ሕልሙም ለፈርዖን ደጋግሞ መታየቱ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቈረጠ ስለሆነ ነው፤ እግዚአብሔርም ፈጥኖ ያደርገዋል።
ኢሳይያስ 14:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሎአል፥ “እንደ ተናገርሁ በእርግጥ ይሆናል፤ እንደ መከርሁም እንዲሁ ይጸናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሏል፤ “እንደ ዐቀድሁት በርግጥ ይከናወናል፤ እንደ አሰብሁትም ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራዊት ጌታ እንዲህ ብሎ ምሏል፦ “እንደ ተናገርሁ በእርግጥ ይሆናል፥ እንዳሰብሁም እንዲሁ ይቆማል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራዊት አምላክ እንዲህ ሲል ምሎአል፥ “ያቀድኩት ነገር ሁሉ ተፈጻሚ ይሆናል፤ የወሰንኩትም ነገር ሥራ ላይ ይውላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሎአል፦ እንደ ተናገርሁ በእርግጥ ይሆናል፥ እንዳሰብሁም እንዲሁ ይቆማል። |
ሕልሙም ለፈርዖን ደጋግሞ መታየቱ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቈረጠ ስለሆነ ነው፤ እግዚአብሔርም ፈጥኖ ያደርገዋል።
የይሁዳም ምድር ግብፅን የምታስደነግጥ ትሆናለች፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከመከረባት ምክር የተነሣ ስምዋን የሚሰማ ሁሉ ይፈራል።
ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ ይላል እግዚአብሔር፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።
ስለዚህ እናንተ በግብፅ ምድር የምትኖሩ አይሁድ ሁሉ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ በግብፅ ምድር ሁሉ በሚኖር በይሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእንግዲህ ወዲህ፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ተብሎ እንዳይጠራ፥ እነሆ በታላቁ ስሜ ምያለሁ፥” ይላል እግዚእብሔር።
ስለዚህ እግዚአብሔር በኤዶምያስ ላይ የመከረባትን ምክር፥ በቴማንም በሚኖሩ ስዎች ላይ ያሰባትን ዐሳብ ስሙ፤ ትንንሾች በጎችን ዘርፈው ይወስዷቸዋል፤ የሚኖሩባትንም ማደሪያቸውን ባድማ ያደርጉባቸዋል።
ስለዚህ እግዚአብሔር በባቢሎን ላይ የመከረባትን ምክር፥ በከለዳውያንም ምድር ላይ ያሰባትን ዐሳብ ስሙ፤ በእውነት የበጎቻቸቸው ጠቦቶች ይጠፋሉ፤ በእውነት ማደሪያዎቻቸውም ባድማ ይሆናሉ።
እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ እናገራለሁ፤ የምናገረውም ቃል ይፈጸማል፤ ደግሞም አይዘገይም፤ እናንተ ዐመፀኛ ቤት ሆይ! በዘመናችሁ ቃሌን እናገራለሁ፤ እፈጽመውማለሁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
አንተና ጭፍሮችህ ሁሉ፥ ከአንተም ጋር ያሉ ሕዝብ በምድረ በዳ ፊት ትወድቃላችሁ፤ ለሚናጠቁ ወፎች ሁሉና ለምድር አራዊትም መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።
ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይደነግጡምን? ወይስ እግዚአብሔር ያላዘዘው ክፉ ነገር በከተማ ላይ ይመጣልን?
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “አባት ሆይ! የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።
ሥራዉ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈጸም፥ “እንግዲህ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቍጣዬ ማልሁ” እንዳለ እኛስ ያመንን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን።
እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ፥ ያጠፉአቸው ዘንድ እንዳይራሩላቸው ፈጽመው እንዲያጠፉአቸው፥ ከእስራኤል ጋር ይጋጠሙ ዘንድ ልባቸውን እንዲያደነድኑ እግዚአብሔር ልባቸውን አጸና።