Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




አሞጽ 1:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በቴ​ማን ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የቅ​ጥ​ር​ዋ​ንም መሠ​ረ​ቶች ትበ​ላ​ለች።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የባሶራን ምሽጎች እንዲበላ፣ በቴማን ቅጥሮች ላይ እሳት እሰድዳለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በቴማን ላይ እሳትን እልካለሁ፥ የባሶራንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ስለዚህ በቴማን ከተማ ላይ እሳት እለቅበታለሁ፤ የቦጽራንም ምሽጎች ያቃጥላል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በቴማን ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፥ የባሶራንም አዳራሾች ትበላለች።

Ver Capítulo Copiar




አሞጽ 1:12
14 Referencias Cruzadas  

ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኤ​ዶ​ም​ያስ ላይ የመ​ከ​ረ​ባ​ትን ምክር፥ በቴ​ማ​ንም በሚ​ኖሩ ስዎች ላይ ያሰ​ባ​ትን ዐሳብ ስሙ፤ ትን​ን​ሾች በጎ​ችን ዘር​ፈው ይወ​ስ​ዷ​ቸ​ዋል፤ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ት​ንም ማደ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ባድማ ያደ​ር​ጉ​ባ​ቸ​ዋል።


ስለ ኤዶ​ም​ያስ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በውኑ በቴ​ማን ጥበብ የለ​ምን? ከብ​ል​ሃ​ተ​ኞ​ችስ ምክር ጠፍ​ቶ​አ​ልን? ጥበ​ባ​ቸ​ውስ አል​ቆ​አ​ልን?


እነሆ እንደ ንስር ወጥቶ ይመ​ለ​ከ​ታል፤ ክን​ፉ​ንም በባ​ሶራ ላይ ይዘ​ረ​ጋል፤ በዚ​ያም ቀን የኤ​ዶ​ም​ያስ ኀያ​ላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆ​ናል።


ባሶራ ምድረ በዳ፥ መሰ​ደ​ቢ​ያና መረ​ገ​ሚ​ያም እን​ድ​ት​ሆን በራሴ ምያ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከተ​ሞ​ች​ዋም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባድማ ይሆ​ናሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት በባ​ሶራ፥ ታላ​ቅም እርድ በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድር አለ​ውና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ በደም ተሞ​ል​ታ​ለች፤ በበግ ስብ፥ በፍ​የል ደምም፥ በአ​ው​ራም በግ ስብ ወፍ​ራ​ለች።


ባላ​ቅም ሞተ፤ በእ​ርሱ ፈን​ታም የባ​ሶ​ራው የዛራ ልጅ ኢዮ​ባብ ነገሠ።


የዔ​ሳው ልጅ የኤ​ል​ፋዝ ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ቴማን፥ ኤሞር፥ ሳፍር፥ ጎቶን፥ ቄኔዝ።


ሰይፌ በሰ​ማይ ሆና ሰከ​ረች፤ እነሆ፥ በኤ​ዶ​ም​ያ​ስና በሚ​ጠ​ፉት ሕዝብ ላይ ለፍ​ርድ ትወ​ር​ዳ​ለች።


ከኤ​ዶ​ም​ያስ፥ ከባ​ሶራ የሚ​መጣ፥ ልብ​ሱም የቀላ፥ የሚ​መካ ኀይ​ለኛ፥ አለ​ባ​በ​ሱም ያማረ፥ ይህ ማን ነው? ስለ ጽድቅ የም​ከ​ራ​ከር፥ ስለ ማዳ​ንም የም​ፈ​ርድ እኔ ነኝ።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እጄን በኤ​ዶ​ም​ያስ ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ዘንድ ሰው​ንና እን​ስ​ሳን አጠ​ፋ​ለሁ፤ ባድ​ማም አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ ከቴ​ማ​ንና ከድ​ዳ​ንም ያመ​ለጡ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ።


የአ​ብ​ድዩ ራእይ። ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ኤዶ​ም​ያስ እን​ዲህ ይላል፦ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መስ​ማ​ትን ሰማሁ፤ ከባ​ቢን ወደ አሕ​ዛብ ልኮ፥ “ተነሡ፤ በላ​ይ​ዋም እን​ነ​ሣና እን​ው​ጋት።


እግዚአብሔር ከቴማን፥ ቅዱሱም ከፋራን ተራራ ይመጣል። ክብሩ ሰማያትን ከድኖአል፥ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል።


ባላ​ቅም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ የባ​ሶራ ሰው የዛራ ልጅ ኢዮ​ባብ ነገሠ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios