Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሆሴዕ 2:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ደስ​ታ​ዋ​ንም ሁሉ፥ በዓ​ላ​ቶ​ች​ዋ​ንም፥ መባ​ቻ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ ሰን​በ​ቶ​ች​ዋ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቶ​ች​ዋ​ንም ሁሉ አስ​ቀ​ራ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የደስታ በዓሎቿን ሁሉ፣ የዓመት በዓላቷንና የወር መባቻዎቿን፣ ሰንበቶቿንና የተመረጡ በዓላቷን ሁሉ አስቀራለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ስለዚህ እህሌን በጊዜው፥ ወይን ጠጄንም በወቅቱ ፈጽሞ እወስዳለሁ፥ ዕራቁትነትዋንም መሸፈኛ የነበረውን ጥጤንና የተልባ እግሬን እገፍፋታለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የምትደሰትባቸውን በዓላትዋን ሁሉ ሰንበትዋን፥ ዓመታዊና ወርኀዊ በዓላትዋን እሽራለሁ፤ የተለዩ በዓላትዋንም ሁሉ እንዳታከብር አደርጋታለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ስለዚህ እህሌን በጊዜዋ ወይን ጠጄንም በወረትዋ እወስዳለሁ፥ ዕራቁትነትዋንም እንዳትሸፍን ጥጤንና የተልባ እግሬን እገፍፋታለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ሆሴዕ 2:11
17 Referencias Cruzadas  

ዓመት በዓ​ላ​ች​ሁን ጠል​ች​ዋ​ለሁ፤ አር​ቄ​ው​ማ​ለሁ፤ መዓዛ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን አላ​ሸ​ትም።


“እህ​ልን እን​ሸጥ ዘንድ መባ​ቻው መቼ ያል​ፋል? የኢፍ መስ​ፈ​ሪ​ያ​ው​ንም እያ​ሳ​ነ​ስን፥ ሰቅ​ሉ​ንም እያ​በ​ዛን፥ በሐ​ሰ​ተ​ኛም ሚዛን እያ​ታ​ለ​ልን፥


ምድ​ሪ​ቱም ባድማ ትሆ​ና​ለ​ችና ከይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ የእ​ል​ል​ታን ድም​ፅና የደ​ስ​ታን ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽ​ራን ድም​ፅና የሴት ሙሽ​ራን ድምፅ አጠ​ፋ​ለሁ።


ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት በዘ​መ​ና​ች​ሁም የእ​ል​ል​ታን ድም​ፅና የደ​ስ​ታን ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽ​ራን ድም​ፅና የሴት ሙሽ​ራን ድምፅ ከዚህ ስፍራ አስ​ቀ​ራ​ለሁ።


እርስ በእርሳቸው እንደ ተመሰቃቀለ እሾህ ቢሆኑ፥ በመጠጣቸውም ቢሰክሩ እንደ ደረቅ ገለባ ፈጽመው ይጠፋሉ።


ያን​ጊ​ዜም በመ​ቅ​ደ​ሶ​ቻ​ቸው ዋይ ዋይ ይላሉ” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በየ​ስ​ፍ​ራው የሚ​ወ​ድ​ቀው ሬሳ ይበ​ዛ​ልና፤ እነ​ር​ሱም ይጠ​ፋ​ሉና።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ያለ ንጉ​ሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥ​ዋ​ዕ​ትና ያለ ምሥ​ዋዕ፤ ያለ ካህ​ንና ያለ ራእይ፤ ያለ ኤፉ​ድና ያለ ተራ​ፊም ብዙ ወራት ይቀ​መ​ጣ​ሉና፤


የዘ​ፋ​ኞ​ች​ሽ​ንም ብዛት ዝም አሰ​ኛ​ለሁ፤ የመ​ሰ​ን​ቆ​ሽም ድምፅ ከዚያ ወዲያ አይ​ሰ​ማም።


ከእ​ነ​ር​ሱም የሐ​ሤ​ትን ድም​ፅና የደ​ስ​ታን ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽ​ራን ድም​ጽና የሴት ሙሽ​ራን ድምፅ፥ የወ​ፍ​ጮ​ንም ድምፅ የመ​ብ​ራ​ት​ንም ብር​ሃን አስ​ቀ​ራ​ለሁ።


ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም በስ​ም​ን​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን በይ​ሁዳ እን​ደ​ሚ​ደ​ረግ በዓል ያለ በዓል አደ​ረገ፤ ለሠ​ራ​ቸ​ውም ጥጆች ይሠዋ ዘንድ በቤ​ቴል ወደ ሠራው መሠ​ዊያ ወጣ፤ ለኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችም የመ​ረ​ጣ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ያን ካህ​ናት በቤ​ቴል አኖ​ራ​ቸው።


ዲቃ​ሎ​ችን ልጆች ወል​ደ​ዋ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከድ​ተ​ዋል፤ አሁ​ንም ኵብ​ኵባ እነ​ር​ሱ​ንና ርስ​ታ​ቸ​ውን ይበ​ላ​ቸ​ዋል።


ጕል​በ​ታ​ች​ሁም በከ​ንቱ ያል​ቃል፤ ምድ​ራ​ች​ሁም እህ​ል​ዋን አት​ሰ​ጥም፤ የዱር ዛፎ​ችም ፍሬ​ያ​ቸ​ውን አይ​ሰ​ጡም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios