ኢሳይያስ 16:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ደስታና ሐሤትም ከወይን ቦታሽ ተወስዶአል፤ በወይንሽም ቦታዎች ፈጽመው ደስ አይላቸውም፤ በመጥመቂያውም ወይንን አይረግጡም፤ ረጋጮቹን አጥፍቻለሁና። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ደስታና ሐሤትም ከአትክልቱ ቦታ ተወግዷል፤ በወይን ተክልም ቦታ ዝማሬ የለም፤ እልልታም ቀርቷል። በወይን መጭመቂያ ቦታ የሚረግጥ የለም፤ የረጋጮችን ሆታ አጥፍቻለሁና። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ደስታና ሐሴትም ከፍሬያማው እርሻ ተወስዶአል፤ በወይኑም ቦታዎች ዝማሬና እልልታ የለም፤ በመጥመቂያም ወይን የሚረግጥ የለም፤ የረጋጮቹን እልልታ አጥፍቻለሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 እነሆ በፍሬያማው የእርሻ ቦታ አንድ እንኳ ደስተኛ የለም፤ በወይን ተክል ቦታዎች የእልልታና የዝማሬ ድምፅ አይሰማም፤ የወይን ጠጅ ለመጥመቅ የወይን ፍሬ የሚጨምቅ የለም፤ እግዚአብሔር የደስታ እልልታን ሁሉ እንዲቆም አድርጎአል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ደስታና ሐሴትም ከፍሬያማው እርሻ ተወስዶአል፥ በወይኑም ቦታዎች ዝማሬና እልልታ የለም፥ በመጥመቂያም ወይን የሚረግጥ የለም፥ የረጋጮቹን እልልታ አጥፍቻለሁ። Ver Capítulo |