Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 137 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የሐ​ጌና የዘ​ካ​ር​ያስ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።

1 አቤቱ፥ በፍ​ጹም ልቤ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥ የአ​ፌን ነገር ሁሉ ሰም​ተ​ኸ​ኛ​ልና፤ በመ​ላ​እ​ክት ፊት እዘ​ም​ር​ል​ሃ​ለሁ።

2 በቤተ መቅ​ደ​ስ​ህም እሰ​ግ​ዳ​ለሁ፤ ስለ ምሕ​ረ​ት​ህና ስለ እው​ነ​ት​ህም ስም​ህን አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስም​ህን ከፍ ከፍ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና።

3 በጠ​ራ​ሁህ ቀን በፍ​ጥ​ነት አድ​ም​ጠኝ፤ ነፍ​ሴን በኀ​ይ​ልህ በብዙ አጸ​ና​ሃት።

4 አቤቱ፥ የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፤ የአ​ፍ​ህን ቃል ሁሉ ሰም​ተ​ዋ​ልና።

5 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምስ​ጋና ይዘ​ም​ራሉ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ታላቅ ነውና።

6 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ያለ ነውና፥ የተ​ዋ​ረ​ዱ​ት​ንም ይመ​ለ​ከ​ታ​ልና፤ ትቢ​ተ​ኛ​ው​ንም ከሩቁ ያው​ቀ​ዋል።

7 በመ​ከራ መካ​ከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ታድ​ነ​ኛ​ለህ፤ በጠ​ላ​ቶች ቍጣ ላይ እጆ​ች​ህን ትዘ​ረ​ጋ​ለህ፥ ቀኝ​ህም ያድ​ነ​ኛል

8 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይበ​ቀ​ል​ል​ኛል፤ አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ትህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነው፤ አቤቱ የእ​ጅ​ህን ሥራ ቸል አት​በል።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos