Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 14:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 “ባቢ​ሎ​ንን የወ​ፎች መኖ​ሪያ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ እንደ ኢም​ን​ትም ትሆ​ና​ለች፤ በጥ​ፋ​ትም እንደ ረግ​ረግ ጭቃ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ” ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 “የጃርት መኖሪያ፣ ረግረጋማ ቦታ አደርጋታለሁ፤ በጥፋትም መጥረጊያ እጠርጋታለሁ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 የጃርት መኖርያ የውሃም መቋሚያ አደርጋታለሁ፤ በጥፋትም መጥረጊያ እጠርጋታለሁ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ባቢሎንን ረግረግ ስለማደርጋት የአልቅት መፈልፈያ ትሆናለች፤ ባቢሎንን ሁሉን ነገር ጠራርጎ በሚወስድ መጥረጊያ እጠርጋታለሁ፤ እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 የጃርት መኖርያ የውሃም መቋሚያ አደርጋታለሁ፥ በጥፋትም መጥረጊያ እጠርጋታለሁ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 14:23
17 Referencias Cruzadas  

መንጎችም የምድርም አራዊት ሁሉ በውስጥዋ ይመሰጋሉ፣ ይብራና ጃርት በዓምዶችዋ መካከል ያድራሉ፣ ድምፃቸው በመስኮቶችዋ ይጮኻል፣ የዝግባም እንጨት ሥራ ይገለጣልና በመድረኮችዋ ላይ ጥፋት ይሆናል።


ሌላም ሁለተኛ መልአክ “አሕዛብን ሁሉ የዝሙትዋን ቍጣ ወይን ጠጅ ያጠጣች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች!” እያለ ተከተለው።


ስለ​ዚህ እነሆ፥ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት ላይ መከ​ራን አመ​ጣ​ለሁ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ም​ንም አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ፤ አጥር ተጠ​ግቶ እስ​ከ​ሚ​ሸን ወንድ ድረስ አላ​ስ​ቀ​ር​ለ​ትም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ይነ​ግሥ ዘንድ አል​ተ​ወ​ውም፤ ሰው ገለባ እስ​ኪ​ያ​ልቅ ድረስ እን​ደ​ሚ​ያ​ነ​ድድ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት ላይ እሳ​ትን አነ​ዳ​ለሁ።


በብርቱም ድምፅ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፤ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤


የሰ​ማ​ር​ያ​ንም ገመድ የአ​ክ​ዓ​ብ​ንም ቤት ቱንቢ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ የሽቱ ዕቃ እን​ዲ​ወ​ለ​ወል ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ወል​ውዬ በፊቷ እገ​ለ​ብ​ጣ​ታ​ለሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ቀር​ቦ​አ​ልና አል​ቅሱ፤ ጥፋ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይመ​ጣል።


ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባት አይ​ገ​ኝም፤ ከት​ው​ል​ድም እስከ ትው​ልድ ድረስ ሰው አይ​ኖ​ር​ባ​ትም፤ ዓረ​ባ​ው​ያ​ንም በእ​ርሷ አያ​ል​ፉም፤ እረ​ኞ​ችም በው​ስ​ጥዋ አያ​ር​ፉም።


ስለ ምድረ በዳ የተ​ነ​ገረ ቃል፤ ዐውሎ ነፋስ በም​ድረ በዳ እን​ደ​ሚ​ያ​ልፍ፥ እን​ዲሁ ከሚ​ያ​ስ​ፈራ ሀገር ከም​ድረ በዳ ይመ​ጣል።


ሕዝቤ ከሰ​ሜን በእ​ር​ስዋ ላይ ወጥ​ት​ዋል፤ ምድ​ር​ዋ​ንም ባድማ ያደ​ር​ጋል፤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም አይ​ገ​ኝም፤ ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ ድረስ ሸሽ​ተው ሄደ​ዋል።


ጊዜዋ ደር​ሶ​አ​ልና ሣጥ​ኖ​ች​ዋን ከፍ​ታ​ችሁ እንደ ዋሻ በር​ብ​ሯት፤ ጨር​ሳ​ች​ሁም አጥ​ፏት፥ ምንም አታ​ስ​ቀ​ሩ​ላት።


አቤቱ! ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ ድረስ ማንም እን​ዳ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባት፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ባድማ እን​ድ​ት​ሆን ታጠ​ፋት ዘንድ በዚች ስፍራ ላይ ተና​ግ​ረ​ሃል በል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios