥን ዘንድ፥ የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን እና​ፈ​ስ​ስ​ላት ዘንድ የተ​ሳ​ል​ነ​ውን ስእ​ለ​ታ​ች​ንን በር​ግጥ እን​ፈ​ጽ​ማ​ለን አላ​ችሁ፤ በእ​ጃ​ች​ሁም አደ​ረ​ጋ​ች​ሁት፤ እን​ግ​ዲህ ስእ​ለ​ታ​ች​ሁን አጽኑ፤ ስእ​ለ​ታ​ች​ሁ​ንም ፈጽሙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios