Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 55:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ዐሳቤ እንደ ዐሳ​ባ​ችሁ፥ መን​ገ​ዴም እንደ መን​ገ​ዳ​ችሁ አይ​ደ​ለ​ምና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ፣ መንገዴ እንደ መንገዳችሁ አይደለምና” ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ፥ መንገዴም እንደ መንገዳችሁ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 አሳቤ እንደ አሳባችሁ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና፥ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 55:8
19 Referencias Cruzadas  

ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ እኔ በፊ​ትህ እጅግ ታናሽ ስሆን ስለ ባሪ​ያህ ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተና​ገ​ርህ፤ ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ይህ የሰው ሕግ ነው።


ንዕ​ማን ግን ተቈ​ጥቶ ሄደ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነሆ፥ ወደ እኔ የሚ​መጣ፥ ቆሞም የአ​ም​ላ​ኩን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም የሚ​ጠራ፥ የለ​ም​ጹ​ንም ስፍራ በእጁ ዳስሶ የሚ​ፈ​ው​ሰኝ መስ​ሎኝ ነበር።


ወደ ሰማይ ተመ​ል​ከት፥ እይም፤ ደመ​ናም ከአ​ንተ በላይ ምን ያህል ከፍ እን​ዳለ ዕወቅ።


በእ​ጃ​ቸው ተን​ኮል አለ​ባ​ቸው፥ ቀኛ​ቸ​ውም መማ​ለ​ጃን ተሞ​ል​ታ​ለች።


ልጆቼ ኑ፥ ስሙኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት አስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ዘንድ፤


ጠላ​ቶ​ቼም በላዬ ክፋ​ትን ይና​ገ​ራሉ፦ “መቼ ይሞ​ታል? ስሙስ መቼ ይሻ​ራል?” ይላሉ።


ምስ​ክ​ርህ እጅግ የታ​መነ ነው፤ አቤቱ፥ እስከ ረዥም ዘመን ድረስ ለቤ​ትህ ምስ​ጋና ይገ​ባል።


እግዚአብሔር ለጠማሞች ጠማማ ሥራን ይልክባቸዋል፤ ሥራው የቀናና ንጹሕ ነውና።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ምሎ​አል፥ “እንደ ተና​ገ​ርሁ በእ​ር​ግጥ ይሆ​ናል፤ እንደ መከ​ር​ሁም እን​ዲሁ ይጸ​ናል።


እኛ ሁላ​ችን እንደ በጎች ተቅ​በ​ዝ​ብ​ዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ገዛ መን​ገዱ አዘ​ነ​በለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ለሞት አሳ​ልፎ ሰጠው።


ፈቃ​ድ​ህን በተ​ቀ​ደ​ሰው ቀኔ ከማ​ድ​ረግ እግ​ር​ህን ከሰ​ን​በት ብት​መ​ልስ፥ ሰን​በ​ት​ንም ደስታ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቀ​ደሰ ብታ​ደ​ር​ገው፥ ክፉ ሥራን ለመ​ሥ​ራት እግ​ር​ህን ባታ​ነሣ፥ በአ​ፍ​ህም ክፉ ነገ​ርን ባት​ና​ገር፥


በጽ​ድቅ መን​ገድ ወደ​ማ​ይ​ሄዱ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ወደ​ሚ​ከ​ተሉ ዐመ​ፀ​ኞች ሕዝብ ቀኑን ሁሉ እጆ​ችን ዘረ​ጋሁ።


“ሥራ​ቸ​ው​ንና አሳ​ባ​ቸ​ውን ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤ እነ​ሆም እኔ እመ​ጣ​ለሁ፤ አሕ​ዛ​ብ​ንና ልሳ​ና​ት​ንም ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይመ​ጣሉ፤ ክብ​ሬ​ንም ያያሉ።


“ሰው ሚስ​ቱን ቢፈታ፥ ከእ​ር​ሱም ዘንድ ሄዳ ሌላ ወንድ ብታ​ገባ፥ በውኑ ደግሞ ወደ እርሱ ትመ​ለ​ሳ​ለ​ችን? ያች ሴት እጅግ የረ​ከ​ሰች አይ​ደ​ለ​ች​ምን? አን​ቺም ከብዙ እረ​ኞች ጋር አመ​ን​ዝ​ረ​ሻል፤ ወደ እኔም ትመ​ለ​ሻ​ለ​ሽን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት፦ የጌታ መን​ገድ የቀ​ናች አይ​ደ​ለ​ችም ይላሉ። የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በውኑ መን​ገዴ የቀ​ናች አይ​ደ​ለ​ች​ምን? ይል​ቅስ የእ​ና​ንተ መን​ገድ ያል​ቀ​ናች አይ​ደ​ለ​ች​ምን?


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ጣዖት ለኤ​ፍ​ሬም ምን​ድን ነው? እኔ አደ​ከ​ም​ሁት፤ አጸ​ና​ሁ​ትም፤ እኔ እንደ ተወ​ደደ አበባ አፈ​ራ​ዋ​ለሁ፤ ፍሬ​ህም በእኔ ዘንድ ይገ​ኛል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ፊቱን፥ የቁ​መ​ቱ​ንም ዘለ​ግታ አትይ፤ ሰው እን​ደ​ሚ​ያይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አያ​ይ​ምና ናቅ​ሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ልብን ያያል” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos