Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 6:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እኔም፥ “የመ​ለ​ከ​ቱን ድምፅ አድ​ምጡ” ብዬ ጠባ​ቂ​ዎ​ችን ሾም​ሁ​ባ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን፥ “አና​ዳ​ም​ጥም” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ጠባቂዎችን አቆምሁላችሁ፤ ‘የመለከትንም ድምፅ ስሙ’ አልኋችሁ፤ እናንተ ግን፣ ‘አንሰማም’ አላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እኔም፦ ‘የመለከቱን ድምፅ አድምጡ’ ብዬ ጠባቆችን ሾምሁባችሁ፤ እነርሱ ግን፦ ‘አናደምጥም’ አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ከዚያን በኋላ እግዚአብሔር የማስጠንቀቂያውን ጥሩምባ ድምፅ የሚያሰሙ ጠባቂዎችን አቆመ፤ እነርሱ ግን “አንሰማም” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እኔም፦ የመለከቱን ድምፅ አድምጡ ብዬ ጠባቆችን ሾምሁባችሁ፥ እነርሱ ግን፦ አናደምጥም አሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 6:17
19 Referencias Cruzadas  

ስለ ኤዶ​ም​ያስ የተ​ነ​ገረ ነገር። አንዱ ከሴ​ይር፥ “ጕበኛ ሆይ፥ ሌሊቱ ምን ያህል ነው? ጕበኛ ሆይ፥ ሌሊቱ ምን ያህል ነው?” ብሎ ጠራኝ።


ሁሉም ዕው​ራን እንደ ሆኑ ኑና እዩ፤ ሁሉ ያለ ዕው​ቀት ናቸው፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው፤ ይጮ​ኹም ዘንድ አይ​ች​ሉም፤ በመ​ኝ​ታ​ቸ​ውም ሕል​ምን ያል​ማሉ፤ ማን​ቀ​ላ​ፋ​ት​ንም ይወ​ድ​ዳሉ።


በኀ​ይ​ልህ ጩኽ፤ አት​ቈ​ጥብ፤ ድም​ፅ​ህን እንደ መለ​ከት አንሣ፤ ለሕ​ዝቤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን፥ ለያ​ዕ​ቆብ ቤትም በደ​ላ​ቸ​ውን ንገር።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ሽን በቅ​ጥ​ርሽ ላይ ቀንና ሌሊት አቁ​ሜ​አ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​ስቡ ከቶ ዝም አይ​ሉም፤


እነ​ርሱ ግን፥ “እን​ጨ​ክ​ና​ለን፤ ክዳ​ታ​ች​ንን ተከ​ት​ለን እን​ሄ​ዳ​ለን፥ ሁላ​ች​ንም ክፉ ልባ​ች​ንን ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኛ​ትን እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባሪ​ያ​ዎ​ቹን ነቢ​ያ​ትን ወደ እና​ንተ ላከ፤ እነ​ር​ሱም ማል​ደው ገሠ​ገሡ፤ እና​ን​ተም አል​ሰ​ማ​ች​ኋ​ቸ​ውም፤ ለመ​ስ​ማ​ትም ጆሮ​አ​ች​ሁን አላ​ዘ​ነ​በ​ላ​ች​ሁም።


አሕ​ዛ​ብና የመ​ን​ጋው ጠባ​ቂ​ዎች ሆይ፥ ስለ​ዚህ ስሙ።


አን​ተም፦ የአ​ም​ላ​ኩን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ያል​ሰማ፥ ተግ​ሣ​ጽ​ንም ያል​ተ​ቀ​በለ ሕዝብ ይህ ነው፤ እው​ነት ጠፍ​ቶ​አል፤ ከአ​ፋ​ቸ​ውም ተቈ​ር​ጦ​አል ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።


ሕዝቤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስለ ምን ወደ ኋላ​ቸው ተመ​ለሱ? ዐመ​ፅን ዐም​ፀ​ዋል፥ መመ​ለ​ስ​ንም እንቢ ብለ​ዋል።


ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ክፉ​ዎ​ችና ልበ ደን​ዳ​ኖች ናቸ​ውና፥ እኔ​ንም መስ​ማት እንቢ ብለ​ዋ​ልና የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት አን​ተን አይ​ሰ​ሙ​ህም።


በብ​ብ​ታ​ቸው እንደ መሬት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት እንደ ንስር ይመ​ጣል። ቃል ኪዳ​ኔን ተላ​ል​ፈ​ዋ​ልና፥ በሕ​ጌም ላይ ዐም​ፀ​ዋ​ልና።


በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፥ በአምባ ላይም እወጣለሁ፣ የሚናገረኝንም፥ ስለ ክርክሬም የምመልሰውን አውቅ ዘንድ እመለከታለሁ።


የቀደሙት ነቢያት ለአባቶቻችሁ እንዲህ ብለው ሰብከዋል፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፣ እነርሱ ግን አልሰሙም፥ እኔንም አላደመጡም፣ እንደ እነርሱ አትሁኑ፥ ይላል እግዚአብሔር።


እነርሱ ግን ደንደሳቸውን አዞሩ እንጂ መስማትን እምቢ አሉ፣ እንዳይሰሙም ጆሮአቸውን አደነቈሩ።


ለመ​ም​ህ​ሮ​ቻ​ችሁ ታዘዙ፤ ተገ​ዙ​ላ​ቸ​ውም፤ ስለ እና​ንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ምላሽ የሚ​ሰጡ እንደ መሆ​ና​ቸው፥ ይህን ሳያ​ዝኑ ደስ ብሎ​አ​ቸው ያደ​ር​ጉት ዘንድ ስለ ነፍ​ሳ​ችሁ ይተ​ጋ​ሉና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos