ኢሳይያስ 24:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከበሮአቸው ደስታ አልቆአል፤ መታጀራቸውም አልቃለች፤ የኃጥኣን ሀብት አልቆአል፤ የመሰንቆ ድምፅም ቀርቶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የከበሮ ደስታ ጸጥ አለ፤ የጨፋሪዎች ጩኸት አበቃ፤ ደስ የሚያሠኘውም በገና እረጭ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የከበሮው ሐሤት ቀርቷል፥ የደስተኞች ድምጽ ዝም ብሏል፥ የመሰንቆ ደስታ ቀርቶአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚያስደስት የመሰንቆ፥ ሙዚቃና የአታሞ ድምፅ መሰማቱ ቀርቶአል፤ የበዓል አከባበር ሁሉ ቆሞአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከበሮው ሐሤት ቀርቷል፥ የደስተኞች ድምጽ ዝም ብሏል፥ የመሰንቆ ደስታ ቀርቶአል። |
በቤተ መቅደስህም እሰግዳለሁ፤ ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህም ስምህን አመሰግናለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና።
ደስታና ሐሤትም ከወይን ቦታሽ ተወስዶአል፤ በወይንሽም ቦታዎች ፈጽመው ደስ አይላቸውም፤ በመጥመቂያውም ወይንን አይረግጡም፤ ረጋጮቹን አጥፍቻለሁና።
በመሰንቆና በበገና፥ በከበሮና በእምቢልታም እየዘፈኑ የወይን ጠጅን ይጠጣሉ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም፤ የእጁንም ሥራ አላስተዋሉም።
ሲኦልም ሆድዋን አስፍታለች፤ አፍዋንም ያለ ልክ ከፍታለች፤ የተከበሩና ታላላቅ ሰዎች ባለጠጎቻቸውና ድሆቻቸውም ወደ እርስዋ ይወርዳሉ።
ስለዚህም የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በዐይናችሁ ፊት በዘመናችሁም የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ ከዚህ ስፍራ አስቀራለሁ።
ከእነርሱም የሐሤትን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራን ድምጽና የሴት ሙሽራን ድምፅ፥ የወፍጮንም ድምፅ የመብራትንም ብርሃን አስቀራለሁ።
ምድሪቱም ባድማ ትሆናለችና ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም አደባባይ የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ አጠፋለሁ።
በእግዚአብሔር ገነት በዔድን ነበርህ፤ የከበረ ዕንቍስ ሁሉ፥ ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮን፥ አልማዝ፥ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያሰጲድ፥ ሰንፔር፥ በሉር፥ የሚያብረቀርቅ ዕንቍ፥ ወርቅም ልብስህ ነበረ፤ የከበሮህና የእንቢልታህ ሥራ በአንተ ዘንድ ነበረ፤ በተፈጠርህበትም ቀን ተዘጋጅተው ነበር።
በገና የሚመቱና የሚዘምሩም ድምፅ እንቢልታንና መለከትንም የሚነፉ ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ የእጅ ጥበብም ሁሉ አንድ ብልሃተኛ እንኳ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይገኝም፤ የወፍጮ ድምጽም ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤