Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




አሞጽ 2:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በሞ​ዓብ ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የከ​ተ​ሞ​ች​ዋ​ንም መሠ​ረ​ቶች ትበ​ላ​ለች፤ ሞዓ​ብም በድ​ካ​ምና በው​ካታ፥ በመ​ለ​ከ​ትም ድምፅ ይሞ​ታል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የቂርዮትን ምሽጎች እንዲበላ፣ በሞዓብ ላይ እሳት እሰድዳለሁ፤ ሞዓብ በጦርነት ጩኸትና በመለከት ድምፅ መኻል፣ በታላቅ ሁካታ ውስጥ ይሞታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በሞዓብ ላይ እሳትን እልካለሁ፥ የቂርዮትንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች፤ ሞዓብም በውካታና በጩኸት በመለከትም ድምፅ መካከል ይሞታል፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ስለዚህ በሞአብ ምድር እሳት እለቅበታለሁ፤ የቂሪዮትንም ምሽጎች ያቃጥላል፤ ጦረኞች ድንፋታ፥ ጩኸትና የመለከት ድምፅ እያሰሙ የሞአብን ሕዝብ ይጨርሳሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በሞዓብ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፥ የቂርዮትንም አዳራሾች ትበላለች፥ ሞዓብም በውካታና በጩኸት በመለከትም ድምፅ ይሞታል፥

Ver Capítulo Copiar




አሞጽ 2:2
8 Referencias Cruzadas  

በደም የተ​ለ​ወሰ ልብስ በእ​ሳት ከሚ​ቃ​ጠል በቀር ለም​ንም አይ​ጠ​ቅ​ምም።


በቂ​ር​ዮት፥ በቦ​ሶራ፥ በሞ​አ​ብም ምድር ከተ​ሞች ሁሉ ቅር​ብና ሩቅ በሆኑ ላይ ፍርድ መጥ​ቶ​አል።


ከሐ​ሴ​ቦን ጩኸት እስከ ኤሊ​ያ​ሊና እስከ ኢያሳ ድረስ ድም​ፃ​ቸ​ውን ሰጥ​ተ​ዋል፤ ከሴ​ጎር እስከ ሖሮ​ና​ይ​ምና እስከ ዔግ​ላት ሺሊ​ሺያ ድረስ ይደ​ር​ሳል፤ የኔ​ም​ሬም ውኃ ደር​ቋ​ልና።


ሐቄ​ር​ዮት ተያ​ዘች፤ አን​ባ​ዎ​ች​ዋም ተወ​ስ​ደ​ዋል፤ በዚ​ያም ቀን የሞ​አብ ኀያ​ላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆ​ናል።


ከሰ​ልፍ የሸሹ ከሐ​ሴ​ቦን ጥላ በታች ቆመ​ዋል፤ እሳት ከሐ​ሴ​ቦን፥ ነበ​ል​ባ​ልም ከሴ​ዎን ወጥ​ቶ​አል፤ የሞ​አ​ብ​ንም ማዕ​ዘን፥ የሚ​ጮኹ ልጆ​ች​ንም ራስ በል​ቶ​አል።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሞአ​ብና ሴይር፦ እነሆ የይ​ሁዳ ቤት እንደ አሕ​ዛብ ሁሉ ነው ብለ​ዋ​ልና፤


በራባ ቅጥር ላይ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በጦ​ር​ነት ቀን በጩ​ኸት መሠ​ረ​ቶ​ች​ዋን ትበ​ላ​ለች፤ በፍ​ጻ​ሜ​ዋም ቀን ትና​ወ​ጣ​ለች።


በአ​ዛ​ሄል ቤት ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የወ​ልደ አዴ​ር​ንም መሠ​ረ​ቶች ትበ​ላ​ለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos