እንዲህም አለ፥ “ቸርነቱንና እውነቱን ከጌታዬ ያላራቀ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ ለእኔም ወደ ጌታዬ ወደ አብርሃም ወንድም ቤት መንገዴን አቀናልኝ።”
ዘፍጥረት 32:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ ከወንድሜ ከዔሳው እጅ አድነኝ፤ መጥቶ እንዳያጠፋኝ፥ እናትን ከልጆችዋ ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከወንድሜ ከዔሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤ መጥቶ እኔንም ሆነ እነዚህን እናቶች ከነልጆቻቸው ያጠፋናል ብዬ ፈርቻለሁና፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከወንድሜ ከዔሳው እጅ አድነኝ፥ መጥቶ እንዳያጠፋኝ፥ እናቶችንም ከልጆች ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእኔ ላይ አደጋ በመጣል ሴቶችና ሕፃናት እንኳ ሳይቀሩ ያጠፋናል ብዬ ስለ ፈራሁ ከወንድሜ ከዔሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከወንድሜ ከዔሳው እጅ አድነኝ፤ መጥቶ እንዳያጠፋኝ እናቶችንም ከልጆች ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና። |
እንዲህም አለ፥ “ቸርነቱንና እውነቱን ከጌታዬ ያላራቀ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ ለእኔም ወደ ጌታዬ ወደ አብርሃም ወንድም ቤት መንገዴን አቀናልኝ።”
ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፤ ዔሳውም በልቡ አለ፥ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ትቅረብ፤ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”
ለርብቃም ታላቁ ልጅዋ ዔሳው ያለው ተነገራት፤ ታናሹን ልጅዋን ያዕቆብንም ልካ ጠራችው፤ አለችውም፥ “እነሆ ወንድምህ ዔሳው ያድድንሃል፤ ሊገድልህም ይፈልጋል።
ያዕቆብም እጅግ ፈራ፤ የሚያደርገውንም አጣ። ከእርሱም ጋር ያሉትን ሰዎች ላሞችንም፥ ግመሎችንም፥ በጎችንም ሁለት ወገን አድርጎ ከፈላቸው፤
ንጉሡ ዳዊትም ገባ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ፥ “ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ ይህን ያህል የወደድኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድን ነው?
በሕዝብህም መካከል ጥፋት ይነሣል፤ እናትም በልጆችዋ ላይ በተጣለች ጊዜ የሰልማን አለቃ ቤትአርብኤልን በጦርነት ቀን እንዳፈረሰ፥ አምባዎችህ ሁሉ ይፈርሳሉ።
“በመንገድ በማናቸውም ዛፍ ላይ ወይም በመሬት ላይ ከጫጭቶችና ከእንቍላል ጋር እናቲቱ በእነዚህ ላይ ተቀምጣ የወፍ ጎጆ ብታገኝ እናቲቱን ከጫጭቶችዋ ጋር አትውሰድ።
እነርሱም፦ እግዚአብሔርን ትተን በዓሊምንና ምስሎቹን በማምለካችን በድለናል፤ አሁንም ከጠላቶቻችን እጅ አድነን፤ እናመልክሃለንም” ብለው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ ።
አሁንም የእስራኤል ንጉሥ ማንን ለማሳደድ ወጥተሀል? አንተስ ማንን ታሳድዳለህ? የሞተ ውሻን ታሳድዳለህን? ወይስ ቍንጫን ታሳድዳለህ?